TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የከተማው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንሰፔክተር ከበደ ገመዴ እንደገለጹት በይርጋጨፌ ከተማ #ትላንት ማምሻውን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ቤት ከሙሉ ንብረቱ ጋር #ሊወድም ችሏል።

በከተማው በተለምዶ #ደንቦስኮ ሰፈር በሚባለው አከባቢ በ25 ሊትር ጀርካኖች ተቀድቶ የተቀመጠ ነዳጅ #ፈንድቶ እሳት ማንሳቱን ተከትሎ አደጋው መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡

በአደጋው የስድስት ወር አራስ እናትና ልጇን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበት በይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን ተናግረዋል።

“ቃጠሎው ወደ ሌሎች ቤቶች #እንዳይዛመት ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ጥረት ለማስቆም ተችሏል” ያሉት ኢንስፔክተሩ አደጋው በደረሰበት ቤት የችርቻሮ የነዳጅ ሽያጭ ይካሄድ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

በከተማው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጎዳና ላይ የነዳጅ ሽያጭ መበራከቱን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ንረትና እጥረት ከመታየቱም ባለፈ ለተለያዩ አደጋዎች መንስኤ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ከሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ባለፈ በአያያዝና አጠቃቀም ጉድለት ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አልሰማሁም፤ አላየሁም እንዳትሉ...
(TIKVAH-ETHIOIA)

የጥላቻ ንግግር የዘር ማጥፋት ዋነኛ መሰረት ነው። የጥላቻ ንግግር ከጀርባው #ያላስተናገደ አንዳች አይነት የዘር ማጥፋት በዓለማችን አልተፈፀመም፡፡

#ናዚ በአይሁዳዊያን ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት መፈፀም ከመጀመሩ በፊት #ጀርመናዊያን በአይሁዶች ላይ የከፋ ጥላቻን እንዲያዳብሩ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ መደላድልን ሰርቷል፡፡

#በሩዋንዳ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ከደረሰው የዘር ማጥፋት ጀርባ #በሬዲዮ ፕሮፖጋንዳ ጭምር የታገዘ #የጥላቻ_ንግግር_ዘመቻ ነበር፡፡

(በተሾመ ታደሰ)

#StopHateSpeech

TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በመላው ሀገሪቱ እያደረግን ያለነውን #የፀረ_ጥላቻ_ንግግር ዘመቻ #እንድትደግፉን እንለምናለን!!

ስልክ፦ 0919 74 36 30

🇪🇹ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ🇪🇹

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋር ክልል ጥቃት ተፈፀመ‼️

#ሰኞ መጋቢት 16 እና #ማክሰኞ መጋቢት 17 በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ከጎረቤት ሀገራት መጡ የተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ። ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ አዋሳኝ አካባቢዎች በኩል በገቡ ኃይሎች መሆኑን የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ኻሌይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/በአፋር-ክልል-ጥቃት-ተፈፀመ-04-04-2
#update ከመጋቢት 27 ቀን 2011 አ.ም እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

የአውሮፕላን ነዳጅ...

በመጋቢት ወር #ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር ብር 22 ከ74 ሳንቲም በአለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 2 ብር ከ 12 ሳንቲም በመጨመር በሊትር ብር 24 ከ 86 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

#FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥላቻ #የሚገድለው ጠይውን እንጂ ተጠይውን አይደለም!! ጥላቻ በሽታ ነው፤ ምንም ጥያቄ የሌለው በሽታ!!

ፍቅር፤ ተስፋ፤ አንድነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሦስት የተቀዋሚ ድርጅት አመራሮች ወደ በርሊን አቅንተው ከጀርመን ቡንድስታግ (ፓርላማ) ጋር ተነጋግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ከአርበኞች ግንቦት 7 ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ከኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግሬስ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)፣ ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሌንጮ ለታ በጉብኝቱ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሽታየ ምናለ እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳም ተገኝተዋል፡፡ ከቡድኑ ጋር የተመካከሩት የቡንድስታጉ ምክትል አፈ ጉባዔ ክላውዲያ ሩዝ ሲሆኑ ለቡድኑ ስለ ጀርመን ፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትና ምርጫ ሕግጋት ገለጻ ተደርጎለታል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ናይጄሪያ ከ110 #ኤምባሲዎቿ መካከል በበጀት ማነስ ምክንያት 80ዎቹን ልትዘጋ እንደምትችል ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት የተመደበው በጀት ለ30 ኤምባሲዎች ወጪ ብቻ እንደሚበቃ ነው የተነገረው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነገው ዕለት የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር አዲስ እየተዘጋጀ ባለው #የፀረ_ጥላቻ_ንግግር ረቂቅ ህግ ላይ ውይይት ያደርጋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ቦይንግ ካምፓኒ ሃላፊነቱን ወሰደ። ቦይንግ ካምፓኒ 346 ሰወች ለሞቱበት በቦይንግ 737 ማክስ 8 ሁለት አውሮፕላኖች ላይ ለደረሱት አደጋዎች ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቆ በአደጋው ለሞቱ ሰወች ቤተሰቦችም #ይቅርታ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ዛሬ ያወጣውን የመጀመሪያ ደረጃ መግለጫ ተከትሎ ቦይንግ ማምሻውን በሃላፊው በዴኒስ ሙሊንበርግ በኩል በሰጠው መግለጫ የኢንዶኔዥያውም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰው አደጋ ከሶፍትዌር ጋር የተያያዘ መሆኑን አምኖ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰወችም ይቅርታ መጠየቁን ዋሽንግተን ፖስት ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🇪🇹ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ🇪🇹
🇪🇹ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ🇪🇹
🇪🇹ለቀጣዩ ትውልድ ኢትዮጵያን እናውርስ🇪🇹

#StopHateSpeech - በዚህ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ከTIKVAH-ETH ጋር በጋራ ለመራት እና ለእናት ሀገራችሁ ሰላም እና ብሩህ ተስፋ አስተዋፅኦ ማድረግ የምትፈልጉ የመንግስት ተቋማት እና የግል ድርጅቶችን ልታግዙን ትችላላችሁ!!

ደውሉልን 0919 74 36 30

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሶማሌ ክልል ኖጎብ፣ ኤረር፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ዶሎ፣ ሊባን፣ ጃራር እና ሲቲ የተባሉ አካባቢዎች አስከፊ የምግብ እና የውሐ እጦት እንደገጠማቸው አስታውቋል። ኦብነግ የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሰዎች ከመሞታቸው በፊት ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስቧል። በተለይ አርብቶ አደሮች በሚኖሩባቸው ምሥራቅ እና ደቡብ ምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከጥር እስከ ግንቦት የሚጠበቀው ዝናብ ባለመጣሉ ሥጋት መፈጠሩን ዓለም አቀፉ የረሐብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በዚህ ሳምንት ገልጾ ነበር። ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የግጦሽ መሬት እና የከርሰ ምድር ውሐ እንደሚጠበቀው አላገገሙም። በዚህ ወቅት የሚጠበቀው ዝናብ በደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ ሶማሌ ባለመጀመሩ አካባቢው ከወትሮው የተለየ ከባድ ሙቀት እንደገጠመው በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) የተመሰረተው የረሐብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ አትቷል። በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና በጉጂ ዞኖች መጣል የነበረበት ዝናብ ከየካቲት አጋማሽ እስከ መጋቢት አጋማሽ ቢጥልም በቂ አይደለም።

Via እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባምንጭ ዝግጁ

የኢትዮጵያ ልጆች #የምንሰባሰብበት #የStopHateSpeech መድረክ ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ምሽት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ...

#TIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት በዝግጅቱ ላይ ተካፋይ ይሆናሉ!! #ethiopia

ሀገራችን #እንዳትፈርስ ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ! ጥላቻ ሀገር ያፈርሳል!!

🇪🇹ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ🇪🇹

ስልክ፦ 0919 74 36 30

አዘጋጅ፦

•TIKVAH-ETH
•የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
•የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ፎረም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይና አቶ ለማ🚁በደሌ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ማለዳ ላይ ነው በደሌ ከተማ የገቡት።

በበደሌ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ከቡኖ በደሌ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia