TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኒፕሲ ገዳይ ማን እንደሆነ ታወቀ‼️

በአባቱ ኤርትራዊ እንደሆነ የተነገረው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኒፕሲ ሐስልን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብን ፖሊስ መያዙን አስታወቀ።

ባለስልጣናት እንዳሉት ኤሪክ ሆልደር የተባለው ግለሰብ ከእሁድ ዕለቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ በፖሊስ ሲፈለግ ነበር። ኒፕሲ ሐስል በተሰነዘረበት ጥቃት የተገደለው የእራሱ በሆነው የልብስ መደብር አቅራቢያ ነበር። በጥቃቱ ሌሎች ሁለት ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

እሁድ ዕለት በተከፈተበት ተኩስ የተገደለው የራፕ ሙዚቀኛው ኒፕሲ ሐስልን ለማሰብ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ አድናቂዎቹ የተገኙ ሲሆን በስፍራው በተፈጠረ መጨናነቅ ቢያንስ 19 ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

ትክክለኛ መጠሪያው ኤርሚያስ ዳቪድሰን አስገዶም የሆነው ኒፕሲ ሐስል በደቡባዊ ሎስአንጀለስ ውስጥ ያደገ ሲሆን በታዳጊነት እድሜው የአንድ የጎዳና ላይ የወሮበሎች ቡድን አባል ነበረ።

በኋላ ላይ ግን ከቡድኑ በመውጣት በዙሪያው ያለን ማህበረሰብን ማስተባበርና መርዳት ጀምሮ በጥበብ ሥራዎች ውስጥም አስተዋጽኦን ሲያበረክት ቆይቷል። ከመገደሉ ቀደም ብሎ በትዊተር ገጹ ላይ “ጠንካራ ጠላት ካለህ መባረክ ነው” ሲል አስፍሮ ነበር።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት...

ባሳለፍነው ሳምንት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው ተብሎ የተሰራጨው ዜና #የተሳሳተ መረጃ ነው ሲል የናፍያድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ገለፀ፡፡

እንደ ተቋሙ ገለፃ የተቋሙ ባለቤት #ናፍያድ_ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚል ድርጅት ስም በከፈቱት አካውንት ከሳሽ ለተባሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ ምንም አይነት ቼክ እንዳልሰጡ እና ከግለሰቡ ጋርም በስራ ዘርፍም ሆነ በሌላ ጉዳይ የማይገናኙ እንደሆኑ ጠቅሶ ተሰጠ የተባለው ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ መሰረቁን ቀደም ተብሎ ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረገ ገልጾአል።

በጉዳዩ ላይ ክስ ተመስርቶ እየታየ እንደነበር የገለፀው የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለዚህም ድርጅቱ ከሚገኝበት ከኦሮምያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፖሊስ የደረሰበትን ውጤት የሚያሳይ ለተቋሙ የተፃፈን ደብዳቤን አቅርቧል፡፡

ፖሊስ ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ ከወጋገን ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ስለመሰረቁ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው የወንጀል ምርመራ በሚመለከት የፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ይጠቁማል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ከሳሽ ነኝ ያሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ የተባሉት ግለሰብ በጠፋው ቼክ ጉዳይ ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮምያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ እና በዋስ መብት የተለቀቀቁ" ናቸው ያለው የህዝብ ግኝኑነት ክፍሉ “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኃል እንዲሉ በተገላቢጦሽ ግለሰቡ ከሳሽ ሆኖ መቅረባቸው አስገራሚ ሆኖብናል” ያለ ሲሆን ጉዳዩ በህግ የተያዘ መሆኑን አስታውሶ "ክሱ ሆን ተብሎ የድርጅቱን ባለቤት እና የተቋሙን መልካም ስም ለማጉደፍ የተቀናባበረ" መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

Via ሸገር ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech🔝

የትላንት ምሽቱ የTIKVAH_ETHIOPIA #STOP_HATE_SPEECH 3ኛው መድረክ እጅግ በጣም በተሳካ ሁኔታ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ(WSU) በተገኙበት ተካሂዷል። ዶክተር ታከለ #ለመላው ሀገራችን ህዝብ የሚሆኑ #ጠንካራ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትም በቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

⌚️ምሽት 1:30 የዶክተሩን ንግግር ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን አቀርብላችኃለሁ!!

ማስታወሻ🗓

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ #StopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ስለሚኖር ተዘጋጁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
etv Live🔝

#ከመጋቢት_እስከ_መጋቢት በሚል ርዕስ የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ ሀላፊነታቸውን የተረከቡበት #1ኛ_ዓመት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተከበረ ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: #የStopHateSpeech እንቅስቃሴ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ #ፕሬዘዳንቱ ዶክተር #ታከለ_ታደሰ በተገኙበት የመጨረሻው መድረክ ተካሂዷል።

ፎቶ፦ @odansiif
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech

ደካማ አመራሮች...

"የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ያደረጉት ደካማ አመራሮች ነበሩ። አንዱ ሌላውን #እንዲገድል ጎራዴ በመኪና ተጭኖ እንዲጓዝ ሲያደርጉ የነበሩት አመራሮች ናቸው። ... በሙሉ ሲሰበክ የነበረው #ጥላቻ፤ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ነው። አማራው ኦሮሞው ላይ፤ አማራው ትግሬው ላይ እንዲነሳ፤ ወላይታ ሲዳማ ላይ፤ ሲዳማ ወላይታ ላይ እንዲነሳ ሲሰራ ከርሟል ይሄ ድምር ውጤት ደግሞ #የመንግስት ነው።" አዲሱ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ_ታደሰ በTIKVAH-ETH የStopHateSpeech 3ኛው መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia