#update የቻይና ከተማ የሆነችው ሻንጋይ የ5ጂ የቴሌኮም ኔትወርክ አገልግሎት በመስጠት በአለም #ቀዳሚ መሆኗን አስታወቀች፡፡ ከተማዋ ይህን አዲስ የቴሌኮም ቴክኖሎጂ ይፋ ያደረገችው በሙከራ ደረጃ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም ሂደት ኔትወርኩ ከተማውን ሙሉ ለሙሉ እንዲሸፍን ለማድረግ ባለፉት ሶስት ወራት ቴክኖሎጂውን መሸከም የሚችሉ ጣቢያዎች መተከላቸውን ተነግሯል። ይህም አዲስ መሰረተ ልማት ቻይና አሜሪካንና ሌሎች ሀገሮችን በመቅደም ቀጣዮ ትውልድ የሞባይል ኮሙኒኬሽን ለመፍጠር ምቹ ሁኔታ እንደሚያመቻች ተመልክቷል፡፡ ቀጣዮ ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ እንደሆነ የሚነገርለት የ5ጂ የቴሌኮም ኔትወርክ ከ4ጂ ቴክኖሎጂ ይልቅ መረጃዎችን ከኢንተርኔት ከ10 እስከ 100 እጥፍ በሆነ ፍጥነት የማውረድ አቅም አለው፡፡
ምንጭ፦ቢዝነስ ስታንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ቢዝነስ ስታንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኒፕሲ ሐስል ተገደለ‼️
ትውልደ ኤርትራዊው የሎስ አንጀለሱ ታዋቂ ራፐር፣ #ኤርምያስ_አስገዶም (ኒፕሲ ሐስል) በተከፈተበት ተኩስ ሎስ አንደለስ ውስጥ መገደሉን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
የ33 ዓመቱ ራፐር በርካታ ቦታዎች ላይ በጥይት መመታቱን እና ሆስፒታል እንደደረሰ ሕይወቱ ማለፉን ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘግቧል። ሌሎች ሁለት ሰዎችም በተተኮሰባቸው ጥይት #ቆስለዋል።
ከኤርትራዊ አባት እና ጥቁር አሜሪካዊ እናት የተወለደው ኤርሚያስ አስገዶም በዚህ ዓመት ለሽያጭ ያበቃው አልበሙ በግራሚ የምርጥ ራፕ አልበሞች ምርጫ ላይ እጩ ለመሆን በቅቶ ነበር።
ሞቱ ካስደነገጣቸው ታዋቂ ሰዎች መካከል አንዷ ሪሃና ስትሆን "በዚህ ዜና መንፈሴ ታውኳል" ስትል የቲውተር ገጿ ላይ አስፍራለች።
ኤርሚያስ አስገዶም ተወልዶ ያደገው በደቡባዊ ሎስ አንጀለስ ሲሆን በተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችና በኪነጥበብ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል።
"ያደኩት በውንብድና ቡድኖች ውስጥ ነው" ሲል ለሎስ አንጀለስ ታይምስ በአንድ ወቅት ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ ነበር "... ሞት፣ ግድያ የየእለት ትዕይንቶቻችን ነበሩ። በጦርነት ቀጠና ውስጥ እንደመኖር ነው፤ ከዚህ መንደር ሰዎች ሲሞቱ ከቁብ አይቆጠርም ነበር።"
ኤርሚያስ ከመገደሉ በፊት በነበረ አንድ እሁድ "አምርሮ የሚጠላህ ሲኖር መባረክ ነው" በማለት በቲውተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
Via BBC

#update በጉጂና ጌዴኦ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ እየተሰራ ነው።
https://telegra.ph/በጉጂና-ጌዴኦ-በተፈጠረው-ግጭት-የተፈናቀሉ-ዜጎች-ሙሉ-ለሙሉ-ለመመለስ-እየተሰራ-ነው-04-01

Telegraph
በጉጂና ጌዴኦ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ እየተሰራ ነው
በጉጂና ጌዴኦ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ እየተሰራ ነው ቡሌ ሆራ መጋቢት 22/2011 በጉጂና ጌዴኦ በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ባህላዊ እርቅ ተካሂዶ በርካቶች ወደ ቀያቸው ተመልሰው ቀሪዎችን ለመመለስ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። በጉጂና ጌዴኦ መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካቶች መፈናቀላቸው ይታወሳል። ተፈናቃዮቹን መልሶ በማቋቋሙ ላይ የኦሮሚያና የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና…
ጥንቃቄ ይደረግ‼️
ከወለጋ #እንደተፈናቀሉ_በማስመሰል #በጅማ_ከተማ ህብረተሰቡን በማጭበርበር እርዳታ ሲያሰባስቡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደገለጸው ግለሰቦቹ ከወለጋ እንደተፈናቀሉና ቤታቸው ንብረታቸው እንደተወሰደ በመናገር በሀሰት ከህብረተሰቡ ለአምስት ቀን #እርዳታ ሲያሰባስቡ ቆይተዋል።
ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በግለሰቦቹ ላይ ባደረገው ክትትል የካቲት 22/ 2011ዓ.ም. በጅማ ቢሺሼ የገበያ ማዕከል እንደያዛቸው የመምሪያው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውጋቸው ተናግረዋል።
“በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ መሆኑ በተደረገባቸው ምርመራ ተረጋግጧል” ብለዋል።
በሃሰት ካሰባሰቡት ገንዘብ ውስጥ አንደኛው መኪናውን እንድታሰራለት 5 ሺህ 300 ብር ለባለቤቱ መላኩንና ሌላኛው ደግሞ 3 ሺ 23 ብር ለዘመዶቹ መላኩን በሰጡት የእምነት ቃል አረጋግጠዋል።
ከዚህ ገንዘብ በተጨማሪም ፖሊስ በግለሰቦቹ እጅ አራት ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ በኢግዚቢትነት መያዙንም አመልክተዋል።
በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎች እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ጽኑ እስራትና በ500 ብር እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
ግለሰቦች #ክስቸውን_እንዲከላከሉ እደሉ ቢሰጣቸውም #ባለመቻላቸው የቅጣት ውሳኔው ጸንቶባቸዋል፡፡
ምንጭ፦ ENA

ጥንቃቄ‼️
ፍፁም ከባህላችን ጋር አብሮ #የማይሄደው #አፕሪ_ዘ_ፉል በማለት አንዳድ ግለሰቦች ሰዎችን ሲሸወዱ ሀሰተኛ መረጃን ሲያሰራጩ እየተመለከትን ነው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ከእንዲህ አይነት #ያልተገባ ድርጊት ራሳችሁን አርቁ።

የአዲስ አበባ ችግር❓
"የውሸት ጭቅጭቅ ነው፡፡ ትክክለኛው የአዲስ አበባ ችግር ምንድነው ተብሎ የአዲስ አበባ ሕዝብ ቢጠየቅ፣ የአዲስ አበባ #ባለቤትነት ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖም አያውቅም፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ ጥያቄ በቂ ትራንስፖርት የለኝም፣ መኖሪያ ቤት የለኝም፣ ሕክምና ማግኘት አልቻልኩም፣ ልጄን ማስተማር አልቻልኩም፣ ወዘተ የሚሉ ናቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች #መፍታት ነው ያለብን፡፡ ይኼንን የሚያደርጉ ፖለቲከኞች መሰማት የሌለባቸው ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ ይኼን የሚገፋ መንግሥት ለእኔ መሰማት የሌለበት መንግሥት ነው፡፡ ሕዝቡ እኮ ዛሬ ከቤቱ ወጥቶ ሥራውን ሠርቶ ይኖራል፡፡ ይህ ከተማ የእኔ ነው የሚለው ጉዳይ ጭቅጭቅ ሆኖ አያውቅም፡፡ ስለዚህ የሕዝብ መንግሥት ነው ከተባለ፣ የሕዝብን ችግር ልፈታ ነው ካለ፣ መጀመርያ ችግሩን በትክክል ማወቅና መረዳት አለበት፡፡ ችግሩ የወሰንና የባለቤትነት ጉዳይ አይደለም፡፡" የአዲስ አበባና የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ #ክቡር_ገና የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ለሪፖርተር እንደተናገሩት--

የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች እንዳትቀሩ፦
ዶክተር #ታከለ በተገኙበት የመጀመሪያው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ #StopHateSpeech እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት #ይጠናቀቃል።
ቦታ፦ በፕሬዘዳንት ፅ/ቤት ህንፃ ፊት ለፊት
ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
በቀጣይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር #ታከለ በተገኙበት የመጀመሪያው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ #StopHateSpeech እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት #ይጠናቀቃል።
ቦታ፦ በፕሬዘዳንት ፅ/ቤት ህንፃ ፊት ለፊት
ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
በቀጣይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WSU የዛሬው እንግዳ ዶክተር ታከለ ናቸው! ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዓት ይከበር። #ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ
#StopHateSpeech
•ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
•ቦታው፦ ከፕሬዘዳንት ህንፃ ፊት ለፊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech
•ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
•ቦታው፦ ከፕሬዘዳንት ህንፃ ፊት ለፊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️
በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተፈጠረ ላለው ችግር ከወዲሁ መንግስቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው እና የችግሩን መንስኤ በማጣራት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ ተማሪዎች እየጠየቁ ናቸው። ውድ ተማሪዎችም ከተለያዩ አላስፈላጊ ድርጊቶች #ተቆጥባችሁ በጋራ ልትቆሙ ይገባል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱኝ አቀርባለሁ!

#update የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ውህደት ፈጽሟል መባሉን አስተባበለ። መኢአድ ዛሬ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ፓርቲው አገራዊ ለውጡን ተከትሎ እንደገና አደረጃጀቱን እያጠናከረ፣ አባላቱን እያሰባሰበና ቢሮ እየከፈተ ይገኛል። ይህ እየሆነ ባለበት ወቅት በመገናኛ ብዙሃን ‘መኢአድ ውህደት ፈጸመ’ መባሉ የማያውቀው ከመሆኑ ውጪ በድርጅቱ ላይ የተከፈተ ”አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችንን የመከፋፈልና የተነሳንለትን አገርንና ህዝብን ወደተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማሸጋገር ዓላማ የሚያደናቅፍ ነው” ብሏል። ውህደት ፈጸመ መባሉ ህገ-ወጥና ጸረ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ እንደሆነ በመግለጽ ድርጊቱን ኮንኗል።
Via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 8ተኛ ዓመት በዛሬው እለት የግድቡ ግንባታ እየተካሄደ ባለበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️
በሱሉልታ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በትንሹ #የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።
የትራፊክ አደጋውም በዛሬው እለት ከማለዳው 12 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ገደማ ላይ መድረሱን የሱሉልታ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የትራፊክ አደጋው የደረሰውም ከጫንጮ ከተማ ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ 88 ቁጥር አንበሳ የከተማ አውቶብስ ከአዲስ አበባ ወደ ጫንጮ ሲጓዝ ከነበረ ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መሆኑም ተነግሯል።
እስከአሁን ባለው መረጃ መሰረትም በትራፊክ አደጋው በትንሹ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሱሉልታ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የትራፊክ አደጋው በምን ምክንያት እንዳጋጠመ እየተጣራ መሆኑንም የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
Via FBC

በቅሎ ወለደች❓
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በጣርማበር ወረዳ በመዘዞ ንኡስ ወረዳ ኮሶበር ቀበሌ አንዲት በቅሎ መውለዷን የወረዳው መንግስት ኮምዩኒኬሺን ጉዳዮች ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
ፅ/ቤቱ እንዳስታወቀው የበቅሎዋ ባለቤት አቶ ሙላት ሃ/ሚካኤል በቅሎዋን በ2009 ዓ/ም በመግዛት ሲገለገሉባት እንደቆዩና ግቷ ሲጨምርም ህመም መስሏቸው እንደነበር ተናግረው መጋቢት 21/2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት አካባቢ መውለዷን ተናግረዋል፡፡
ሁኔታው አዲስ እንደሆነባቸው የገለጹት አቶ ሙላት የዚህ አይነቱ ክስተት ታይቶ እንደማይታወቅና በአሁኑ ሰዓት እናትና ልጅ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርድ ተከለሃይማኖት በበኩላቸው በቅሎዋ ቀደም ሲል የእርሳቸው እንደነበረችና እንደሸጧት ገልፀው ሁኔታው አዲስ መሆኑንና በቅሎ አትወልድም የሚባለውን የሚሽር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጫንጮ ወረዳ የእንስሳት ጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ግርማ ጅሬኛን ይህ ነገር እንደምን ሆነ ? ሲል በስልክ አነጋግሯል፡፡
አቶ ግርማ ጅሬኛ በሳይንሱ ይህ ክስተት ሊያጋጥም ይችላል የሚችል የሚል መላምት እንደሌለና በቅሎ ያላት ሃብለበራሂ /Chromosome/ ነጠላ በመሆኑ መውለድ የምትችልበት አጋጣሚ የለም፤ ይህ ለሳይንሱም አዲስ ክስተት ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ በፊትም በግንቦት ወር 2009 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ ማርጢቆስ ቀበሌ አንዲት በቅሎ ፈረስ መውለዷ የሚታወስ ነው፡፡
Via EPA