TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#StopHateSpeech🔝

የመጀመሪያው ምሽት የStopHateSpeech እቅስቃሴ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በተገኙበት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። በዝግጅቱ ላይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት #ፕሬዘዳንት ወጣት #ዘገየ ተገኝቶ መልዕክቱን አስተላልፏል። ወጣት ዘገየ ባስተላለፈው መልዕክት ሁላችንም ራሳችንን ከጥላቻ ንግግሮች በማራቅ ለሀገራችን #ሰላም እና #እድገት በጋራ እንስራ ሲል ጥሪ አቅርቧል። ወጣቶች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸውን ለመልካም እና ለበጎ ነገር በማዋል ለሀገራቸው ሰላም ዘብ እንዲቆሙ፤ ከልዩነት ይልቅ ለአንድነት ትልቅ ቦታ እዲሰጡ ጠይቋል።

ምሽቱ በተቋሙ የኪነ ጥበብ ማህበር (ትሩ ላይፍ) ደምቆ አልፏል። #true_Life(WSU)

ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ የ2ኛው ቀን ዝግጅት ይቀጥላል በዛሬው ዝግጅት ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ይገኛሉ።

በቀጣይ፦

አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech
#TIKVAH_ETH

ፎቶ፦ @odansiif (ዱሬሳ-TIKVAH-ETH)

የሀሳቡ ደጋፊዎች፦ 0919 74 36 30
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#tikvah_eth መምጣት ትችላላችሁ!
Day 2

#የወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደተዘጋጀው መድረክ መምጣት ትችላላችሁ። #StopHateSpeech

ቦታው፦ የፕሬዘዳንት ፅ/ቤት ህንፃ
ሰዓት - ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ

ኑ የጥላቻ ንግግርን እናውግዝ!

ልዩ የኪነ ጥበብ ድግስ!
ከበርካታ የሞባይል ካርድ ሽልማቶች ጋር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

ለአዲስ አበባ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተመሠረተው የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ባደረገው ጥረት እስከ አሁን 3147 የጎዳና ላይ ነዋሪዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል 701 ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ቀሪዎቹን ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በእስከ አሁን የማገገሚያ ቆይታቸው የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እና የስነ-ልቦና ትምህርቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡

ለዚህ ስራ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የተገኙት ኢ/ር #ታከለ_ኡማ እስከአሁን ማገገሚያ የገቡትን ስራ የማስጀመርና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቅርቡም ተጨማሪ የጎዳና ላይ ልጆችን የማንሳትና ወደ ማገገሚያ ማዕከል የማስገባት ስራው እንደሚካሄድም ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ለማህበራዊ ትረስት ፈንዱ በዋናነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ህብረተሰቡን እና ተቋማትን በማስተባበር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ...

ካፋ፤ ሸካ እና ቤንች ማጂ ዞኖች ከመጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር በሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚተዳደሩ የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በውሳኔው መሠረት የመከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ አካባቢዎቹን ይቆጣጠራል። የአካባቢው ጸጥታ ከተናጋ 8 ወራት ቢቆጠሩም ችግሮች መፍትሔ እንዳልተበጀላቸው የቤንች ማጂ ዞን የኮምዩንኬሽን ቢሮ ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል።

የደቡብ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ተቀዳሚ የቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ "እንደ ሀገር በፈጣን ዕድገትና ልማት ውስጥ ብንገኝም ለውጡ ከተጀመረ ጊዜ ወዲህ በርካታ ተስፋዎችና ተግዳሮቶችን እያስተናገድን እንገኛለን። እንደ ክልል ባለፉት 8 ወራት በበርካታ ዞኖችና ወረዳዎች በሠላም እጦት የተነሣ ዜጎች ሀብት ንብረታቸው የወደመበት ፣ ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበትና በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ችግር ውስጥ የገቡበት ወራቶችን አሳልፈናል" ሲሉ ተናግረዋል።

በቤንች ማጂ፣ ሸካና በከፊል ካፋ ዞን ያለው የፀጥታ ሁኔታ የመከላከያ፣ የፌደራልና ልዩ ሀይል አካላት ለማረጋጋት ሞረው አልተሳካላቸውም ተብሏል። አሁንም በአካባቢው ውጥረት ያለ ሲሆን የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው አልተመለሱም።

የቤንች ማጂ ዞን የኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያሰራጨው መግለጫ "በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል መብራህቶም ሀይሉ የአንድ ወር ጊዜያዊ የሠላምና ጸጥታ ኮሚቴውን ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ዕቅዱ በዋናነት በቀጠናው የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የህብረተሠቡ መፈናቀል፣ ግጭትና ስቃይ እንዲቆምና አጥፊዎች በጥፋታቸው ልክ የሚቀጡበትን ሁኔታ መፍጠር ነው ብለዋል። በዕቅዱ መሠረት በቤንች ማጂ ዞን ማጂ ፣ ሱርማ ፣ ቤሮ ፣ ጉራፈርዳ ወረዳዎችና እንዲሁም በሸኮ ቴፒና የኪ ወረደ ከደቡብ ሱዳን ከሚያገናኝ ድንበር የድንበር ጥበቃ ከሚያደርጉ ውጭ ማንኛውም ግለሰብ ስለታማ ነገር፣ የጦር መሣሪያና ትጥቅ መንቀሳቀስ አይፈቀድም " ማለታቸውን አትቷል።

Via እሸት በቀለ(ጀርመን ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech🔝

TIKVAH-ETH ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር #በመተባበር እያደረገ የሚገኘው የStop Hate Speech እንቅስቃሴ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት #የሁለተኛው_ቀን መድረክ ተካሂዷል። በዛሬው እለት ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች መካለል አቶ #እሸቱ ተገኝተው መልዕክት አተላልፈዋል። አቶ እሸቱ እንደተናጋሩት ተማሪዎች ከየትኛውም አይነት #የጥላቻ_ንግግር እና አንደንዛዥ አስተሳሰቦች #ሊርቁ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን ላይክ እና ሼር ባለማድረግ ለሀገራቸው #ሰላም ዘብ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፤ ከዚህ ባለፈም ስለግቢያቸው #ሀሰተኛ መረጃ ሲሳራጭ #ሲመለከቱም እውነታውን መፃፍና እውነቱን ብቻ ማጋራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። አቶ እሸቱ ከወራት በፊት በግቢው በተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ የተፈጠረውን ክስተት አንስተው ተማሪው እውነቱን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

•በዛሬው ምሽት ቆይታ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በአካል ተገናኝተው አጭር ቆይታ አድርገዋል፤ በርካታ ስራዎችን በቀጣይ ለመስራትም አጭር ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም TIKVAH-ETH በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንደ ማህበር የሚቋቋምበት መንገዶች ላይ በቀጣይ ሰፊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

ምሽቱ ልክ እንደትላንቱ #በትሩ_ላይፍ የኪነ ጥበብ ቡድን ታጅቦ አልፏል። #TrueLife

በነገው ዕለት የ3ኛውና የመጨረሻው ቀን መድረክ የሚኖር ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፋሉ።

በቀጣይ፦

አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech
#TIKVAH_ETH

ፎቶ፦ @odansiif (ዱሬሳ-TIKVAH-ETH)

የሀሳቡ ደጋፊዎች፦ 0919 74 36 30

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቻይና ከተማ የሆነችው ሻንጋይ የ5ጂ የቴሌኮም ኔትወርክ አገልግሎት በመስጠት በአለም #ቀዳሚ መሆኗን አስታወቀች፡፡ ከተማዋ ይህን አዲስ የቴሌኮም ቴክኖሎጂ ይፋ ያደረገችው በሙከራ ደረጃ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም ሂደት ኔትወርኩ ከተማውን ሙሉ ለሙሉ እንዲሸፍን ለማድረግ ባለፉት ሶስት ወራት ቴክኖሎጂውን መሸከም የሚችሉ ጣቢያዎች መተከላቸውን ተነግሯል። ይህም አዲስ መሰረተ ልማት ቻይና አሜሪካንና ሌሎች ሀገሮችን በመቅደም ቀጣዮ ትውልድ የሞባይል ኮሙኒኬሽን ለመፍጠር ምቹ ሁኔታ እንደሚያመቻች ተመልክቷል፡፡ ቀጣዮ ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ እንደሆነ የሚነገርለት የ5ጂ የቴሌኮም ኔትወርክ ከ4ጂ ቴክኖሎጂ ይልቅ መረጃዎችን ከኢንተርኔት ከ10 እስከ 100 እጥፍ በሆነ ፍጥነት የማውረድ አቅም አለው፡፡

ምንጭ፦ቢዝነስ ስታንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia