የምክር ቤት አባላቱ አደጋ ደረሰባቸው‼️
#የፓርላማ_አባላትን ጭኖ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ በነበረ መኪና ላይ በደረሰ የግጭት አደጋ፣ በፓርላማ አባላትና በጽሕፈት ቤትሠራተኞች ላይ ጉዳት ደረሰ።
የፓርላማ አባላት ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የተፈናቀሉ ዜጎችያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ አማራ ክልል ጉዞ እያደረጉእንደነበር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ከወጡ በኋላም አደጋውእንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል። በደረሰው አደጋ የሞተ የፓርላማአባልም ሆነ የጽሕፈት ቤት ሠራተኛ ባይኖርም፣ ከባድ የአካል ጉዳትየደረሰባቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸውመሆኑን ለማወቅ ተችሏ።
የፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ጉዳት የደረሰባቸውንየፓርላማው አባላት ሁኔታ ለመከታተል በጠዋት ጥቁር አንበሳሆስፒታል ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የዛሬው የፓርላማው ስብሰባምበዚሁ ምክንያት ዘግይቶ ነበር የተጀመረው። አፈ ጉባዔ ታገሰስብሰባውን ባስጀመሩበት ወቅት አደጋው የደረሰባቸው አባላትበደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።
Via ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጣና ፎረም የቦርድ አባል ሆነው መመረጣቸውን ፎረሙ በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡ ከአዲሶቹ 6 ተመራጮች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ደዔታ ኂሩት ዘመነ እና የኢንፎርሜሽን ኔትወርክ ኤጀንሲ (ኢንሳ) ዳሬክተር እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ተመስገን ጥሩነህ ይገኙበታል፡፡ ተመራጮቹ በተሰማሩበት መስክ ልዩ የአመራር ብቃት በማሳየታቸው የተመረጡ ሲሆን ለ3 ዐመታት ያገለግላሉ፡፡ ቦርዱ 11 ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ነው፡፡ ፎረሙ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አነሳሽነት የተቋቋመ የምክክር መድረክ ሲሆን በየዐመቱ የተወሰኑ የሀገራት መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ምሁራን እና ከፍተኛ የጸጥታ ዘርፍ ባለሙያዎች በባሕር ዳር ከተማ እየተገናኙ በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
• አዲስ አበባ የሁሉምናት እንጂ የአንዱ ብቻናት የሚለው ትክክል አይደለም።
• በህገመንግስቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል፤ የሚለውን ሀሳብ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው።
• ኢህአዲግ የቀድሞ ጥምረቱ አለ፤ ብዙዎች የተለያየን የሚመስላቸው የልዩነት ሀሳቦች ሲኖሩ አራቱ ፓርቲዎች በውስጣዊ ውይይት ብቻ ይገድቡት የነበረው ሂደት ቀርቶ ፓርቲዎቹ የልዩነት አቋማቸውን በአደባባይ መግለፃቸው ነው ጥምረቱ የሌለ የሚያስመስለው።
• ይህ አካሄድ ወደፊትም ይቀጥላል ሆኖም ተግባራዊ የሚሆነው በጋራ የወሰነው ሀሳብ ነው
• ይበልጥ ወደ አንድ ለመወሃድ የጀመርነው ሂደትም ይቀጥላል።
• የፌደራል መንግስት ተዳክሟል ለማለት መለኪያው መሆን ያለበት ሀገር ስትወረር መመከት ሲያቅተው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በብቃት መመከት አልችል ሲል ነው።
አሁን ግን በዚህ መልኩ የሚገለፅ አንዳችም ተግዳሮት አልገጠመንም በክልሎች የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ጣልቃ የማንገባው ክልሎች በራሳቸው መፍታት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው።
• ከኤርትራ ጋር ያደረግነው ስምምነት መሰረት ያደረገው ሰላምን ነው፤ በቀጣይ ኢኮኖሚ: ንግድ እና መሰል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት በሂደት ላይ ነን፤ ስለዚህ ከህዝብ የተደበቀ ሌላ ስምምነት የለንም፡፡
• ዲያስፖራው አሁንም ሀገሩን ለመደገፍ የጀመረውን መንገድ ሊገፋበት ይገባል፤ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ በሚወጡ መረጃዎች ተስፋ የመቁረጥ ነገር ይታያል ይህ ተገቢ አይደለም ሁሉም ነገር ቀድሞ በተግባባንበት መልኩ እየተተገበረ ነው፤ ስለሆን ወደ ኋላ ማለት አይገባም
• በኮዬ ፌጬ የኮንደሚኒዮም ግንባታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ወሰን ያለው ውዝግብ ተፈቶ ለኮንዶሚኒዮም ባለእድለኞች ቤቶቹ እንዲተላለፉ እየተሰራ ነው
• በኦዲፒና በአዴፓ እንዲሁም በኦዲፒ በራሱ ውስጥ አንድነት እንጂ ምንም አይነት የተለየ ልዮነቶች የለም ነግር ግን በመካከላቸው የልዮነት ሀሳብ ይኖራሉ እነሱንም በመነጋገር እየፈታን ነው
• ከለውጡ በሃላ ኢኮኖሚው በሚፈለገው ደረጃ ውጤቶች ያልታየው ኢኮኖሚው ችግር ውስጥ ሆኖ ስለተቀበልነው እሱን የማስተካከል ስራ እየተሰራ ቆይተናል፡፡ በዚህም በርካታ ሀገራት ድጋፍ ስላደረጉ ውጤት ማግኘት ተችሏል፡፡
• አሁን ላይ ኢኮኖሚው ከታመመበት ሁኔታ ላይ ወጥቶ ጤናማ ሆኗል፡፡
• የአማራና የትግራይ ክልል ውጥረት በቀጣይ በእርግጠኝነት የሚረግብና ወደ ሰላም የሚመለስ ነው፡፡ ሁሉቱም ወገን በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ያመጣውን ኪሳራ ስለሚያውቁ መካከላቸው ያለው ልዮነት በሰላም ይፈታሉ፡፡
Via etv

"በኮዬ ፌጬ የኮንደሚኒዮም ግንባታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ወሰን ያለው ውዝግብ ተፈቶ ለኮንዶሚኒዮም #ባለእድለኞች ቤቶቹ እንዲተላለፉ እየተሰራ ነው።" ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
'MINDSET'🔝
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ስርጸት ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት እና በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ዙሪያ ተወዳዳሪ ብሎም ተመራጭ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ አስተሳሰብ ላይ የተመረኮዘ ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው ማህብሰብ መሰጠቱን ገለፀ፡፡
ስልጠናውን ከሀገረ ደቡብ ኮሪያ ተጋብዘው የመጡ አለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ደቡብ ኮሪያውያን ፕሮፌሰሮች መስጠታቸው ነው የተገለፀው፡፡
ስልጠናው #አስተሳሳብ ላይ የተመሰረተ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ በስልጠናው የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳዳር እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
ደቡብ ኮሪያ እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትገኝ የነበረች እና ዜጎቿም ዝቅተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው ነበሩ፣ ነገር ግን ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ዛሬ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን ስልጠናውን እየሰጡት ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ተናግረዋል፡፡
ዛሬ ላይ ደቡብ ኮሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንደስትሪ ግንባታ በመጀመሪያው ተርታ ተሰልፋ ትገኛለች፤ይህ የሆነው ታዲያደቡብ ኮሪያውን ለቀጣዩ ትውልድ እንስራ፣ሳንበገር ተሃምር መፍጠር እንችላለን ብለው እጅ ለእጅ ተያይዘው በቁርጠኝነት በመስራታቸው የመጣ ለውጥ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ጠቁመዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከድህነት ተላቀን ለቀጣዩ ትውልድ #የተሸለች ሀገር ለማውረስ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት ለመሆን በጋራ እንረባረብ ሲል #መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

Alert‼️
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል፤ ቃጠሎውም #እየተባባሰ እንደሆነ ነው የተሰማው። ከደባርቅ ከተማ ወጣቶች ተሰብስበው ወደ ፓርኩ ሄደው #ለማጥፋት ቢፈልጉም ተሽከርካሪ ማግኘት አለመቻላቸውን ለአብመድ ተናግረዋል።
እሳቱ #ሳንቃ_በር አካባቢም መከሰቱን ወጣቶቹ ተናግረዋል የደባርቅ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የወጣቶችን #ጥቆማ ተጋርቷል።
ከፓርከ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መካከል አቶ #ታደሰ_ይግዛው እሳቱ እሜት ጎጎ እና ሳንቃበር አካባቢ #መባባሱን ገልጸው ወደ ቦታው ለማቅናት ተሽከርካሪ እያፈላለጉ መሆኑን ገልጸዋል። ጊዜው #በመምሸቱ ስልክ የሚያነሳላቸው ሰው ማጣታቸውንም ተናግረዋል። ከዞንና ክልል የሥራ ኃላፊዎች መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ሲል አብመድ ዘግቧል።

አያቶች ነን!!
ብዙኀንን የቤት ባለቤት ያደረገው። አያት አ.ማ ዛሬም በተለዩ አማራጮች የደንበኞችን እንደፍላጎታቸውና እንዳቅማቸው የሚስተናገዱበት ሁኔታ አመቻችጥቷል። 🍭 የዴቤ አማራጭ፦ (20 በ 80 እና 30 በ 70 በዶላር ለሚከፍል) በብር ለሚከፍል (75 በ 25) 🍭ቅድመ-ክፍያ ፦ 8% ድረስ ዝቅ ብሏል ለአጭር ጊዜ የሚቆይ። 🍭የካሬ ዋጋ፦ በሙሉ ግንባታ 25,047 ብር በካሬ በከፊልግንባታ 21,758 ብር በካሬ 🍭 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911992486 / 0969438539

‹‹አዲስ አበባ የሁላችን ናት›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)
.
.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲስ አበባ ‹‹የእኛ ናት›› የሚል ክርክር በስፋት እንደሚነሳ በማውሳት ለተጠየቁት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ‹‹አዲስ አበባ የሁላችን ናት፤›› በማለት የመለሱ ሲሆን፣ ‹‹በመሠረቱ አዲስ አበባ የማን ናት የሚል ጥያቄ በእኛ ደረጃ አንስቶ መወያየት አሳፋሪ ነው፤›› ሲሉም አስታውቀዋል፡፡
‹‹አዲስ አበባ የማን ናት፣ የማን አይደለችም እያሉ የሚከራከሩ ሰዎች ከጭንቅላታቸው ጀርባ ምን አስቀምጠው ነው የሚነጋገሩት የሚለውን በራሳቸው አውድ መመልከት ያስፈልጋል፤ ምን ታስቦ ነው የማናት የሚባለው?›› በማለት፣ ‹‹አዲስ አበባ የእኔ ናት ስል የአንተ አይደለችም ማለት ከሆነ ስቼያለሁ፡፡ የእኔ ሆና የአንተ እንዳሆነች የምናገር ከሆነ ስህተት ነው፡፡ አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡
በታሪክ የፌዴራል ሥርዓቱ ሲዋቀር አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል አካል የማድረግ ፍላጎት እንደነበረ ገልጸው፣ ነገር ግን ባጠራት ክልል ውስጥ ባላት ግንኙነት የተነሳ ክልሉ ልዩ ጥቅም ማግኘት አለበት የሚል በሕገ መንግሥቱ ተቀምጧል በማለት ያብራሩ ሲሆን፣ ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሁን ባለበት አቅጣጫ በትክክለኛ መንገድ እንዳይሄድ ባልባሌ ጉዳይ ጊዜ እንድናባክን የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው ይህንን ሐሳብ የሚያንሸራሽሩት፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ለአዲስ አበባ ሰዎች ይኼ አጀንዳ ሊሆን አይችልም፡፡››
‹‹አዲስ አበባ የእኛ ናት ስንል መነሻችን ምንድነው?›› በማለት የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የዛሬ 20 ዓመት በአዲስ አበባ የአሁኑን ያክል ሰው እንዳልነበረ፣ ብሎም ባለፉት 20 ዓመታት ይኼንን ያክል ሰው በአዲስ አበባ እንዳልተወለደ በመጥቀስ፣ አዲስ አበባ ከፍቶትም ሆነ ተደስቶ የመጣውን ኢትዮጵያዊና የውጭ አገር ዜጎች አቅፋና ተሸክማ ኖራለች ብለዋል፡፡ ነገር ግን ‹‹በሚያሳዝን ሁኔታ በኩራዝ የሚኖሩ ዜጎች ያሉባት ከተማ ስለሆነች ይህችን ከተማ እንዴት እንቀይራት ነው የእኛ ጉዳይ መሆን ያለበት፤›› ሲሉም አስምረዋል፡፡
ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ያላት ልዩ ጥቅም ሕገ መንግሥታዊ በመሆኑ፣ እንዴት ይተግበር የሚለው ላይ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል አስተዳደሮች በጋራ መምከር አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በተያያዘም ለአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ማስዋብ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘጋጅነት በሰሀን አምስት ሚሊዮን ብር የሚሸጠው እራት በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚካሄድ በማመላከት፣ ለእራት የሚታደሙ ሰዎች እንደ ስጦታ ሳይሆን በረዥም ጊዜ ውጤቱ የሚታይ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ እንደሆነ በመረዳት ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዚህ ፕሮጀክት ለመሳተፍና ለመደገፍ ኬንያ፣ ግብፅ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲና ሌሎች አገሮች ፍላጎት እንዳሳዩ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ቻይና የፕሮጀክቱን መነሻ በሸራተን ሆቴል ፊት ለፊት ላለው 12.5 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ማልሚያ የዲዛይንና የትግበራ እገዛ ማድረጓን አስታውቀቃል፡፡ ይህ ስፍራ በአንድ ጊዜ ከ100 ሺሕ በላይ ሰዎችን መያዝ የሚችል ስፍራ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቱ አካልና በአንድ ጊዜ 20 ሺሕ ሰዎችን መያዝ የሚችል ቤተ መጻሕፍት እንደሚገነባም ጠቁመዋል፡፡

"አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፡፡… አዲስ አበባ ለዘመናት ከፍቶት የመጣን ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጇን ዘርግታ ትቀበል ነበር፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የጎረቤት ሀገር ዜጎችንም እንደዛው፡፡ ሁሉንም አቅፋ የምትኖር ከተማ ናት፡፡ ስለዚህ እቺ ከተማ የእከሌ የእከሌ ሳትሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት፡፡" ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትላንት ምሽት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ቁጥጥር ስር ውሏል። ትናንት ምሽት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ጌትነት ይግዛው በተለይ ለኢቢሲ እንደገለፁት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስዔ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ምሽት በመሆኑ ቃጠሎውን የፈጸሙ ግለሰቦችን ለጊዜውም ቢሆን ቁጥጥር ስር ማዋል እንዳልተቻለ አቶ ጌትነት ተናግረዋል፡፡በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ባለፈው አመትም በከፍተኛ ደረጃ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበርና ይህንን ችግር በቋሚነት ለመፍታት መስሪያ ቤታቸው እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል።
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopi
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopi
ሞህ ፋራህ ...ተዘረፍኩኝ አለ!
እንግሊዛዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ሞህ ፋራህ ልምምድ ለማድረግ ባረፈበት ያያ አፍሪቃ የአትሌቲክስ መንደር መዘረፉን አስታወቀ። ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ የሚገኘው ያያ አፍሪቃ የአትሌት ሀይሌ ገብረስላሴና (ሸሪኮቹ) ንብረት የሆነ የአትሌቲክስ መንደር ነው።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንግሊዛዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ሞህ ፋራህ ልምምድ ለማድረግ ባረፈበት ያያ አፍሪቃ የአትሌቲክስ መንደር መዘረፉን አስታወቀ። ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ የሚገኘው ያያ አፍሪቃ የአትሌት ሀይሌ ገብረስላሴና (ሸሪኮቹ) ንብረት የሆነ የአትሌቲክስ መንደር ነው።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያያ ቪሌጅ ሪዞርት ማናጀር ዛሬ ጠዋት በስልክ በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ የሚከተለውን ብለዋል፦
"ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አምስት የሪዞርቱ ሰራተኞች በጥርጣሬ ተይዘዋል። እነዚህ በወቅቱ የሆቴል ክፍሎችን ቁልፎች ይዘው የነበሩ ናቸው። አሻራ እና ቃል ሰጥተዋል። ምን ያህል ብር እንዲሁም ምን አይነት የእጅ ሰአት እንደተሰረቀበት አላወቅኩም። ሆቴሉ ካሜራ የለውም ስለዚህ ሰራተኞቹ በጥርጣሬ ነው የተያዙት። ሞ ፋራህ አሁንም በሪዞርቱ ይገኛል። ነገር ግን ፌስቡክ ላይ እንደፃፈው ሳይሆን እኛ በጣም ተባብረነዋል። ሶስት እና አራት ግዜ በየቀኑ ፖሊስ ጣብያ እኔ እራሴ እየተመላለስኩ ነበር። የምርመራው ውጤት እስኪያልቅ ትብብራችንን እንቀጥላለን።"

የሀዋሳ ድምፅ FM 97.7‼️
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ በ‹‹ ትራንስሚተር ›› #ብልሽት ምክንያት #አስር_ወራትን ያለ ሥርጭት ማሳለፉን የዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ #አርማዬ_አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ በ‹‹ ትራንስሚተር ›› ብልሽት ምክንያት ለአስር ወራት ያህል አገልግሎት እንዳልሰጠና መረጃዎችን በተገቢው ለማኅበረሰቡ ማድረስ ባለመቻሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል፡፡ ጣቢያው ለረጅም ወራት አገልግሎት እንዳይሰጥ የተደረገውም የመሣሪያ ግዥ ሂደቱ ሰፊ ጊዜን በመውሰዱ ምክንያት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፤ መሣሪያው ብልሽት በደረሰበት ወቅት በባለሙያዎች ተመርምሮ ሲጣራ መቀየር እንዳለበት ታምኗል፡፡ ማሣሪያውን ለመቀየር ዩኒቨርሲቲው ቀጥታ ግዥ ማድረግ ስለማይችል ሦስት ጊዜ ጨረታ ቢወጣም ብቸኛ የጨረታ አቅራቢ አንድ ሰው ብቻ ስለነበር እንዳይካሄድ ተደርጓል፡፡ በዚህም የግዥው ሂደት ጊዜ በመውሰዱ ጣቢያው ለረጅም ወራት አገልግሎት እንዲያቆም ተገልጿል፡፡
የማኅበረሰብ ራዲዮ ጣቢያው ያለ ሥርጭት መቆየቱ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ያሉት ወይዘሮ አርማዬ፤ ጣቢያው ሲቋቋም ዩኒቨርሲቲው እየሠራ ያለውን ጥናትና ምርምር እንዲሁም መሠረታዊ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ለማድረስና ራሱን የሚያስተዋውቅበት መድረክ እንደመሆኑ አገልግሎት አለመስጠቱ መረጃዎችን በተገቢው ለማኅበረሰቡ ማድረስ ባለመቻሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም ተናግረዋል፡፡
የማኅበረሰብ ራዲዮ ጣቢያው ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ለጥናትና ምርምር፣ ለማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ለመማርና ማስተማር ሥራዎች ድጋፍ ስለሚያደርግ ትኩረት ተሰጥቶት መሣሪያው መገዛት እንዳለበት ታምኖ ለግዥ ኤጀንሲ ደብዳቤ በመጻፍ በውስጥ ጨረታ እንዲገዛ ፈቃድ መሰጠቱን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም አቅራቢ ድርጅቱ ውል መፈፀሙንና በቅርብ ቀናት ውስጥ ማሣሪያው ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደሚገባ፤ ለግዥውም ሦስት ሚሊዮን ብር ወጭ መደረጉን፤ የሥርጭት አገለግሎቱም በቅርቡ እንደሚጀመር ተናግረው፤ ከመሣሪያ ግዥው በተጨማሪ በቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ገብረጊዮርጊስ አብርሐ በበኩላቸው፤ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማኅበረሰብ ራዲዮን በሚመለከት በ‹‹ ትራንስሚተር ›› ብልሽት ምክንያት አስር ወራትን ከአገልግሎት ውጭ መሆኑ በብሮድካስት ባለሥልጣኑ በኩል እንደሚታወቅ ገልፀዋል፡፡
የጥገናና ተከላው ሥራ የባለ ሥልጣኑ ድርሻ አለመሆኑንና፤ ነገር ግን የራዲዮ ጣቢያዎች እንዲህ ዓይነት እክል ሲያጋጥማቸው በውስጥ ሙያተኞች የሚስተካል ከሆነ ሥራውን ማከናወን የሚችሉ ባለሙያዎች እገዛ እንዲያደርጉላቸው፤ በሌላ መልኩ ሥራው በአገር ውስጥ ባለሙያዎች ብቻ የማያልቅ ከሆነ በተለይም መሣሪያዎች በጨረታ የሚገዙ ከሆነ ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ምክር እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድም ባለሥልጣኑ ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተኮር ራዮ ጣቢያ ድጋፍ ማድረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
‹‹የአየር ሰዓት እንኳን አስር ወር ይቅርና አስር ሴኮንድም ቀላል አይደለም›› ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለመደ ሥርጭትና ህዝባዊ አገልግሎት ያለው ሚዲያ ከአገልግሎት ውጭ ሲሆን ተጽዕኖው ቀላል አለመሆኑን ጠቁመው፤ ህዝቡ የመረጃ ባለቤት መሆን እንዳለበትና የተቋቋመውን ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ ምንም እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ በበላይነት የያዘው ቢሆንም፤ አገልግሎቱ የህዝብን የመረጃ ማግኘት ባለቤትነት ማረጋጋጥ ጉዳይ ስለሆነ፤ ፈልገው ያደረጉት ባይሆንም ይህን ያህል ጊዜ አገልግሎት አለመስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ አመላክተዋል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን