TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update 6 ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ሀገራዊ ፓርቲ ለመቋቋም እየሰራን ነው ብለዋል ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ፡፡ ድርጅቶቹ አርበኞች ግንቦት 7፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ሰማያዊ፣ የጋምቤላ ክልላዊ ንቅነቄና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መሆናቸውን ኢዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ የሚቋቋመው ፓርቲ ለማኅበራዊ ፍትህ የሚታገል፣ የዜግነት ፖለቲካን መሠረት ያደረገ እንደሚሆንም ተገልጧል፡፡ ውህደቱን እውን ለማድረግም የተለያዩ ግብረ ሃይሎች ተቋቁመዋል፡፡ ፓርቲው በመጭው ግንቦት 1 በይፋ እንደሚመሠረት ይጠበቃል፡፡

Via አዲስ ስታንዳርድ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ መጋቢት 19 ቀን 2011 ከአገር ውስጥና ከውጭ #ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሾች👆

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update #ፍትህ_ለመአዛ

"...ተጠርጣሪው አምልጧል!.."
የተበዳይዋ የመአዛ እህት ደወለችልኝ።

''ተስፋ እባክህን የምትችለውን አርግልን... ተጠርጣሪው አምልጧል። የቤቷን የልጆቿን አድራሻ ያውቃል። 'የህግ ያለህ' ብለህ ጩህልን። "

ከዚ በላይ መቀጠል አልቻለችም።

መአዛ በህክምና ላይ ሆና ስትሰቃይ ቤተሰቦቿ የህጉን ሂደት መከታተል አልቻሉም። ፖሊስም 'እየተጣራ ነው' ከማለት ውጭ ምንም መረጃ አልሰጣቸውም።

በመሀል የት ሆኖ እንደደወለ ባይታወቅም ደውሎ ' መአዛ ደህና ናት ብላችሁ አስፈቱኝ' ብሏል።

እህትየው ዛሬ ለመርማሪው ስትደውልለት ስልክ አያነሣም። በሌላ ሰው ሲደወልለት ደግሞ 'ሀኪም ቤት ስንወስደው አምልጦናል' ብሏል።

ምን አቅም አለኝ? ምን ላርግላት?
ማድረግ የምችለው ጩኸታቸውን መጮህ ነው።

እባካችሁን አጋሩልኝ
ለመረጃ 0924410897

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በሀላባ ቁሊቶ በሚገኘው #ፖስታ_ቤት #የእሳት_አደጋ መድረሱን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የአደጋው ምክንያት ባይታወቅም እሳቱን #ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላቱ አደጋ ደረሰባቸው‼️

#የፓርላማ_አባላትን ጭኖ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ በነበረ መኪና ላይ በደረሰ የግጭት አደጋ፣ በፓርላማ አባላትና በጽሕፈት ቤትሠራተኞች ላይ ጉዳት ደረሰ።

የፓርላማ አባላት ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የተፈናቀሉ ዜጎችያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ አማራ ክልል ጉዞ እያደረጉእንደነበር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ከወጡ በኋላም አደጋውእንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል። በደረሰው አደጋ የሞተ የፓርላማአባልም ሆነ የጽሕፈት ቤት ሠራተኛ ባይኖርም፣ ከባድ የአካል ጉዳትየደረሰባቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸውመሆኑን ለማወቅ ተችሏ።

የፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ጉዳት የደረሰባቸውንየፓርላማው አባላት ሁኔታ ለመከታተል በጠዋት ጥቁር አንበሳሆስፒታል ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የዛሬው የፓርላማው ስብሰባምበዚሁ ምክንያት ዘግይቶ ነበር የተጀመረው። አፈ ጉባዔ ታገሰስብሰባውን ባስጀመሩበት ወቅት አደጋው የደረሰባቸው አባላትበደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

Via ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጣና ፎረም የቦርድ አባል ሆነው መመረጣቸውን ፎረሙ በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡ ከአዲሶቹ 6 ተመራጮች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ደዔታ ኂሩት ዘመነ እና የኢንፎርሜሽን ኔትወርክ ኤጀንሲ (ኢንሳ) ዳሬክተር እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ተመስገን ጥሩነህ ይገኙበታል፡፡ ተመራጮቹ በተሰማሩበት መስክ ልዩ የአመራር ብቃት በማሳየታቸው የተመረጡ ሲሆን ለ3 ዐመታት ያገለግላሉ፡፡ ቦርዱ 11 ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ነው፡፡ ፎረሙ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አነሳሽነት የተቋቋመ የምክክር መድረክ ሲሆን በየዐመቱ የተወሰኑ የሀገራት መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ምሁራን እና ከፍተኛ የጸጥታ ዘርፍ ባለሙያዎች በባሕር ዳር ከተማ እየተገናኙ በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

• አዲስ አበባ የሁሉምናት እንጂ የአንዱ ብቻናት የሚለው ትክክል አይደለም።

• በህገመንግስቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል፤ የሚለውን ሀሳብ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው።

• ኢህአዲግ የቀድሞ ጥምረቱ አለ፤ ብዙዎች የተለያየን የሚመስላቸው የልዩነት ሀሳቦች ሲኖሩ አራቱ ፓርቲዎች በውስጣዊ ውይይት ብቻ ይገድቡት የነበረው ሂደት ቀርቶ ፓርቲዎቹ የልዩነት አቋማቸውን በአደባባይ መግለፃቸው ነው ጥምረቱ የሌለ የሚያስመስለው።

• ይህ አካሄድ ወደፊትም ይቀጥላል ሆኖም ተግባራዊ የሚሆነው በጋራ የወሰነው ሀሳብ ነው

• ይበልጥ ወደ አንድ ለመወሃድ የጀመርነው ሂደትም ይቀጥላል።

• የፌደራል መንግስት ተዳክሟል ለማለት መለኪያው መሆን ያለበት ሀገር ስትወረር መመከት ሲያቅተው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በብቃት መመከት አልችል ሲል ነው።

አሁን ግን በዚህ መልኩ የሚገለፅ አንዳችም ተግዳሮት አልገጠመንም በክልሎች የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ጣልቃ የማንገባው ክልሎች በራሳቸው መፍታት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው።

• ከኤርትራ ጋር ያደረግነው ስምምነት መሰረት ያደረገው ሰላምን ነው፤ በቀጣይ ኢኮኖሚ: ንግድ እና መሰል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት በሂደት ላይ ነን፤ ስለዚህ ከህዝብ የተደበቀ ሌላ ስምምነት የለንም፡፡

• ዲያስፖራው አሁንም ሀገሩን ለመደገፍ የጀመረውን መንገድ ሊገፋበት ይገባል፤ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ በሚወጡ መረጃዎች ተስፋ የመቁረጥ ነገር ይታያል ይህ ተገቢ አይደለም ሁሉም ነገር ቀድሞ በተግባባንበት መልኩ እየተተገበረ ነው፤ ስለሆን ወደ ኋላ ማለት አይገባም

• በኮዬ ፌጬ የኮንደሚኒዮም ግንባታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ወሰን ያለው ውዝግብ ተፈቶ ለኮንዶሚኒዮም ባለእድለኞች ቤቶቹ እንዲተላለፉ እየተሰራ ነው

• በኦዲፒና በአዴፓ እንዲሁም በኦዲፒ በራሱ ውስጥ አንድነት እንጂ ምንም አይነት የተለየ ልዮነቶች የለም ነግር ግን በመካከላቸው የልዮነት ሀሳብ ይኖራሉ እነሱንም በመነጋገር እየፈታን ነው

• ከለውጡ በሃላ ኢኮኖሚው በሚፈለገው ደረጃ ውጤቶች ያልታየው ኢኮኖሚው ችግር ውስጥ ሆኖ ስለተቀበልነው እሱን የማስተካከል ስራ እየተሰራ ቆይተናል፡፡ በዚህም በርካታ ሀገራት ድጋፍ ስላደረጉ ውጤት ማግኘት ተችሏል፡፡

• አሁን ላይ ኢኮኖሚው ከታመመበት ሁኔታ ላይ ወጥቶ ጤናማ ሆኗል፡፡

• የአማራና የትግራይ ክልል ውጥረት በቀጣይ በእርግጠኝነት የሚረግብና ወደ ሰላም የሚመለስ ነው፡፡ ሁሉቱም ወገን በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ያመጣውን ኪሳራ ስለሚያውቁ መካከላቸው ያለው ልዮነት በሰላም ይፈታሉ፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በኮዬ ፌጬ የኮንደሚኒዮም ግንባታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ወሰን ያለው ውዝግብ ተፈቶ ለኮንዶሚኒዮም #ባለእድለኞች ቤቶቹ እንዲተላለፉ እየተሰራ ነው።" ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
'MINDSET'🔝

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ስርጸት ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት እና በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ዙሪያ ተወዳዳሪ ብሎም ተመራጭ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ አስተሳሰብ ላይ የተመረኮዘ ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው ማህብሰብ መሰጠቱን ገለፀ፡፡

ስልጠናውን ከሀገረ ደቡብ ኮሪያ ተጋብዘው የመጡ አለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ደቡብ ኮሪያውያን ፕሮፌሰሮች መስጠታቸው ነው የተገለፀው፡፡

ስልጠናው #አስተሳሳብ ላይ የተመሰረተ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ በስልጠናው የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳዳር እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

ደቡብ ኮሪያ እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትገኝ የነበረች እና ዜጎቿም ዝቅተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው ነበሩ፣ ነገር ግን ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ዛሬ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን ስልጠናውን እየሰጡት ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ላይ ደቡብ ኮሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንደስትሪ ግንባታ በመጀመሪያው ተርታ ተሰልፋ ትገኛለች፤ይህ የሆነው ታዲያደቡብ ኮሪያውን ለቀጣዩ ትውልድ እንስራ፣ሳንበገር ተሃምር መፍጠር እንችላለን ብለው እጅ ለእጅ ተያይዘው በቁርጠኝነት በመስራታቸው የመጣ ለውጥ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከድህነት ተላቀን ለቀጣዩ ትውልድ #የተሸለች ሀገር ለማውረስ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት ለመሆን በጋራ እንረባረብ ሲል #መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia