TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ "የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማት"ን ተቀዳጀ። አየር መንገዱ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፎረም ላይ ነው የዓመቱ "የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማት" የተበረከተለት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Free_Nazrawit_Abera!!

መንግስት በቻይና መንግስት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ የምትገኘውን ናዝራዊት አበራን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት #ጓንዡ_ግዛት በሚገኘው ማረሚያ ቤት የምትገኘውን የናዝራዊት አበራን ጉዳይ #በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል።

በስፍራው በሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰራተኞችም ናዝራዊት በምትገኝበት ማረሚያ ቤት ሶስት ጊዜ በመሄድ ያለችበትን ሁኔታ ተመልክተዋል ነው ያሉት።

መንግስትም ዜጋውን የመከታተል መብቱን ተጠቅሞ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፥ ተጠርጣሪዋን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሱ ያሉ ወሬዎች #ሃሰት መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በተለይም ከተጠረጠረችበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ #የሞት_ፍርድ_ተፈርዶባታል በሚል እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሃሰት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዋ አሁን ላይ በማረሚያ ቤት የምትገኝ ሲሆን አቃቤ ህግም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ክሱን ካቀረበ በኋላ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ #እንደሚወሰንም አስረድተዋል።

መንግስት አሁን ላይ እንደ ዜጋ መጠየቅ የሚችለውን እያደረገ ሲሆን፥ ትክክለኛ ፍርድ እንድታገኝ ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tijvahethiopia
ደንገጎ🔝በደንገጎ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰዎች ህይወት ማለፉን በአካባቢ የነበሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተናግረዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች አደርሳችኃለሁ!
Via Aidu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሳዑዲ አየር መንገድ አውሮፕላን በአንዲት መንገደኛ ድንገተኛ ምጥ ምክንያት በኤርትራ ዋና ከተማ #አስመራ አረፈ። ጀነቲ ሑሴን ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ስትጓዝ የስምንት ወር እርጉዝ እንደነበረች በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። ጀነቲ ባለፈው ቅዳሜ በጉዞ ላይ ሳለች ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ምጥ ሲጀምራት ከአዲስ አበባ በመብረር ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርትራ የአየር ተቆጣጣሪዎች ጋር በመነጋገር አስመራ ማረፉን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። ኤምባሲው "አውሮፕላኑ እንዳረፈ የኤርትራ ጤና ጥበቃ አምቡላንስ በምጥ ስትሰቃይ የነበረችው ጀነቲ ሁሴንን በፍጥነት በአስመራ ከተማ ትልቁ ወደሆነው ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ወስደዋት በኤርትራውያን አዋላጅ ሀኪሞች እርዳታ ሁለት ሴት መንታ ልጆችን በሰላም ተገላገለች" ሲል ኹኔታውን አብራርቷል። ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ የጀነቲ ልጆች በአስመራ ከተማ በሚገኘው የኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሕክምና ባለሙያዎች አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት መንታዎቹ ልጆች እስከ መጪው ሐሙስ ክትትል እየተደረገላቸው ይቆያሉ።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በምስራቅ ሀረርጌ ቀርሳ ወረዳ #ደንገጎ አቅራቢያ #ቢሻን_ዲልድላ እየተባለ በሚጠራው አካበቢ በዛሬው ዕለት በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ከምስራቅ ሀረርጌ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ኮማንደር #ስዩም_ደገፋ ያገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Via ድሬ ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የአንድ አገር ህዝቦችንና ዜጎችን ለመከፋፈል፣ ለማዋጋትና ደም ለማፋሰስ የሚደረገው ቅስቀሳ መቆም አለበት፣ መንግስት ደግሞ ትልቅ ኃላፊነት አለበት፣ መንግስት ብቻም ሳይሆን ሁላችንም እያንዳንዳችን ኃላፊነት አለብን፣ የአንድነት፣ የእኩልነትና የሰላም አገር ለሁላችንም ታስፈልገናለች” ዶ/ር #አረጋዊ_በርኸ /የትዴት ሊቀመንበር/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች🔝

#በባሌ_ተራራዎች ድጋሚ ተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ወደስፍራው አቅንተው ነበር። በቂ የተሽከርካሪ አቅርቦት ባለመኖሩ ተማሪዎች #በጭነት_መኪናም ጭምር ወደስፍራው እንደተጓዙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦዴፓ ለ29ኛ ዐመት ምስረታ በዓሉ ባወጣው መግለጫ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር ለመመስረት እታገላለሁ ብሏል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር #ዐቢይ_አሕመድ ዜጎች የእኔ ማለት ትተው የእኛ ማለት እንዲጀምሩ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia