TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር...
(TIKVAH-ETH)

ኢሳት ቲቪ በትላንትናው ዕለት ዘገባው በኢንጂነሪ ታከለ ኡማ ትዕዛዝ ለOBN ጋዜጠኞች የኮንዶሚንየም ቤት ተሰጣቸው ብሎ የሰራው ዘገባ ፍፁም የተሳሳተ ነው፡፡

እውነታው ፦

1. ጋዜጠኞቹ ጥያቄ ያቀረቡት ከሁለት ዓመት በፊት ነው!

2. የከተማ አስተዳደሩ በአሰራሩ መሠረት የቤቶች ኤጀንሲ ትብብር እንዲያደርግ እና የቀበሌ ቤቶች በኪራይ ውል እንዲሰጥ የሚገልፅ ደብዳቤ በ2/11/2010 (ማለትም ኢ/ር ታከለ ከመሾሙ 8 ቀናት በፊት)ፃፈ፡፡

3. ከከተማ አስተዳደሩ በተላለፈው መመርያ መሠረት እስከ አሁን ለአንድም የOBN ጋዜጠኛ የተሰጠ ኮንዶሚንየም የለም፡፡

4.ጥያቄ ካቀረቡ ጋዜጠኞች መካከል ለ 7 ጋዜጠኞች ብቻ የቀበሌ ቤት በኪራይ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

5. ኢ/ር ታከለ ኡማ ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ ለOBN ጋዜጠኞች አይደለም የኮንዶሚንየም ቤት ሊሰጣቸው በቀድሞ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የተፈቀደው የቀበሌ ቤት እድልንም ተነጥቀናል በማለት ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ በኢ/ር ታከለ ኡማ ላይ ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡
-
-
-
-
-
እንዲህ እንዲህ ፤ እውነት እውነታው ለህዝባችን ግልፅ እያደረግን የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ከግብ እናደርሳለን፡፡

Via የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለTIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር #ድንገተኛ የስራ ምልከታ አደረጉ፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በክ/ከተማው ስር ባሉ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጎበኙ ሲሆን ከተጠቃሚዎች፣ ከክ/ከተማው አመራሮች እና ሰራተኞች ጋርም ተነጋግረዋል፡፡

Via @MayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ሰዎች በተዘጋጀው ቴሌቶን ከ626 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ቴሌቶኑ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳተፈ እንደነበር የመዲናዋ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ #መላኩ_ፈንታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጌዴኦ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ካደረገው የ30 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የከተማውን ነዋሪ በማስተባበር የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ወስኖ በየክ/ከተሞቹ ከህብረተሰቡ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ሲሰበስብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከ25.5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ንብረት የተሰበሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከ56 በላይ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪናዎች ወደ ጌድዮ መጓጓዝ ጀምረዋል።

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 Max ፓይለቶች #ስልጠናን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ👆

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአውሮፕላኑ የአደጋ ስፍራ በየዕለቱ እየተገኙ የሚያለቅሱት እናት👆

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር በተያያዘ በስፋት ከተሰራጩትና ለአደጋው ሰለባዎች መሪር ሃዘናቸውን ከሚገልፁ ፎቶግራፎች መካከል የአዛውንቷ የወይዘሮ #ሙሉነሽ_በጂጋ ፎቶ አንዱ ነው።

ከዚህ አንፃር የወይዘሮ ሙሉነሽ ታሪክ የተለየ የሚሆነው ደግሞ በአደጋው የሞተ ዘመድም ሆነ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሳይኖር በሰውነታቸው ብቻ ስለደረሰው አደጋ አዘውትረው ማዘናቸው ነው።

አዛውንቷ ወይዘሮ ሙሉነሽ ነዋሪነታቸው በመጥፎ ዕጣ የ157 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው አውሮፕላን በተከሰከሰበት ስፍራ ሲሆን፤ በተመለከቱት አሰቃቂ ክስተት ሳቢያ ከዚያች ዕለት በኋላ እጅጉን አዝነው እንቅልፍ አጥተዋል። እንባቸውንም በአደጋው ለተቀጠፉት ለማያውቋቸው ሰዎች እያፈሰሱ ቀናት ተቆጥረዋል።

የቱሉ ፈራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እኚህ እናት፤ ቤታቸውም አደጋው ከደረሰበት ሁለት ኪሎ ሜትር ያክል ርቀት ቢኖረውም ከአደጋው ቀን አንስቶ አንድም ቀን ከቦታው ርቀው አያውቁም። "እስካሁን ደጋግሜ ከአደጋው ቦታ ሄጄ ባለቅስም ሃዘኔ አልወጣልኝም" ይላሉ።

አሁንም በየቀኑ ወደ ስፍራው ከሚመጡ የአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች ጋር በመሆን ሃዘናቸውን ይገልፃሉ። "የሃገሪቷ ሁኔታ ነው የተበላሸው፤ ሰዎች ባህላቸውንና ወጋቸውን በመርሳታቸው የዚህ ሁሉ ሰው ደም ፈሰሰ" በማለት ጉዳዩን ከፈጣሪ ቁጣ ጋር ያያይዙታል።

"ከዚህ በፊት በአያት ቅድመ አያቶቻችን ዘመን አይተንም ሰምተንም የማናቀውን ነገር በእኛ ቀዬ ሲፈጠር በጣም አስደነገጠኝ፤ ይህም ነው ቀን ከሌሊት እንዳለቅስ ያደረገኝ" ይላሉ ወይዘሮ ሙሉነሽ።

እኚህ እናት እንዲህ በሃዘን የሚንገበገቡት ለኢትዮጵያዊያኑ ብቻ ሳይሆን በአውሮፕላኑ ውስጥ ለነበሩት የሰው ልጆች ነው። "የሰው ልጅ ኢትዮጵያ ሃገራችን መጥቶ ተቃጠለ። ደማቸው ባዶ ሜዳ ላይ መፍሰሱን ሳስብ ሆዴ ይረበሻል። በዕለቱ ስለተከሰከሰው የሰው አጥንትና ስለፈሰሰው ደም አልቅሼ ሊወጣልኝ አልቻለም" ሲሉ የሃዘናቸውን ጥልቀት ይናገራሉ።

አደጋው ከደረሰ በኋላ በስፍራው ስለተመለከቱት ነገርም ሲያስታውሱ፤ የአውሮፕላኑ አካል የተበተነ ወረቀት እንጂ የሰው ልጅ በውስጡ የያዘ አይመስልም ነበር። "ታዲያ ይሄ እንዴት ለእኔ እረፍት ይሰጠኛል? የእነርሱ ደም ነው የሚያቃጥለኝ" ይላሉ ወይዘሮ ሙሉነሽ።

በተለይ ደግሞ አደጋ በልጆቻቸው ላይ ደርሶ ቢሆን ኖሮስ ብለው ሲያስቡ ሃዘናቸው የሚብሰው ወ/ሮ ሙሉነሽ "እኛም ልጆች አሉን፤ ልጆቻችንም በአየር ይበራሉ። ታዲያ ከእነዚህ መካከል የእኛ ልጆች ቢኖሩስ ብዬ አስባለሁ።"

ወይዘሮ ሙሉነሽ በየዕለቱ አደጋው የደረሰበት ቦታ ይሄዳሉ። "አንድም ቀን ቀርቼ አላውቅም።" በየአጋጣሚውም እርሙን ለማውጣት ከሚመጣው ሰው ሁሉ ጋር ስለሞቱት ሰዎች ያለቅሳሉ። "ቤትም ስገባ ያ የፈሰሰው የሰው ደም ነው ትዝ የሚለኝ፤ ምግብም አስጠልቶኝ ቡናው እራሱ ቡና አይመስለኝም" ይላሉ።

ይህ አደጋ በወይዘሮ ሙሉነሽ ላይ የተለየ ጥልቅ ሀዘንን ፈጥሮባቸዋል። ከዚህ በፊት በቅርብ የሚያውቋቸውና ከቤተሰባቸው አባላት መካከልም የተለያዩ ሰዎች በሞት ተለይተዋቸዋል። ነገር ግን ይህን ያህል ሃዘን ውስጥ ገብተው እንደማያውቁ የሚናገሩት ወይዘሮ ሙሉነሽ ይህ ክስተት ለእርሳቸው የተለየ ነው።

ወይዘሮ ሙሉነሽ ይህንን ሃዘናቸውን ልክ እንደ ቤተሰብ ለመግለፅ ባላቸው አቅም በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡት ሰዎች ኃይማኖታቸው በሚያዘው መሠረት የተዝካር ሥነ-ሥርዓት ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ይናገራሉ።

ምንጭ:- BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን አቅርበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ተሹመውላቸዋል፡፡ ሹመቱ የጸደቀው በ10 ተቃውሞና 28 ድምጸ ተዓቅቦ ነው፡፡ በምክር ቤቱ የኦዴፓው ተወካይ ፍቃዱ ተሠማ ሰብሰባቢ ሲሆኑ ተሸዋሚዎቹ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ የትነበርሽ ንጉሴ፣ ተፈራ ደርበው፣ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ አብዲዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ቃለ መኻላው ግን ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡ ከነባር አባላቶች ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና ወ/ሮ ካሚያ ጁነዲ ባሉበት ይቀጥላሉ፡፡

Via evt(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia