አደጋው በአውሮፕላን አብራሪዎች ላይ ምን ስሜት ፈጠረ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን አደጋ 157 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ የኢትዮጵያዊያንን፣ የኬንያዊያንን፣ የጣሊያናዊያንን እና ሌሎች የሠላሳ ሃገራትን ልብ ከመስበር አልፎ ዓለምን በጠቅላላ በድንጋጤ ያናወጠ ክስተት ነበረ።
ይህን አደጋ ተከትሎ ከሃምሳ በላይ ሃገራትም ሁኔታው ተጠንቶ፣ ተጣርቶና የመረጃው ሳጥን ውጤት ይፋ እስኪደረግ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላኖቻቸውን ከመብረር ማገዳቸውም ይታወሳል።
በዚህም ወቅት የተለያዩ ሰዎች ሐዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ባለፈው እሑድ ኢትዮጵያ ውስጥ ተምሳሌታዊ ቀብር ሥነ-ሥርዓት ሲደረግ በኬንያ ደግሞ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ በሙሉ የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ተዘጋጅቶ ነበር።
ዜናው በርካቶች ላይ ጥልቅ ሐዘንን የፈጠረ ቢሆንም ለሥራው ቅርብ የሆኑት የአውሮፕላን አብራሪዎች ላይ ተለየ ስሜትን መፍጠሩ አይቀርም። ቢቢሲ ሁለት አብራሪዎችን ከአደጋው ጋር ተያይዞ የተፈጠረባቸውን ስሜት እንዲያጋሩ ጠይቋቸው ነበር።
ካፕቴን #መኮነን_ብሩክ አውሮፕላን አብራሪ ከሆነ ከሦስት ዓመታት በላይ የተቆጠሩ ሲሆን፤ አርሱም ሴስናር ካራቫን 208 የተሰኙ አውሮፕላኖች ያበራል። ትውስታውን ወደዛች አሳዛኝ ዕለት መለስ ባደርገነው ጊዜ መኮነን ጥልቅ ሐዘኑን ገልፆ "በረራ 302 እንደወደቀ እኛ ወደ ጂንካ ለመብረር በመዘጋጀት ላይ ነበርን። በረራ 302 አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፉንና እንደሚመለስ ከበረራ መቆጣጠሪያ ማማው ሞተራችንን አጥፍተን እንድንጠብቅ በራድዮ ትዕዛዝ አስተላለፉልን" ይላል።
ካፕቴን መኮነን የሚያበረው ትንሽ አውሮፕላን ሲሆን፤ የ12 ሰዎችን ነፍስ በአየር ላይ ይዞ መጓዝና ከ170 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ መካከል ትልቅ ልዩነት ቢኖርም እንኳን ሁሉም የአየር ጉዞ እራሱን የቻለ ስጋትና ውጥረት እንዳለው ይናገራል።
"ከግማሽ ሰዓት በኋላ በራድዮ አውሮፕላኑ ከራዳር እንደወጣና በአየር ኃይል ፍለጋ እንደተጀመረ ሲነገረን መከስከሱ ወዲያውኑ ነበር የገባኝ" የሚለው ካፕቴን መኮነን አክሎ በናሽናል ጂዮግራፊ 'ኤርክራሽ ኢንቬስትጌሽን' ፕሮግራሞች እንደሚያስረዱት አውሮፕላን ከራዳር ጠፋ ማለት መጥፎ ነገር እንደተከሰተ የሚያሳይ የመጀመሪያው ምልክት ነው በማለት ያስረዳል።
"መከስከሱን ተረዳን፤ ወዲያውኑ በራድዮ የመብረር ፈቃድ ተሰጠንና ልባችን እንደተሰበረ ወደ ጂንካ አመራን" ይላል።
ሜሮን አመሃ በአሜሪካ አየር ኃይል ውስጥ በተንታኝነት የሠራች ሲሆን፤ በሥልጠና ወቅት ለአየር ኃይል አብራሪነት የበረራ ሥልጠና ወስዳ ሰርቲፊኬት ለመውሰድ 100 ሰዓታት የሚቀሯት ቢሆንም "የምይዘውን አውሮፕላን የማላውቀው ከሆነ ምንም ሰላም አይሰጠኝም" ትላለች።
"አደጋው በጣም አሳዛኝና ልብ የሚሰብር ስሜት ነው የፈጠረብኝ" የምትለን ሜሮን ብዙውን ጊዜ የአውሮፕላን አደጋ በሚሰማበት ወቅት በእውቀት እጥረት ወይም በቴክኒክ ብልሸት የተፈጠረ ነው ተብሎ እንደሚጠረጠርም ትናገራለች።
"እንደዚህ ዓይነት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ የብዙዎችን አውሮፕላን አብራሪ ችሎታ፣ አቅምና እውቀታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው" የምትለን ሜሮን "ይህም ሙያችንን የሚያሰድብና የሚያስጠይቅ ክስተት" ሊሆን የሚችል ነበር ትላለች።
ነገር ግን የአሁኑ አደጋ "የአውሮፕላኑ ችግር በመሆኑ በይበልጥ ልብ የሚሰብር ነገር ነው። ለብዙዎች ሕይወት ኃላፊነት ይዞ ለሚያበር ሰው ብቻ ሳይሆን ለተሳፋሪ እራሱ ለማመን የሚከብድ እውነታ ነው። ምክንያቱም የአውሮፕላን ችግር በማንም ሊፈታ የሚችል አይደለም" ትላለች። አክላም ኃላፊነቱን የሚወስደው ማን እንደሆነም ሊታሰብበት ይገባል ስትል ትጨምራለች።
ካፕቴን መኮነን "እኛ የምንይዘው አውሮፕላን አነስ ያለ በመሆኑ በወቅቱ ምንም ብናዝንም የበረራ ጉዟችንን ለመቀጠል ብዙ አልከበደንም ነበር። በዚያን ሰዓት ትልቅ አውሮፕላን የምንይዝ ቢሆን ኖሮ በጣም እንደነግጥ ነበር። ግን ዞሮ ዞሮ እንጀራችን ስለሆነ ምንም ማድረግ አልቻልንም አበረርን" ይላል በሐዘን በተሰበረ ስሜት።
በቁጥር ሲታይ፤ ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር የተያያዙ አደጋዎች ከአየር አደጋዎች አንፃር እጅግ በጣም ይበዛሉ። በዓለም ዙሪያ በዓመት ቢያንስ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች በመንገድ ትራንስፖርት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የዓለም አቀፍ የመንገድ ትራንስፖርት ደኅንነት ማኅበር ይገልፃል።
በአየር ትራንስፖረት የሚፈጠሩ አደጋዎችን በምንመለከትበት ጊዜ ደግሞ ከዓመት ዓመት የሚለያይ ሲሆን ለምሳሌ እ.አ.አ በ2016 በዓለም ዙሪያ 325 ሰዎች፣ በ2017 ከ37 ሚሊዮን በረራዎች 13 ሰዎች፣ በ2018 ደግሞ 500 ሰዎች በአውሮፕላን አደጋ ሳቢያ በሞት ተቀጥፈወል።
የአየር ትራንስፖርት አደጋዎች ከቁጥር አንጻር ዝቅተኛ ነው። "እኛ ሁሌም በአየር ላይ ነንና ሰው ሠራሽ ነገር ምንጊዜም ዘላቂነት የለውም። አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ሁላችንንም ነው የሚነካን፤ ምክንያቱም እንደ ቤተሰብ ነን" የሚለው ካፕቴን መኮነን "ሰው የቤተሰቡን አካል ሲያጣ ምንም ማለት አይችልም ከማዘን ሌላ። ግን እኔ ማብረሬን አላቆምም" ይላል።
ሜሮን ደግሞ "እንደዚህ ዓይነት አደጋ በምሰማበት ወቅት ለማብረር ያለኝ ፍላጎትና ባለሙሉ ልብነት ላይ የራሱ የሆነ ውጤት ይኖረዋል" በማለት አደጋው ከፈጠረባት ሃዘን ባሻገር ያለውን ውጤት ገልፃ፤ ሁሉንም የሚነካ አደጋ እንደመሆኑ "የአደጋው መንስዔ ውጤቱ ቢታወቅ ለአብራሪዎችም ሆነ ለተጓዦች በሙሉ ልብ ለመብረር ተስፋ ይሰጣል፤ ለዚህም ነው በጉጉት ውጤቱን የምንጠባበቀው" ትላለች።
ምንጭ፦ bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የተቻለኝን ለወገኔ!
#በጌዴኦ ማህበረሰብ ላይ በደረሰው ችግር የተጎዱ ወገቻችን #ለመርዳት በአርባሳት በፅዳት እቃዎች እና የተለቻልን አልባሳት እንዲሁም የተለያዩ አፈላጊ ቁሳቁስ እናግዝ።
አድራሻ፦ ቦሌ ሞርኒንግ ስታር ሞል
Morning⭐️Star Mall

ሀዋሳ--TIKVAH-ETH ከአለን ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር ለጌዴኦ ተፈቃዮች የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ሀዋሳ የምትገኙ በየትኛውም አካባቢ ሆናችሁ በነዚህ ስልክ በመደወል ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ፦
Bisrat (0935932153)
Getenet (0916424992)
Aregi (0916109080)
Ethiopia (0915607656)
Hareg (0916448414)
Yordanos (0934727411)
በተጨማሪ....
•ሀዋሳ #ቱሩፋት አካባቢ DURESSA GROCERY በመሄድም ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ ፦ አቶ ሁሴን ከድር +251916828904

#update Pantsir-S1 የተሰኘው ዘመናዊው ሩሲያ ሰራሽ ጸረ-አውሮፕላን መሳሪያ በኢትዮጵያ እንዳላት ዲፈንስ ብሎግ የተሰኘ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ መከላከያ ሠራዊቷ ቢያንድ የአንድ Pantsir-S1 ባለቤት ሆኗል ብሏል ዘገባው፡፡ የጦር መሳሪያው አምራች ኩባንያ ይህንኑ መሳሪያ ለኢትዮጵያ ስለመሸጡ አስተያየት ተጠይቆ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከዚሁ ጸረ-አውሮፕላን መሳሪያና ራዳሮች የተወሰኑትን ለመግዛት የሩሲያና ዩክሬን ኩባንያዎችን ጠይቃ እንደነበር ምንጮት ጠቁመዋል ሲል አክሏል ዘገባው፡፡ ድረገ ገጹ ዘገባውን ያወጣው ባንድ የኢቢሲ ዜና ላይ መሳሪያው በመከላከያ ሠራዊቱ ወታደራዊ ካሚዮን ላይ ተገጥሞ ሲዘዋወር በማየቱ ነው፡፡ ሚሳይሉ የተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ሔሊኮፕተሮችንና ክሩይዝ ሚሳይሎችን ጥቃት ማክሸፍ ይችላል፡፡
Via wzemradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via wzemradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይ🛬ዶሃ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ #ዶሃ_ቀጠር ገብተዋል። Ethiopian Embassy in Doha

ሀሰት ነው‼️
በትላንትናው ዕለት #በአዲስ_አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ #ግጭት የብሄር ነው፤ ቄሮ እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ተጋጩ እየተባለ በማዕበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ሀሰት ነው። በጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ የታክሲ ሹፌር የሆነ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የተፈጠረውን በዝርዝር አብራርቶልኛል። በማህበራዊ ሚዲያ ጉዳዩን አግዝፎ በከተማው ውስጥ እልቂት እና ነውጥ ለመፍጠር እንቅስቃሴዎች ታይተዋል። ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ትንሽ የምትመስለን ጉዳይ ነገ አድጋ ታጫርሰናለችና በማዕበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎችን ለሌሎች ስታጋሩ በጥንቃቄ ይሁን።
•እውነተኛነቱን ተረጋግታችሁ አረጋግጡ
•በብዙ መልኩ አጣሩ!
•ከስሜታዊነት ይልቅ በምክንያታዊነት ላይ ተመስርታችሁ በብስለት ሁኔታዎችን አጢኑ!
•ስሜታዊነት ሀገሪቷን ለማፈራረስ ምክንያት ይሆናል እና የምፅፈውን እንጠንቀቅ!

#update በጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አህመድ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ #ኳታር ገብቷል፡፡ የልዑካን ቡድኑ ዶሃ ሲደርስ የአገሪቱ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር፣ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር እንዲሁም በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር አቀባበል አድርገውለታል፡፡
ምንጭ፡ በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡ በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦይንግ❓
ቦይንግ ኩባንያ እየጨመረ የመጣውን ዓለም አቀፍ ጫና ለመቋቋም ሲውተረተር የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን መርማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ 302 ቦይንግ 737 አውሮፕላን የመረጃ ማጠራቀሚያ ሳጥን ግምገማ በፓሪስ የጀመሩት መርማሪዎች ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አንድ ሒደቱን በቅርብ የሚያውቁ የመረጃ ምንጭ ለሬውተርስ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያው 737 ማክስ አውሮፕላን ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ለመከስከስ ያበቃውን ምክንያት ለማወቅ ወራት የሚፈጅ ቢሆንም አምራቹ ቦይንግ ግን የከፋ ጫና ውስጥ ገብቷል። በተለይ በኢትዮጵያው እና ከዚህ ቀደም በኢንዶኔዥያ በተመሳሳይ አውሮፕላን ላይ በተከሰተው አደጋ መካከል "ግልጽ መመሳሰሎች" መኖራቸውን የኢትዮጵያ የትራንስፖርት ምኒስትር እና የፈረንሳይ የበረራ ደኅንነት ምርመራ ባለሥልጣን ካረጋገጡ በኋላ ቦይንግ 737 ማክስ እንዴት የደኅንነት ማረጋገጫ አገኘ የሚለው ጥያቄ በርትቷል።
ከጃካርታ አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰው የላየን አየር መንገድ አውሮፕላን እንደ ኢትዮጵያው ሁሉ 737 ማክስ 8 ነበር።
የካናዳ የትራንስፖርት ምኒስትር አገራቸው ለ737 ማክስ አውሮፕላን የሰጠችውን የደኅንነት ማረጋገጫ እንደገና እያጤነች መሆኑን መናገራቸው በቦይንግ ኩባንያ ላይ ጫናውን አበርትቶታል። ዎል ስትሪት ጆርናል እና ሲያትል ታይምስ ጋዜጦች ቦይንግ ለአውሮፕላኑ የደኅንነት ማረጋገጫ ለማግኘት ያለፈበትን ሒደት ጥያቄ ውስጥ የከተቱ ዘገባዎች አስነብበዋል። ሲያትል ታይምስ የአሜሪካ የበረራ አስተዳደር ባለሥልጣናት የ737 ማክስ አውሮፕላንን ደኅንነት የመፈተሽ ኃላፊነታቸውን መልሰው ለቦይንግ ሰጥተዋል ብሏል። ቦይንግ አውሮፕላኑ የበረራ ደኅንነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ያሳወቀበት ትንታኔም ጉድለቶች እንዳሉበት ይኸው ጋዜጣ ዘግቧል።
የኢትዮጵያው አደጋ ከተከሰተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቪዲዮ ማብራሪያ የሰጡት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሞለንበርግ በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዥያ አየር መንገዶች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው ለኩባንያቸው ስም እና ለሚከተለውን አሰራር ጥብቅና ቆመዋል። "በማንኛውም ምክንያት አደጋ ሲፈጠር ያለማቋረጥ ለምን እንደተከሰተ ለማወቅ ትኩረት እናደርጋለን" ያሉት ሞለንበርግ ምርመራው እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል። የቦይንግ ባለሙያዎች ለመርማሪዎች ቴክኒካዊ እገዛ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ሁለቱን አውሮፕላኖች ለመከስከስ ሳያበቃቸው አይቀርም የተባለውን የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ተሻሽሎ በቅርቡ ሥራ ላይ ይውላል ያሉት ሞለንበርግ የኩባንያው ባለሙያዎች በሚያመርቷቸው አውሮፕላኖች ጥራት እና ደኅነት እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ

#update በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ ተብሎ የሚጠራው ቀበሌ ውስጥ ዛሬ ጠዋት 1:30 ላይ ባልታወቁ ኃይሎች 5 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ሲሆኑ፣ ሁለቱ ደግሞ የውጭ ዜጎች መሆናቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopua
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopua
አዲስ አበባ🔝በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ #ብስራተ_ገብርኤል በሚባል አካባቢ እየተሰራ ያለ አፓርትመንት ሊፍት ወድቆ ሰው ላይ አደጋ ደርሷል።
Via OBANI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via OBANI
@tsegabwolde @tikvahethiopia