TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ ፊርማ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የክልል ሕገ መንግስት አይደለም፣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሕገ መንግስት ሆኖ የሚቀርበው የአብዛኛውን ህዝብ ፍላጎት ለመመለስ እንጂ የአንድን ክልል፣ የአንድን ብሔር ፍላጎት ለማሳካት አይደለም፡፡

• የሁሉንም ፓርቲ ፍላጎት የሚያሟላ ሕገ መንግስት ኢትዮጵያ ከ100 ዓመት በኋላም ሊኖራት አይችልም፡፡

• ፓርቲዎች ሰብሰብ ማለት ከቻሉ መንግስት ባለው አቅም እንዲሁም ሌሎች አካላትን በማስተባበር ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው፡፡ ለ100 ፓርቲ ግን ይህንን ማድረግ አይቻልም፡፡

• የእኛ ፍላጎት ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ዴሞክራሲን ማምጣት እንጂ ለዘመናት ስልጣን ላይ መቀመጥ አይደለም፡፡

• የመንግስት ሚዲያዎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማያዳላ መልኩ ማስተናገድ አለባቸው፡፡

• እውነተኛ ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመገንባት አሁን ያለውን ውጥንቅጥ ማለፍ ይጠበቅብናል፡፡

• ዛሬ በርካታ የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያ ያለችበትን መሆን ይመኛሉ፣ ልምድ ይጠይቃሉ፡፡ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ የተሰደዱ እንዲመለሱ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሆነው ለአገር ግንባታ እንዲነጋገሩ ብዙዎች ይመኛሉ፣ ልምድ ይጠይቃሉ፡፡

• አሁን ያለንበት ሁኔታ በለፉት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የሚዲያ ነፃነት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሻቸውን የሚናገሩበት ጊዜ ነው፡፡

• አሁን ላለንበት ጊዜ መምጣት ዋጋ የከፈላችሁ ሰዎች እንደ ድል አድራጊ ክብር ሊሰማችሁ ይገባል፡፡

• ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ፣ እኔና እኛ ላይ ብቻ ያተኮሩ ንግግሮች የፖለቲካ ፓርቲዎችን የኋላ ኋላ ዋጋ ስለሚያስከፍሉ በንግግራችንም በድርጊታችንም የሚታዘበን ህዝብ እንዳለ እያሰብን ቢሆን መልካም ነው፡፡

Via etv
@tsegbawolde @tikvahethiopia
ወረታ🔝

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት 8ኛ የደረቅ ወደብ መደረሻውን ለመገንባት ዛሬ በወረታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል። የመሠረት ድንጋዩ በተቀመጠበት ወቅት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር #አምባቸው_መኮንን፣ ጠትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ #ዳግማዊት_ሞገስን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መከናወኑን የዘገበው አብመድ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
107 ፓርቲዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እባካችሁ ተዋሃዱ ብሎ ሲማፀናቸው የነበሩት ወደ ሰማንያ (80) አካባቢ የሚገመቱ ፓርቲዎች በጥቂት ወራት ውስጥ 107 ደርሰዋል።
--
ከ 107ቱ ውስጥ ሰላሳ ሶስቱ (33) "#ኢትዮጵያ "ን በፓርቲያቸው ስያሜ ውስጥ ተጠቅመዋል። #አማራ የሚል ስያሜአቸው ውስጥ ያላቸው
#አምስት ሲሆኑ #አስራ_ሶስቱ ደግሞ #የኦሮሚያ ፓርቲዎች ናቸው። እነ አንዳርጋቸው ፅጌ ብዙ ጊዜ ክፍፍል ያለው "በዘውግ" የተደራጁ ፓርቲዎች ላይ ነው ቢሉም በኢትዮጵያዊነት ስም የተደራጁት 33 ፓርቲዎች ራሱ ተቀራርበው መዋሃድ አልቻሉም። #ሰማያዊ_ፓርቲ ለምሳሌ #ከአግ7ጋር ተዋህዶ ፈርሷል ቢባልም ዝርዝሩ ውስጥ ተካቷል።
--
ኢህአዴግ እንደ ግንባርም በተናጠልም የፈረመበት ምክንያት ግራ ያጋባል። በዛ ላይ የተፈረመበት ሰነድ ላይ አዴፓ እና ኦዴፓ ሳይሆን #ብአዴን እና #ኦህዴድ ነው የሚለው። አንድ ወጥ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሆነው በድጋሚ ለመመዝገብ ነው ለስያሜው እንኳን ቸልተኛ የሆኑት?
--
ለማንኛውም ሰማንያ አካባቢ ፓርቲ የተሳተፈበት የ 1997 (2005) ምርጫ ላይ የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ያሸነፉት ፓርቲዎች ከላይ ያሉት ነበሩ። በርካቶቹ አንድም መቀመጫ እንዳላገኙ የሚታወቅ ነው።

Via THE FINFINNE INTERCEPT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጥያቄዎቻችሁ መልስ፦

1.የTIKVAH-AID እና TIKVAH-AID 2 በተመለከተ

ከዚህ ቀደም በባንክ እየሄደን ገንዘብ በማሰባሰብ የምንተጋገዝበትን መንገድ በሌላ በተሻለ አማራጭ ለመተካት ብዙ ሲታሰብ ነበር። SMS ለማስጀመርም እንቅስቃሴ ተሞክሯል። ግን ያለው ሁኔታ ምቹ ባለመሆኑ ሊሳካ አልቻለም።

አሁን ግን TIKVAH-ETH ከሜዳ ቻት ጋር በመተባበር በአሞሌ በኩል ስራዎችን ለመስራት ዝግጅታችንን ጨርሰናል። በቀጣይ እንዴት እንደሚሰራ እናሳውቃለን።

2. የTIKVAH-EDU

የመማሪያ ቻናላችንን በተመለከተ ብዙ ለመስራት ተሞክሯል። ነገር ግን #በፍቃደኝነት ላይ ተመስርተው ለሲሩ የተመዘገቡ ሰዎች ስራቸውን በአግባቡ ሊሰሩ ባለመቻላቸው በተቻለ አቅም ሌሎች አማራጮችን እያፈላለግን ነው።
.
.

የተለያዩ አስተማሪ ፅሁፎቻቹን በTIKVAH-ETH ለማቅረብ የምትፈልጉ፦

.አጭር(ከ30 መስመር ያልበለጠ)
.አስተማሪ
.ለሀገር ግንባታ ጠቃሚ የሆኑ ፅሁፍ ያላችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ማስታወቂያ ለማስነገር የምትፈልጉ፦ #ፍቃድ ያላችሁ እና በTIKVAH-ETH አሰራር ለመገዛት ፍቃደኛ የሆናችሁ #ብቻ መጠቀም ትችላላችሁ!
.
.
.
ሌላው ...

የግል ምልከታዬን የማጋራበት፣ ልዩ ልዩ ፅሁፎችን ከተለያዩ ሰዎች መራርጬ የማቀርብበት፤ አባባሎችን፤ የፖለቲካ፤ የማህበራዊና ሌሎች ምልከታዎችን እንዲሁም ከተለያዩ ገፆች የምመርጣቸው ልዩ ልዩ ፅሁፎችን በአማርኛ እና እንግሊዘኛ ለናተ የማጋራበትን የግሌን ቻናል #ከፈለጋችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ @tsegabwolde1

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ የግል የTELEGRAM ቻናሌ ነው! በዚህ ላይ የሚፃፉት እና የሚሰራጩት ፅሁፎች ሁሉ #የግል_አመለካከቴን ውስጤ ያለውን ሀሳብ ብቻ የሚያንፀባርቁ ናቸው። እንዲሁም አንብቤ የወደድኳቸውን ነገሮች ሁሉ አጋራችኃለሁ!

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-WeEn84b8FUyA
ሱሉልታ🔝

በዛሬው ዕለት #ከሱሉልታ ወደአዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ነበር። በአካባቢው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እንደተናገሩት ጉዳዩ #በህገ_ወጥ ቤቶች ላይ ሊወሰድነው በተባለ እርምጃ ሳቢያ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን እናደርሳችኃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia