TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቁር ሳጥኑ ወደ ውጭ ሊላክ ነው‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዕሁድ የተከሰከሰውን ቦይንግ 737 ማክ 8 አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን ለምርመራ ወደ ውጭ ሊለክ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ #ተወልደ_ገብረማርያም ገልጸዋል።

አቶ ተወልደ ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲኤንኤን የቢዝነስ ተንታኝ ሪቻርድ ኩዌስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ የመረጃ ሳጥን መመርመሪያ መሳሪያ ስለሌላት ለምርመራ ወደ ውጭ ይላካል።

ጥቁር ሳጥኑ ወደ አሜሪካ ሊላክ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ተወልደ “መረጃው የለኝም፤ ሆኖም ከቅርበትና ከፍጥነት አኳያ ምናልባት ወደ አውሮፓ ሀገራት ሊላክም ይችላል።” ነው ያሉት።

ባሳለፍነው ዕሁድ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በረራ በጀመረ በስድስት ደቂቃ ውስጥ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ 149 ተሳፋሪዎችና 8 የበረራ ሰራተኞች ሁሉም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

አቶ ተወልደ ለሪቻርድ ኩዌስት እንዳሉት በአየር ትራፊክ ቁጥጥር የድምፅ መቅጃ መረጃ መሰረት አብራሪው የበረራ ሚዛን ማስጠበቅ ችግር አጋጥሞት ነበር።

በተቀዱ የድምፅ ልውውጦች መሰረት አብራሪው የአውሮፕላኑን የበረራ ሚዛን ለማስጠበቅ ችግር ስላጋጠመው፤ ተመልሶ ለማረፍ ጠይቆ መስመር ቢሰጠውም 2 ሰዓት ከ44 ላይ አውሮፕላኑ ከራዳር ዕይታ ውጭ ሆኗል ነው ያሉት።

ሌላው ለአቶ ተወልደ የቀረበላቸው ጥያቄ አብራሪው ስለ ተከሰከሰው አውሮፕላን የበረራ ቁጥጥር መመሪያ በደንብ ያውቃል ወይ? ስልጠናው ወስዷልን? የሚል ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ “አዎ በቦይንግ የተዘጋጀ መመሪያ አለ፤ይህ የበረራ መመሪያ ለአብራሪዎቹ እንዲደርሳቸውና ግልፅ እንዲሆንላቸው ተደርጓል፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪም በበቂ ሁኔታ ስለአዲሱ ቦይንግ ማክስ አውሮፕላኑ የበረራ ደህንነት መመሪያው ግንዛቤ አለው። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከሌሎች የተለየ ስለሆነ ሁሉም አብራሪዎች ስልጠና ወስደዋል” ብለዋል።

ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ኢትዮጵያ ውስጥ መከስከሱን ተከትሎ በርካታ ሀገራትና አየር መንገዶች ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን ከበረራ አገልግሎት አግደዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እግዚያብሔር #ሰጠ እግዚያብሔር #ነሳ አብራው ከምትሠራ ካፒቴን #እጮኛው ጋር #ሊጋቡ እቅድ ይዘው ነበር ” የአብራሪ #ያሬድ_ጌታቸው አባት ዶ/ር #ጌታቸው_ተሰማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"እግዚያብሔር #ሰጠ እግዚያብሔር #ነሳ አብራው ከምትሠራ ካፒቴን #እጮኛው ጋር #ሊጋቡ እቅድ ይዘው ነበር ” የአብራሪ #ያሬድ_ጌታቸው አባት ዶ/ር #ጌታቸው_ተሰማ @tsegabwolde @tikvahethiopia
ማረሚያ: ይህን አጭር መረጃ ተመልክቶ የወጣው ፎቶ ከአዲስ ስታንዳርድ የተገኘውን የታችኛውን ፎቶ በመምረጥ ውስጥ የገባ እንደሆነ ለማሳወቅ እወዳለሁ። በሌላ በኩል በማዕበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉት ካፕቴኑን እና እጮኛውን የሚመለከቱ ፎቶች ሀሰተኛ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ባለፈው እሁድ #በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ያጡ ዛሬ አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

ፎቶ፦ AP
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Countries stopping Boeing 737 MAX 8 flights:

- China
- United Kingdom
- Germany
- France
- Mexico
- Brazil
- Argentina
- Indonesia
- Turkey
- Ireland
- Australia
- Ethiopia
- South Africa
- Malaysia
- Singapore
- Sultanate of Oman
- morocco
- Mongolia
- Netherlands
- India
- Italy
- Norway

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካፕቴን ያሬድ ሃይማኖታዊ የሀዘን ስርአት #ያለ_አስከሬኑ በሞምባሳ ተፈፀመ‼️
.
.
ከጥቂት ቀናት በፊት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 ዋና አብራሪ የነበረው #ያሬድ_ጌታቸው ሃይማኖታዊ የሀዘን ስርአት በሞምባሳ በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በተሰበሰቡበት በእስልምና እምነት መሰረት አስከሬኑ በሌለበት የሐዘን ስርአት በኬንያዋ የባህር ዳርቻ ከተማ #ሞምባሳ በሚገኘው ታዋቂው የባሉች መስጊድ ውስጥ ተፈፅሟል።

አስከሬኑ በሌለበት የሃይማኖታዊ የሀዘን ስርአቱ መፈፀሙ ቤተሰቦቹ አስከሬኑ #እንደማይጠብቁ አሳይ መሆኑን የቢቢሲው ጋዜጠኛ #ዋዚር_ሀስሚን ገልጿል።

ታዋቂው የሞምባሳ ጦማሪ ኦሚ ዳላህ የስርአቱን ቪዲዮ በገፁ ላይ የለጠፈ ሲሆን የካፕቴን ያሬድ ወንድምም በቀኝ በኩል እንደታየ ቪዲዮው ያሳያል።

ታዋቂው የሞምባሳ ጦማሪ ኦሚ ዳላህ የስርአቱን ቪዲዮ በገፁ ላይ የለጠፈ ሲሆን የካፕቴን ያሬድ ወንድምም በቀኝ በኩል እንደታየ ቪዲዮው ያሳያል።

ያሬድ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ሲሆን እናቱ ኬንያዊ ሲሆኑ አባቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

ሞምባሳ ውስጥ ቤት ያላቸው ሲሆን የቤተሰቡ መኖሪያ ተደርጎ እንደሚወሰድም ይህው ቤት እንደሆነ ተገልጿል።

ትናንት መላው ቤተሰብ ከሞምባሳ ሞይ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በከፍተኛ መረበሽና ሀዘን እንደነበር የሃገሪቱ ሚዲያ ኤንቲቪ ዘግቧል።

በቦታው ላይ እናቱና አጎቱ የነበሩ ሲሆን አባቱ ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ በኢትዮጵያ ያለውን ምርመራ እየተከታተሉ በመሆናቸው መምጣት እንዳልቻሉ አጎትየው ገልፀዋል።

ዘገባው ጨምሮም በወቅቱ እናቱን ለማየት እየበረረ እንደነበርና የመጨረሻ ንግግሩም ከእናቱ ጋር ሲሆን "ወደ ናይሮቢ እየመጣሁ ነው። ስልኬን ረስቻለሁ ግን ስገባ እናወራለን" የሚል ነበር።

ልምድ ያለውና #የመጠቀ_ችሎታ እንደነበረው ስለ ተገለፀው ዋና አብራሪ ያሬድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም የበረራ ሰዓቱም ከስምንት ሺ በላይ እንደበረረ አደጋውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC
ፎቶ: Getty Images
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING የጀርመን የፌደራል አውሮፕላን አደጋ መመርመርያ ቢሮ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከሰከሰው አውሮፕላንን #black_box እንዲመረምር ቢጠየቅም "ሶፍትዌሩ ስለሌለን መመርመር አንችልም" ብሎ መልስ ሰጥቷል።

Via Elias Mesert(@eliasmeseret)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING ቦይንግ በስተመጨረሻ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት እንዳይበሩ ወስኗል። ኩባንያው ከአሜሪካ የበረራ አስተዳደር ባለሥልጣን፣ ከአሜሪካ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደኅንነት ቦርድ፤ ከበረራ ባለሥልጣናት እና በመላው ዓለም ከሚገኙ ደንበኞቹ ጋር በመነጋገር ለጥንቃቄ እና ለመንገደኞችን ደኅንነት የአውሮፕላኑን ደኅንነት ለማረጋገጥ ቦይንግ 737 ማክስ ከበረራ እንዲታገድ መስማማቱን አስታውቋል።

Via Eset Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

• እምቢተኛ ሆና የቆየችው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቦይንግ 737 ማክስ 8 እና 737 ማክስ 9 ከበረራ የሚያግድ አስቸኳይ መመሪያ ይፋ አድርገዋል።

• ቀደም ብሎ ካናዳ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከበረራ አግዳለች። የአገሪቱ የትራንስፖርት ምኒስትር እነዚህ አውሮፕላኖች ከካናዳ አየር ማረፊያዎች መነሳት፤ ማረፍ አሊያም የካናዳን የአየር ክልል #ማቋረጥ አይችሉም ብለዋል። በካናዳ የታገዱት 737 ማክስ 8 እና 9 የተባሉት የአውሮፕላኑ ሞዴሎች ናቸው። የካናዳ የትራንስፖርት ምኒስትር ከዚህ ውሳኔ የሚያደርስ እና አውሮፕላኖቹን የተመለከተ መረጃ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia