TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን መካከል ነገ #በሞያሌ ከተማ ለሚካሄደው የሠላም ኮንፈረንስ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተነግሯል፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ለመሳፍ የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል የፀጥታ እንዲሁም የዞን እና የወረዳ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ኡጋዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች ሞያሌ ከተማ እየገቡ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረሪ

በሐረሪ ክልላዊ መስተዳድር ስር በሚገኘው #ጅኔላ_ወረዳ በአካባቢው የሚኖሩ ከስልሳ በላይ ቤቶች ከሌላ አካባቢ መጡ በተባሉ አካላት ጥቃት ተፈፀመባቸው።

የተወሰኑ ነዋሪዎች በሁኔታው በመስጋት ቤታቸውን ጥለው ስለመውጣታቸው ጀርመን ራድዮ ደረሰኝ ባለው መረጃ ጠቁሟል።

ጥቃት ፈጻሚዎቹ ወደ ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤት በመዝለቅ የተለያዩ ንብረቶች ሰባብረዋል ተብሏል። በስፍራው የተገኘው የDW ዘጋቢ የአንዳንድ መኖርያ ቤት አጥሮች ፈርሰው፣ አንዳንዶችም በስለት (ባንጋ) መቆራረጣቸውን ታዝቧል። የውሀ መስመር እና የመብራት ቆጣሪ የተሰባበረበት መኖርያ ቤትንም ተመልክቷል።

ጥቃቱ የተፈጸመው “የአካባቢው መሬት የእኛ በመሆኑ ልቀቁ በሚሉ አካላት” መሆኑን የሚናገሩት ተጎጂ ነዋሪዎች በድርጊቱ ማዘናቸውን ለጀርመን ራድዮ ገልጸዋል። “አሁንም ችግራችንን #አውጥተን ለሚዲያ #ለመናገር እንሰጋለን፤ ህይወታችንም ያሳስበናል፤ ምን ዋስትና አለን” ሲሉ ስማቸውን ለመግለፅ የፈሩ ነዋሪ ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ኃላፊ “ግጭቱ መኖርያ ቤቶቹ ከተገነቡበት ቦታ የይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ” መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በግጭቱ የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ነገር ባይኖርም በጥይት የተመታ አንድ ሰው ግለሰብን ጨምሮ አራት ሰዎች ተጎድተዋል። በጥይት ተመቷል የተባለው ግለሰብም በሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ እንደሚገኝም አስረድተዋል። በግጭቱ በስልሳ አንድ መኖርያ ቤቶች ላይ ጥቃት ሲደርስ ዝርፊያና ንብረት ማውደም ተፈፅሟልም ብለዋል።

ህብረተሰቡን የማወያየት ስራ እየተሰራ መሆኑ እና የተፈጠረው ሁኔታም #ተረጋግቷል ቢባልም ችግሩ መሰረታዊ መፍትሄ ያላገኘ በመሆኑ በነዋሪዎች አንድ አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ናቸው።

#የመከላከያ_ሰራዊት አባላት ግጭቱን ለማረጋጋት በአካባቢው ሲዘዋወሩ የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ የተመለከተ ሲሆን ነዋሪዎች ዱላ፣ ስለታም ነገሮች (መቁረጫ ባንጋ) ይዘው አካባቢያቸውን ሲጠብቁ አስተውሏል። ሐኪም ጋራ እየተባለ በሚጠራው በዚህ አካባቢ የተፈጠረው ሁኔታ ባለመረጋጋቱ ከ150 በላይ ነዋሪዎች በየዕለቱ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ተሰባስበው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ (አማርኛው አግልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኢትዮጵያ #የጥፋት ኃይሎች በስፋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን የምዕራብ ኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በወሰደው #እርምጃ ማረጋጋት እንደተቻለ የኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀኔራል #ብርሃኑ_ጁላ ተናገሩ ። ዛሬ የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በአሶሳ ከተማ ገምገማ አካሂዷል። በግምገማው ወቅት ህብረተሰቡ ከነበረበት የሥጋት ስሜት ወጥቶ በአካባቢው #ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተገልጿል፤ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ይገባል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትግራይ የህዝብ ግንኙነትና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ፦

ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ ዋነኛ አጀንዳችን ሰላም፣ ዲሞክራሲና ልማት ነው!!

የአማራ ክልል ምክር ቤት፣ ከየካቲት 26-29/2011ዓ/ም እያካሄደው ባለው 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 12ኛ መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስመልክቶ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ዳይሬክተር፣ የካቲት 27/2011 ዓ/ም ለአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መግለጫ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አስተላለፉዋቸው ከተባሉት ጉዳዮች መካከል የትግራይ ህዝብና መንግስት ጦርነት ለማካሄድ እያደረጉት ካለው ቅስቀሳና ዝግጅት እንዲቆጠቡ የሚል ማስጠንቀቅያ አዘል መልእክት ተሰራጭቷል፡፡

ነገር ግን የትግራይ ህዝብና መንግስት የጦርነት አስከፊነት ስለሚረዱ፣ ዋነኛ አጀንዳቸው የሆነው ሰላም ማስፈን፣ ዲሞክራሲ ማስፋትና መልካም አስተዳደር ማንገስ እንዲሁም ፈጣንና ሁሉም በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት ልማት ለማረጋገጥ በመታተር ላይ ናቸው፡፡ የትግራይ ህዝብና መንግስት በ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ወቅት፣ ወታደራዊ ፋሽሽት ደርግ ለመደምሰስ በተደረገው መራራ ትግል፣ የአማራ ህዝብ፣ ከወንድሙ የትግራይ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ተገቢው መስዋእትነት ከፍሏል፡፡ በመሆኑም የትግራይ ህዝብና መንግስት የታገሉለትን ህዝባዊ መሰመር አንግበዉ ወደፊት ከመገስገስ ዉጭ በወንድም የአማራ ህዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞርበት አንዳች ምክንያት የላቸዉም፡፡

በመሆኑም የትግራይ ህዝብና መንግስት ባለፉት ዓመታት፣ በተለያዩ ችግሮች የባከኑባቸውን ጊዚያት ለማካካስ፣ ሁለመናቸው ያቀዱት የዲሞክራሲና የትራንስፎርመሽን ዕቅድ ለማሳካት በመሯሯጥ ላይ ናቸው፡፡ በተያያዝነው የበጋ ወቅትም ቢሆን አፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራት በማሳለጥ ለ2011/2012 የክረምት ስራ ቅድመ ዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

ይልቅኑም ማነው በግላጭ ትንኮሳና የጦርነት አታሞ ሲጎስም የከረመው የሚል ጥያቄ ቢነሳ፣ ምላሹ ሰላም ወዳድ ዜጋ ምስክርነት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ሽፍቶች ጨምሮ የተለያዩ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ሃይሎች የተለያዩ የሚድያ አማራጮችን ተጠቅመው፣ ላለፉት ሶስት ዓመታት፣ ያለእረፍት ቀንና ለሊት የጦርነት ቅስቀሳና ቱንኮሳ ከማካሄድ አልፎው፣ በትግራይ ወሰኖች ሄድ መለስ ሲሉ ቆይተዋል፡፡

ትላንት የትግራይ ክልል ብሄር ተወላጆች ብቻ በመሆናቸው በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በድንጋይ ተቀጥቅጦው ሲገደሉ፣ ከ50 ሺ በላይ ዜጎች ጥረው ግረው ያፈሩት ሃብትና ንብረታቸዉ ተዘርፈው፣ እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዮ ሲፈናቀሉ፣ እንዲሁም የአማራና የትግራይ ህዝብ እንዳይገናኙ አውራ መንገዶችን ዘግቶ ባይሳከለትም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲሻክር የተፍጨረጨረዉ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ሃይሉ ታሪክ ይቅር የማይለው በደልና ክህደት ፈፅሟል፡፡

በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብና መንግስት ነጋ ጠባ ከፅንፈኛ ሃይሎች የሚወረወርባቸዉ የቃላት ጦርነትና ትንኮሳ ከልክ በላይ ያለፈ ቢሆንም፣ ጦርነት ለየትኛውም ወገን እንደማይጠቅም አሳምረዉ ስለምያዉቁ፣ እስከ አሁን ድረስ ትዕግስትን መርጧል። ይህንን እውነታ ንፁህ ህሊና ያለው ፍጡር የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ይህ ያደረጉበት ምክንያት ከዋነኛ የሰላምና የልማት አጀንዳቸው ላለመራቅ ነው፡፡ ስለሆነም ትላንትም ሆነ ዛሬ የትግራይ ህዝብና መንግስት ዋነኛ ጠላት ድህነት ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ጦርነታቸዉ ከድህነት ጋር በመሆኑ ማንኛውም ሰላም ወዳድ ዜጋ ስጋት ሊገባዉ አይገባም፡፡

በአጭሩ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዋነኝነት የአማራና የትግራይ ህዝቦች ሰላም ተረጋግጦ የልማት ተቋዳሽ የሚሆኑት፣ በሃገራችን ሕገ-መንግስት ተከብሮ፣ የሕግ የበላይነት ተረጋግጦ፣ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑ የማይታበል ሓቅ ነው፡፡

ሰለሆነም የአማራ ክልል ም/ቤት 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 12ኛ መደበኛ ጉባኤ በፀጥታ ጉዳዮች አስመልክቶ በትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ አስተላልፎታል የተባለው ዉሳኔ ለአማራም ሆነ ለትግራይ ህዝብ ሰለማይበጅ ጉዳይን ዳግም እንዲያጤነዉ የትግራይ ህዝብና መንግስት ጥሪአቸውን ያቀርባሉ፡፡

ዘልአለማዊ ክብር እንከን ለማይነካቸው የትግሉ ሰማእታት!!

የትግራይ የህዝብ ግንኙነትና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ-ትግራይ
የካቲት 28/06/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ #ሞቃዲሾ ውስጥ ከሶማልያው ፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ከሚገኝ ምግብ ቤት ውጭ ዛሬ የደረሰ የመኪና ቦምብ ፍንዳታ በትንሹ ለ5 ሰዎች ሕይወት መጥፋትና ሌሎች ዘጠኝ መቁሰል ምክንያት መሆኑ ተገለፀ። የጥቃቱን ሰላባዎች ቁጥር ያስታወቁት የደኅንነት ባለሥልጣናትና የዳስላን ምግብ ቤት ባለቤት ናቸው።

#VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሴትነት!

#ሴትነት ሰው የመሆን ሁለንተናነት ነው። አንድ ሰው የሴትነትን ታላቅነት ካልተረዳ ገና #ሰው የመሆንን ሚስጢር አልተገነዘበም ማለት ነው። ምክንያቱም ሴት እናት ነች። እናት ደግሞ የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰን #የፍቅርን ምንነት መገለጫ ናት። ታዲያ ከፍቅርና ፍቅርን ከማወቅ በላይ ምን ታላቅ የህይወት ሚስጢር ይኖራል? ምንም አይኖርም።

ሌላው ታላቅ ከሚያደርጓት ነገሮች ደግሞ በህይወት ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋፍጣ #በብልሃት እና #አሸናፊነት የምትወጣ ጠንካራ ፍጥረትነቷ ነው።

ሩህሩህነትን ከአፍቃሪነት ጋር ታድላ የተፈጠረች ለወንድ የህይወቱ ማገር እና ምሶሶ ናት። ወንድ ያለ ሴት ሙሉነት እና የህይወት ጣእም የሌለው ያላለቀ የእግዜር ጅምር ስራ ነው።

ሴት ልጅ ስቃይዋን እና ሃዘኗን መደበቅ ካስፈለጋት መከፋትዋን ሳታሳይ ደስተኛ በመምሰል ለምትወደው ሃሴትን መስጠት የምትችል ረቂቅ ፍጠረት ናት።

ሴትነትን ሆነው ካላዩት በእርግጥ ስለ ሴትነት ሙሉ በሙሉ መናገር የሚቻለው አይኖርም። ረቂቅ እና የህይወት ጣእም ሚስጢር አድርጎ ከፈጠራት ፈጣሪ በስተቀር።

ሴት ልጅ ከወንድ የጎን አጠንት ብትሰራም በህይወት ዘመኑ የጀርባ አጥንቱ ሆና ብርታትን እና ፀናትን የምትሰጠው “ሃይል” ናት። የታላላቅ ስኬቱ ጀንበር ሆና የምትፈነጥቅለት ነገር ግን ከእርሱ ልቃ የማትታይ የመድመቂያው ጮራ መፍለቂያ ናት።

ሴት ልጅ ከልብ የመነጨ ክብር ይገባታል። ሴትን የሚያከበር ራሱን #የሚያከብር ነው። ሴትን የማያከብር ቢኖር የህይወትን ጣእም እና ፍቅርን ካለማወቁም በላይ ሰው የመሆን ብቃት የጎደለው ነው።

ምንጭ ፦ ደንቢያ(ከማህበራዊ ድረ ገፅ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር🔝 #ሼር #share @tikvahethiopia @tsegabwolde
የ20/80ና 40/60 #የጋራ_መኖሪያ_ቤት ባለዕድለኞች👉🔝 (TOP) የምትለውን ምልክት በመጫን በPDF በተዘጋጀው ፋይል ላይ የቤታችሁን አይነት፣ የቤታችሁን ቁጥር፣ ህንፃውን፣ የቤታችሁን የወለል ቁጥር እንዲሁም የሳይቱን ስም መመልከት ትችላላችሁ።

•ከ20/80ና ከ40/60 የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች ካሉ ተከታትዬ አሳውቃችኃለሁ።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ቀበሌ 5 በሚባለው አካባቢ ሌሊቱን የእሳት አደጋ ደርሷል፡፡ በአደጋው ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ቤቶች ወድመዋል፤ እሳቱ እስካሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም፤ በቁጥጥር ሥር ግን ውሏል፡፡

በአካባቢው ያሉ ቤቶች የተያያዙ እና በተቀጣጣይ ቁስ የተገነቡ መሆናቸው ለአደጋው መባባስ ምክንያት መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በቃጠሎው በአካባቢው የሚገኘው የፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ሕንጻም መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል፡፡ በአደጋው የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ሰምተናል፤ ትክክለኛ ቁጥራቸውንና የጉዳታቸውን መጠን እያጣራን ነው፡፡

የእሳት አደጋው የዓይን ምሥክሮች እንዳሉት በግምት ከሌሊቱ 7- 8፡00 ጀምሯል፤ ምክንያቱን ግን አላወቁትም፡፡ አሁንም እሳቱን ወጣቶች ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ነው፤ እንዳይዛመት መቆጣጠር ቢችልም ሙሉ በሙሉ ግን አለመጥፋቱን ተሰምቷል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በተዘጋጀው የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ክብረ በዓል ታድመዋል። ሴቶች የሀገር መሠረት ናቸው ያሉት ጠ/ሚሩ ለመሥዋዕትነታቸውና ለስጦታቸው ግን የሚገባቸውን ያህል ዕውቅና አልተሰጣቸውም ብለዋል። በመቀጠልም ጠ/ሚሩ የኢትዮጵያ ጀግና ሴቶች ማንኛውም ዓይነት ልዩነቶች ሳይበግሯቸው በሀገራዊ ሰላምና አንድነት ላይ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

#PMOEthiopia #InternationalWomensDay
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ። የአማራ ክልል ምክር ቤት እያደረገ ባለው ስብሰባ ጥያቄው ተቀብሏል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር አምባቸው መኮንን ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ዕጩ ሆኑ፡፡ ዶክተር አምባቸው መኮንን ሲሳይ ደግሞ በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለመሆን በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia