TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በዛሬው እለት ለ4ኛ ጊዜ ከተሽከርካሪ ፍሰት የጸዱ መንገዶች ቀን በአዲስ አበባ በደመቀ መልኩ ተከብሮ ውሏል፡፡ መንገድ ለሰው በሚል መሪ ቃል በየወሩ መጨረሻ የሚካሄደው ከተሽከርካሪ ፍሰት የጸዱ መንገዶች ቀን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር #አሚር_አማንን ጨምሮ የተለያዩ ባለሥልጣናትና የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ የተለያየ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የተካሄዱ ሲሆን የተለያዩ የጤና ምርመራዎቸም ተደርገዋል፡፡

Via AfriHealth
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 11...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የተገኙበት የህወሃት 44ኛ ዐመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ #ኢንተር_ኮንትኔንታል ሆቴል እየተከበረ ይገኛል። #በድምፂ_ወያነ እና #በትግራይ_ቲቪ በቀጥታ እየተላለፈ ስለመሚገኘ መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ🔝

"#ኤርሚ የጉዞ አድዋ ተጓዥ #በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል። #Adwa123 #አድዋ123"

"ኤርሚ ካስተላለፈው መልክት ኢትዮጵያን አናውቃትም በFB እንደምናየው አይደለም እኔ ያየዋት ኢትዮጵያ ፍፁም ፍቅር የሆኑ ህዝቦች ያሉበት ሀገር ናት።"

Via Shinshaw(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
OMN🔝

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ 5ተኛ አመት #የምስረታ_በዓሉን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት እያከበረ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ🔝

የሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር የግጭት አፈታትና የሰላም ባህል ግንባታን ላይ በጋራ ለመስራት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሲሳይ_ሸዋአማረ አማካኝነት የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የሰላም ባህልን ማሳደግና የሚፈጠሩና የተፈጠሩ #ግጭቶችን መፍታት አንዱ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራችን ነው ያሉት ዶ/ር ሲሳይ ግጭቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናትና የመፍትሔ ሀሳቦችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት በማቅረብ ለዘላቂ መፍትሄ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንንም ዩኒቨርሲቲው በሰላም ባህል ግንባታ ላይ አለመግባባቶችን በሰላማዊና ዴሞክራሲያው መንገድ ለመፍታት የሚችል ማኅበረሰብ መፍጠር የሁሉም ምሁራን ድርሻ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የሰላም ሚኒስቴር
©ዳንኤል መኮንን(ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia