TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በደሴ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይዎት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። በአማራ ክልል ደሴ ከተማ #በሳላይሽ ክፍለ ከተማ ዛሬ ከረፋዱ 2:00 አካባቢ ነው አደጋው የደረሰው።

በከተማው በአስፓልት መንገድ ላይ ኳስ ሲጫወቱ የነበሩ ሶስት ወጣቶች ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 11 491 FSR የጭነት መኪና ባደረሰው ግጭት ህይዎታቸው አልፏል።

በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር #ሙሃመድ_አበጋዝ ለአብመድ እንደተናገሩት የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው።

ህብረተሰቡ ልጆቹ በመንገድ ላይ እንዳይጫወቱ በማድረግ የመኪና አደጋዎች እንዳይፈጠሩ መከላከል እንዳለበትም ኮማንደር ሙሃመድ መክረዋል፡፡ አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉንም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Adwa123 #አድዋ123

"አድዋ የሙዚቃ ፌስቲቫል"-በመስቀል አደባባይ የተዘጋጀውን ይህን #የሙዚቃ_ፌስቲቫል በOBN ቴሌቪዥን #በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንጅባራ🔝

123ኛው የዓድዋ ድል #እንጅባራ ላይ ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የተገኙት አባት አርበኞች #ወጣቱ ትውልድ ጀግኖች አባቶችና እናቶች ለሃገር ሉዓላዊነት የከፈሉትን መስዋዕትነት በማሰብ ለሀገር አንድነት ዘብ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኢትዮጵያውያን #ለነፃነታቸው በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በፆታ ሳይለያዩ እንደሚቆሙ ዓድዋ ህያው ምስክር ነች›› ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ ደብዳቤ🔝

ከላይ የምትመለከቱት ደብዳቤ በአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) ስም በሀሰት የተዘጋጀ ደብዳቤ እንደሆነ ፓርቲው ገልጿል።

@tsegabwilde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ገዱ አንድ አርጋቸው ጋር በመሆን የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክን በታሪካዊው የአድዋ ድል ቀን በጋራ መርቀው ከፈቱ። የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ1,100 ሜት ካሬ መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን 8 የማምረቻ ዛኒጋባዎች አሉት። ይህ የጋራ ምርቃት የምሥራቅ አፍሪካን የጥምረት እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያጠናክር ሲሆን ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች ጋር ተመሳሳይ የፕሮጀክት ምርቃቶች የሚከናወኑ ይሆናል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የአድዋ ድል ክብረ በዓልና የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ወቅት ባደረጉት ንግግር ሁላችንም ፍቅር ሰላምና አንድነት ላይ እናተኩር ብለዋል። በወቅቱም መንግስት በሚቀጥሉት አመታት የሚተገብራቸው አቅጣጫዎች ያሏቸውን ስድስት የአስተዳደር ምሰሶዎች ያስተዋወቁ ሲሆን እነሱም፤ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ብልፅግና፣ ብሄራዊ አንድነት፣ ፍትህና ብሄራዊ ኩራት ሲሆኑ ይህም የህዝቦችን ተቻችሎ መኖርና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን የለውጥ አመራር በማድነቅ ለምስራቅ አፍሪካ ውህደት ራእይ የኬንያን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia