TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

አርቲስት #አሚር_ዳውድ ከለሊቱ #8_ሰዓት ገደማ በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። የአርቲስቱን ህልፈትም የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር #ሀጎስ_ጎደፋይ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አረጋግጠዋል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጎት ቫለርስትሮም ጋር ዛሬ አገኝተው አነጋገሩ። በዚሁ ወቅትም በኢትዮ ስዊዲን ትብብር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፥ ቫለርስትሮም ስዊዲን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በድጋሜ ማረጋጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀገር ማለት ሰው ነው፤ ሰው ማለት ሀገር ነው፡፡ አባቶች በደም ዋጋ በአደራ የሰጡኝን ምድር በንፅህና ጠብቃለው፡፡ ነገ በገርጂ ታክሲ ተራ ልዩ አረንጓዴ አድዋ ፅዳት ዘመቻ በሴፍ ላይት የወጣቶች ንቅናቄ ከዓለም ጋለሪና ከወረዳ 13 ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያደርጋል፡፡ ልክ ጠዋት 1:00 በአለም ጋለሪ እንገናኝ፡፡ አደዋ የእኔ የስራ ወኔ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበበ የስራ ፍቃዳቸዉን ባላሳደሱ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ #እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበበ ከተማ ዉስጥ በ2011 የንግድ ፍቃዳቸዉን ማሳደስ የሚጠበቅባቸው 251 ሺ 6 መቶ የንግድ ተቋማት ቢኖሩም፣ ፍቃዳቸዉን እስከ ታህሳስ 30፣2011 ዓ.ም ድረስ ማደስ የቻሉት ግን ከ218ሺ አይበልጡም ተብሏል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️

ሁለት ታዋቂ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ትናንት ምሽት በሞት የተለዩት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎቹ #ጌታቸው_ደባልቄ እና #አሚር_ዳውድ ናቸው፡፡

አቶ ጌታቸው ደባልቄ ለረጅም ዓመታት በጸሐፊ ተውኔት እና በአዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡ በ83 አመታቸው ያረፉት የአንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሞያ የቀብር ስነ ስርአት ነገ ይፈጸማል ተብሏል፡፡

በትግርኛ ዘፈኖቹ የሚታወቀው አርቲስት አሚር ዳውድ ትናንት ምሽት በመቐለ አይደር ሆስፒታል ነው ያረፈው፡፡ አርቲስቱ የግጥምና የዜማ ደራሲ ሲሆን፥ በተለይም አይሞቱም ጀጋኑና በሚለው ሙዚቃው ይታወቃል። በአርቲስቱ ህልፈት የትግራይ ክልል መንግስት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል። ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ቆይታ ያደርጋሉ። ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮ ኬንያ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እየተሳተፉ ይገኛል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia