TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ ከሶማሊ ላንድ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር ተወያይቷል። በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ በሶማሊ ላንድ ጉብኝት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው ከአስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው የተወያዩት።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ #ነገ የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 21/2011 ዓ.ም

በወላይታ ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት፦

በወላይታ ዞን በተለይም በሶዶ ከተማ ህግን የማስከበርና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የዞኑ አስተዳደር እና የሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በወቅታዊ የሶዶ ከተማ ፀጥታ ዙሪያ ለአካባቢው ሚዲያዎች ትናንት ማምሻውን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንዳሉት የወላይታ ሶዶ ከተማ ሰባት የመግቢያና መውጫ በር ያላት፣ በፈጣን ዕድገት ውስጥ የሚትገኝ ከተማ በመሆኗ በርካታ ግለሰቦች በከተማዋ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ግንባታ በማከናወን የቤት ባለቤት ለመሆን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በሰኔ 8/2010 ዓ.ም በከተማው የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ መነሻ በማድረግ የህግ የበላይነት የማይከበርበት ከተማ አድርጎ በመቁጠር በርካታ ግለሰቦች ህገወጥ ግንባታ ፈጽመዋል ብለዋል፡፡

በተለይም በቅርቡ ወደ ከተማ የተካለሉ ቀበሌያት ላይ እየተፈጸመ ያለው ህገወጥ ቤቶች ግንባታ አሳሳቢ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከህገወጥ ድርጊቶች ሊቆጠብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በህገወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን ለማፍረስና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በወሰኑት ውሳኔ እና በየቀበሌው በህገወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶች መፍረስ እንዳለባቸው ህዝቡ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እርምጃው እየተወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፐክተር ጥበቡ ዳዊት እንደገለጹት በሀገራችን እየመጣ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገው ውይይት በከተማው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ተችሏል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ እጅግ በጣም ሰፊ፣ የንግድ ማዕከል እና በፍጥነት እያደገች የሚትገኝ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ደላሎች ህብረተሰቡን በማታለልና የቀበሌ አመራሮችም ጭምር እንዲሳተፉ በማድረግ በከተማው ክልል በርካታ ህገወጥ ግንባታ እንዲካሄድ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

እነዚህን በህገ ወጥ መንገድ ቤቶችን የገነቡ ግለሰቦች በግብረ ኃይል ከመፍረስ አስቀድመው በራሳቸው ፈቃድ እንዲያፈርሱ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በመሠራቱ በርካቶች በራሳቸው ፈቃድ ማፍረሳቸውን ኢንስፐክተሩ አስታውቀዋል፡፡

ባልፈረሱ ህገ ወጥ ቤቶችን ለማፍረስ ግብረ-ኃይሉ ሲሄድ አንዳንድ ግለሰቦች ሁከት ለመፍጠርና መንገድ ለመዝጋት ሙከራ አድርገዋል ብለዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ ባደረገው ጥረት በከተማው በ3 ቀበሌያት ብቻ ከ518 በላይ ህገወጥ ቤቶች መፍረሳቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት በከተማው ውስጥ ሁምቦ ላሬና ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ አንድ ግለሰብ በህገወጥ መንገድ የገነባውን የራሱን ቆርቆሮ ቤት በራሱ ፈቃድ ለማፍረስ ከወጣበት በድንገት ወድቆ በሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ ህይወቱ አልፏል ብለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ አንዳንድ ግለሰቦች ፖሊስ በጥይት ተኩሶ ገድሏል በማለት የተሳሳተ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው በከተማው አዲሱ መናኻሪያ አከባቢ አሮጌ ጎማ በማቃጠል ሁከት እንዲፈጠር ሙከራ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

የተፈጠረው ሁከት በፀጥታ አካላትና በህብረተሰቡ ትብብር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሳያመራ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢንስፐክተር ጥበቡ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በሶዶ ከተማ የህግ የበላይነትን የማስከበርና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ በህገ ወጥ መንገድ የተሰማሩ ጥቂት ግለሰቦች በሚፈጥሩት ሁከት ሊቆም እንደማይችል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና የከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገበታ ለሸገር...

በሚከተለው የባንክ አካውንት የ”ገበታ ለሸገር” ተሳትፎዎን ያረጋግጡ።

👉 1000275826317

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ምሽቱን #በሞቃዲሾ ህዝብ በሚበዛበት ቦታ በተፈፀመ #የቦንብ_ጥቃት በትንሹ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ። ለጥቃቱ #አልሸባብ የተባለው የሽብር ቡድን #ሀላፊነት መውሰዱ ነው የተሰማው።

ፎቶ፦ Harun Maruf
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሩብ ሚሊዮን የምንልቅ የTIKVAH-ETHIOPIA (@tikvahethiopia) ቤተሰብ አባላት ከቅዳሜ ጀምሮ ለ1 ሳምንት ከፌስቡክ #ልንርቅ ነው።

ይህን የምናደርገው ፌስቡክ በኢትዮጵያ፦
•የስድብ እና የጥላቻ መድረክ
•የሀሰት መረጃ መፈብረኪያ
•የጦርነት መቀስቀሻ
•የክፋት እና ተንኮል መጠንሰሻ
•ህዝብ መከፋፈያ
•ደም ማፋሰሻ
•በብሄር ተቧድኖ መሰዳደቢያ
•ሀገር ማተራመሻ
•ሰላም ማደፍረሻ....የማህበራዊ ሚዲያ እየሆነ በመምጣቱ ነው። እየያን ያለነው ሁኔታም #ስላሰጋን እና #ስላሳሰበን ጭምር ከፌስቡክ ራሳችንን ለማግለል #ወስነናል። እንዲሁም ለሀገራችን እና ለአእምሮአችን #ሰላም ስንል 1 ሳምንት ከፌስቡክ #እንርቃለን!

•በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት በእውቀት እና በብስለት ያልዳበረው የፌስቡክ #አጠቃቀማችን ሀገሪቱን የለየለት ቀውስ ውስጥ ከመክተቱ በፊት አንዳች መፍትሄ ቢፈልግለት መልካም ነው።

ዝርዝር ጉዳዮችን እንነጋገራለን!

እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስነው በሺዎች ከሚቆጠሩ የቻናላችን አባላት ጋር ለሁለት ቀን በውስጥ መስመር ከተወያየን በኃላ ነው!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

አርቲስት #አሚር_ዳውድ ከለሊቱ #8_ሰዓት ገደማ በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። የአርቲስቱን ህልፈትም የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር #ሀጎስ_ጎደፋይ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አረጋግጠዋል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia