TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት መምህራን ስልጠና ሲሰጥ ሰንብቷል።

ከመስከረም 3/2015 ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት ለ1200 መምህራን ነው ስልጠና የተሰጠው።

ነገር ግን ስልጠና በተለያዩ የግል ምክኒያቶች ያልወሰዱ መምህራን የማስተማር መብት የላቸውም መባሉን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ዉስጥ ገብተዋል።

ስልጠናዉን " በጤና በቤተሰብና በከባባድ ማህበራዊ ምክኒያቶች መካፈል አልቻልንም " የሚሉ አካላት ገና ካሁኑ በተለይ የግል ትምህርት ቤቶች " ስልጠናዉን ያልወሰዱ አካላት በትምህርት መምሪያ በኩል ወደስራ አይገቡም የሚል አቅጣጫ ተሰጥቶናል " በማለታቸዉ ከፍተኛ ቅሬታና ድንጋጤ ዉስጥ ገብተዋል።

በመሆኑም የከተማዉ ትምህርት መምሪያ ችግራችን ተረድቶ መፍትሄ ይፈልግልን ሲሉ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ላለፉት አስር ቀናት የሰለጠኑ መምህራንን የእዉቅናና የምስክር ወረቀት በተሰጠበት ወቅት የሲዳማ ክልል ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ተክሉ አዳላ ባስተላለፉት መልእክት ፤ እንደሀገር የተጀመረዉን የትምህርት ችግር ቀርፎ ዉጤታማ ለመሆን እንዲህ ያለዉ  ስልጠና የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ዙር ስልጠናዉን ያልወሰዱ መምህራንን ጉዳይ በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያነሳንላቸዉ የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት ልማት አመራር ዳይሬክተር አቶ አዳነ አብርሀም በበኩላቸዉ ፤ የዚህን ዙር ያልተካፈሉ መምህራን በቀጣይ በሚዘጋጀዉ ስልጠና አንደሚካተቱ በመግለጽ ስልጠናዉን ያልወሰዱ መምህራን ያሏቸዉ ትምህርት ቤቶችም ለትምህርት መምሪያዉ ሪፖርት በማድረግ መምህራን እየሰሩ የሚሰለጥኑበት መንገድ ማመቻቼት እንደሚቻል ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ ዉስጥ ያለዉ ህገወጥ እንቅስቃሴ ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር ሆኖ በሰራዉ ስራ ከፍተኛ ለዉጥ ቢታይም አሁንም ችግሮች መኖራቸዉ ተገለጸ።

በከተማዉ ባሉ የታክሲ መሳፈሪያና መዉረጃ አካባቢዎች የስልክ ነጠቃና ስርቆት እንዳማረራቸዉ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ በዚህ መልክ የተዘረፉ ስልኮች በገበያ ዉስጥ በግልጽ ሲሸጡ እንደሚታይ ይናገራሉ።

አሁን ላይ የተሰረቁ ስልኮችን በግልጽ በከተማዉ ዉስጥ ባሉ የገበያ መግቢያዎች ሲሸጡ እንደሚታይ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ይህ ጉዳይ ሀይ ሊባል እንደሚገባ በመግለፅ የሚመለከተዉ አካል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ የሰጠዉ  የከተማዉ ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታዎችን ለማስተካከል በአዲስ አደረጃጀትና ተልእኮ ከተማዋን የተሻለ ሰላም ያላት ለማድረግ  እንደሚሰራ  ገልጿል።

በቅርቡ ወደስልጣን የመጡት የሀዋሳ ከተማ ጸጥታ ጉዳይ ሀላፊዉ አቶ ወንድሙ ቶርባ ሁኔታዉን ለማስተካከል ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን በከተማዉ ነዋሪ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጉት ዉይይት ገልጸዋል።

ይህ የማህበረሰብና የፖሊስ የትብብር አንቅስቃሴና ስምሪት  በደመራ በአል በስፋት የተስተዋለ ሲሆን ወጣቶችና ፖሊስ በመቀናጀት ዉጤታማ ስራ ሲሰሩ መታየታቸዉን በቦታው የሚገኙ የቲኪቫህ ቤተሰቦች ተመልክተዋል።

@tikvahethiopia
#Sidama #Hawassa #Motor

በሀዋሳ ከተማ ከሞተር ሳይክል የታርጋ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ክፍል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በአንፃሩ የሞተር ባለቤቶች ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ ታርጋ የላቹም ብሎ ያሳድደናል " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

አንዳንዶች ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ክልል  ታርጋ ወደ ሲዳማ ታርጋ መቀየር አለበት በሚል የመያዝና የማንገላታት ነገርም አለ ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ፤ ህብረተሰቡ ህጋዊ  ታርጋ በማዉጣት ህጋዊ ይሆን ዘንድ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር ተስፋዬ አክለውም፤ " የደቡብ ታርጋ አየተያዘ ነዉ " የሚባለዉ #ስህተት መሆኑን በመግለጽ ማንም በነጻነት ማሽከርከር እንደሚችል ገልጸዋል።

" በዚህ ምክንያት የታሰሩ ሞተሮች ካሉ ስህተት ነው፤ ይለቀቃሉ። የደቡብ ክልል ታርጋ እስካልሸጠ እስካለወጠ ድረስ ችግር የለውም " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ከአዲስ ታርጋ ጋር በተያያዘ በጹሑፍ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ አባላት ታርጋ የላቹም ብለው ያሳድዱናል። እኔ በግሌ 2% ግብር ከከፈልኩ ወራቶች ተቆጥረዋል ነገር ግን ታርጋ ማግኘት አልቻልኩም የሚመለከተው አካል መፍትኤ ይስጠን፤ ትራፊክ ፓሊስ አባላት እያንገላቱን ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ይህንን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዳንቾ ችግሩ መኖሩን በማመን ችግሩ ከሀገራዊ የዶላር ችግር ጋር ተያይዞ የመጣ (ለታርጋ ማሳተሚያ) መሆኑን አንስተዋል።

" አሁን ላይ ህትመቱ በማለቁ በሚቀጥለዉ ሳምንት ይሰጣል " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም፥ ታርጋ ያልደረሳቸዉ አሸከርካሪዎች ሪሲት በማሳየት እንዲንቀሳቀሱ የተያዙትም እንዲለቀቁ ከከተማዉ ትራፊክ ፖሊስ አመራሮች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ ምላሽ  ሰጥተዉናል።

መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Hawassa

" ለአራት ቀን ያለምንም ወንጀል የታሰሩበት ምክንያት በፋጣኝ ምላሽ ይሰጥበት። " - የታሳሪ ቤተሰብ

" በእስር ላይ የሚገኙ አሸከርካሪዎች ከእስር ተለቀዉ ወደ ስራ ይመለሳሉ ፤ ሁሉም ነገር  በህግና በደንብ  እየተመራ ይቀጥላል " -  የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርትና  መንገድ ልማት


ወደ ሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ቅሬታቸዉን ለማቅረብ የተንቀሳቀሱ በርካታ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መታሰራቸዉ ተሰማ።

አንድ የታሳሪ ቤተሰብ ነኝ ያሉ ግለሰብ ፤ " በሀዋሳ ከተማ እለተ አርብ በጠዋት፣ በተለምደው የሺ ከብልስቶን መንገድ በሚባል መንገድ ላይ የባጃጅ ሾፈሮች ከመንገዱ እና ካላቸው የስምሪት ጥያቄ የተነሳ ቅሬታ ለማቅረብ ወደ መንገድ እና ትራሰንፖርት አቅንተው ነበር " ብለዋል።

" እኚሁ የባጃጅ ሹፌሮች ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በሄዱበት በፖሊስ ተከበው ወደ 80 የሚጠጉ የባጃጅ ሾሬሮችን በየክፍለከተማው አስር  አስር እየተደረጉ በፓትሮል ተወስደው ታስረዋል " ያሉት እኚሁ ግለሰብ " ይህ የተፈፀመው አርብ ፣ ቅዳሜ እሁድ እና ሰኞን ጨምሮ ነው " ብለዋል።

" የተሰራ ወንጀልም ይሁን የተሰማ ድምፅም የለም " የሚሉት የታሳሪው ቤተሰብ " የታሰሩት ሰዎች እስካሆን ጉዳያቸውን የሚያነሳ አካልም የለም፣ በምን ጉዳይ ላይ እንደታሰሩም የተሰጠም ማብራሪያም የለም፣  ተዳፍነው እስር ቤት ናቸው " ብለዋል።

" የሲዳማ ክልል ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ይሄን ጉዳይ ያውቀው ይሆን ? " ሲሉ የጠየቁት ግለሰቡ " አይደለም 80 አንድ እስረኛ በ48 ሰዓት ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት ነው ህጋችን። ለአራት ቀን ያለምንም ወንጀል የታሰሩበት ምክንያት በፋጣኝ ምላሽ ይሰጥበት። " ብለዋል።

ይህንን እና በውስጥ የመጡ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ አባል የባጃጅ ሹፌሮችን አነጋግሯል።

ያነጋገራቸው የባጃጅ ሹፌሮች ባጃጆችን ከዋና ዋና መንገዶች የማስወጣት እንቅስቃሴ በከተማዉ ዳርቻም ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ የነዳጅ ፣ የመለዋወጫና የኑሮ ሁኔታዉን ያላገናዘበ ታሪፍና ድንገተኛ ስምሪት እየተጣለብን ነው  ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

ከሰሞኑን ከአቶቴ - ንግስተ ፉራ የነበረዉ ርቀት ድንገት በመቀየሩ የተፈጠረዉን አለመግባባት በዉይይት ለመቅረፍ ወደመንገድ ትራንስፖርት የተመረጡ አሽከርካሪዎች መሄዳቸዉን ተከትሎ ለእስር መዳረጋቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርትና  መንገድ ልማት ምክትል የመምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ ፤ ችግሩ የተከሰተዉ የትራፊክ ፖሊስ የስምሪት ቦታዉን በመለወጣቸዉና አሽከርካሪዎች አዲሱን ርቀት አንቀበልም በማለት በተነሳ ግጭት መሆኑን ጠቅሰዉ  አሁን ላይ ስምሪቱን የከተማዉ መንገድ ትራንስፖርት ብቻ እንደሚሰጥ መተማመን ላይ በመድረሱ ችግሩ ተቀርፏል ብለዋል።

ምክትል ኃላፊዉ ፤ በእስር ላይ የሚገኙ አሸከርካሪዎች ከእስር ተለቀዉ ወደ ስራ እንደሚመለሱ ገልጸው ሁሉም ነገር  በህግና በደንብ  እየተመራ እንደሚቀጥል አስገዝበዋል።

@tikvahethiopia
#Hawassa

" አደጋ ለመከላከል ተብለው የተቀመጡ የፍጥነት መቀነሻዎች ወይም ስፒድ ብሬከሮች ምልክት ስለሌላቸው እራሳቸው የአደጋ መንስኤ እየሆኑ ነው " - ነዋሪዎች

" ችግሩ ጎልቶ የሚታይበትን ዋና መንገድ የሰራዉ የፌደራል መንግስት ነው የፍጥነት መቀነሻዎችን ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክትም ሆነ ከርቀት እንዲታዩ የሚረዳ ቀለም የመቀባት ኃላፊነት አለበት " - የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት  መምሪያ

በሀዋሳ ከተማ ያሉ የፍጥነት መቀነሻዎች ወይም ስፒድ ብሬከሮች የአደጋ መንስኤዎች ሆነዉብናል ሲሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ገለጹ።

በከተማዉ የተለያዩ መንገዶች በተለይም ከተማዉን አልፎ በሚሄደዉ አዉራ ጎዳና ላይ የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቀነስ በርካታ የፍጥነት መቀነሻዎች እንዳሉ ይታወቃል።

ይሁንና እነዚህ መቀነሻዎች ከፍተኛ መጠን ያላቸዉ ከመሆኑ በተጨማሪ ለአካባቢው አዲስ ለሆኑ አሽከርካሪዎች ምልክት አለመቀመጡንና የተለየ ቀለም አለመቀባታቸዉን ተከትሎ ከፍተኛ አደጋ እየፈጠሩ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የከተማዉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት  ምክትል የመምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ በበኩላቸዉ ቅሬታዉን ቀድመዉ እንደሚያዉቁት ገልጸዋል።

ችግሩ ጎልቶ የሚታይበትን ዋና መንገድ የሰራዉ የፌደራል መንግስት መሆኑን በመግለጽ ለተሰሩ የፍጥነት መቀነሻዎችም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክትም ሆነ ከርቀት እንዲታዩ የሚረዳ ቀለም የመቀባት ሀላፊነት ያለበት ራሱ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን መሆኑን ያነሳሉ።

አቶ አበራ አክለዉም አሁን ላይ ችግሩን ለመቅረፍ በቅርቡ ከፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ጋር ዉይይት ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዉ ምናልባትም ሀላፊነቱን የከተማዉ መንገድ ትራንስፖርት መቀበል ከቻለ ማስተካከያዎችን በቅርብ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

መረጃ ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Hawassa

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል።

ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦

" ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር ' መኪና ባስቆሙ በተደራጁ ዘራፊዎች ተዘርፈናል ፤ በመሃል ከተማ በሳንጃም የግድያ ሙከራም ተደርጎብናል። "

👉 የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

" ... ' ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን ' የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሮዬም ሆነ ስልኬ ክፍት ነው። ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም "

👉 የታቦር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

" . . . ተጎጅዎች ' በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል ' የሚሉት የተሳሳተ ነው። በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር ታሪክ የሆነ ጉዳይ ነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል። ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። 👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦ " ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር…
#Hawassa

የራስሰው ገዛኸኝ የተባሉ ግለሰብ ሀዋሳ ላይ የተደራጀ ዝርፊያ እና ሳንጃ በማውጣት የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈው አሰራጭተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ መልዕክት በውስጥ ደርሶት ተመልክቷል። የሀዋሳ ፖሊስንም ስለጉዳዩ ደውሎ ጠይቋል።

" በሀዋሳ ከተማ ላይ የተደራጀ የዝርፊያ እና የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብናል " ያሉት የራሰው ገዛኸኝ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ መሰረት ፦

- ድርጊቱ የተፈፀመው ሀዋሳ፣ በተለምዶ ከአቶቴ ወደ ፉራ በሚወስደው መንገድ " ቦሌ መንደር " አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ መብራት ጋር ነው።

- ቀኑ 12/04/2016 ዕለተ #አርብ ከምሽቱ 12:30 ላይ ነው።

- ሲያሽከረክሩት የነበረው ላንድ ሮቨር መኪና ሲሆን ውስጥ እንግዶቻቸው ከሆኑ 3 የመንግስት አካላት ጋር ሆነው ሲጓዙ ነበር።

- በተለምዶ " ቦሌ መንገደር  " የትራፊክ መብራቱ ጋር ሲደርሱ የሚያሽከረክሩት መኪና ከጎን በኩል በከፍተኛ ምት ይመታባቸዋል። አደጋ ያደረሱ ስለመሰላቸው መኪናውን ዳር በማስያዝ ያቆማሉ።

- በመኪናው ውስጥ ከነበሩት አንዱ ከመኪና ፈጥነው በመውረድ የተመታውን መኪና ዙሪያውን ቢመለከቱም የደረሰ አደጋ የለም። ግን ሰዎች ተሰብስበዋል።

- የወረደው ሰው ከመኪናው ኃላ የተሰበሰቡ ወጣቶች የደረሰውን ግጭት ምንነት እየጠየቃቸው በነበረበት ወቅት የራስሰው ገዛኸኝም ከመኪናቸው ወርደው ወደ ወጣቶቹ በመሄድ ምን ተፈጠረ ? ማለት ጥያቄ ይጀምራሉ።

- በዚህ ሁኔታ አስፓልቱ ዳር ከሚገኝ 2 ፑል ቤት አንድ ግሮሰሪ ተጨማሪ ወጣቶች ወጥተው ከበባ ያደርጋሉ፤ ወዲያው አንድ ወጣት በተለምዶ በአከባቢው አጠራር " ባንጋ " የተባለ የሚጠራውን ሳንጃ ይዞ ማሳደድ ይጀምራል።

- በተፈጠረው ሁኔታው #ተደናገጠው ቢያፈገፍጉም ወጣቱ ሊተዋቸው ባለመቻሉ ወደ መኪናው ለመግባት ሲሞክሩ እዛው ጋር የነበሩት ሌሎች ወጣቶች በሩን እንዳይገቡ ይይዙታል።

- ሁኔታው በተደራጀ መልኩ #ዘረፋ መሆኑ ስለገባቸው በሳንጃው ላለመወጋት ይሸሻሉ።

- በዚህ መካከል ከመኪና ውስጥ ያልወረዱት ሰዎች መኪናውን ሎክ ለማድረግ ቢሞክሩም ሌሎች ወጣቶች ከኃላ በር በመክፈት፦
* ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣ
* ከአንድ ፕሮግራም ቀረፃ እየተመለሱ በመሆኑ ብላክ ማጂክ ካሜራ ፣
* መቅረፀ ድምፅ የያዘ ቦርሳ ይዘው ተሰውረዋል።

- አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ዘራፊዎቹ ከአከባቢው መሰወራቸውን ተመልክተው " ስፍራውን ቶሎ ለቃችሁ ካልሄዳችሁ አሁን ከመጡ #ይገሏችኋል " በማለት አከባቢውን ለቀው እንዲሸሹ ያስፈራሯቸዋል።

- በተጠና ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ኦፕሬሽን በመሆኑ ከአከባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው የፓሊስ አካል እስኪመጣ ጠበቁ።

- በዚህ መካከል አንድ የፓሊስ አባል ይመጣል። ቀርቦ ምንድነው ? ሲል ይጠይቃል። እነሱም የደረሰባቸውን የዘረፋ ወንጀልና የግድያ ሙከራ አስረድተው የህግ ከለላ ቢጠይቁም። ፓሊሱ " በቃ አሁን ከዚህ ሂዱ ልጆቹ ከላልታወቁ ምን ማድረግ ይቻላል ? " በማለት መልሷል።

- የፖሊስ አባሉ ቢያንስ እንኳን #ፓትሮል ደውሎ ኃይል እንዲያስጨምርላቸው ቢነግሩትም ፤ " እኔ የናንተ ጠባቂም ተላላኪም አይደለሁም " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።

- ወደ አንድ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ዘንድ ደውለውም እንዲደርሱላቸው ፤  የደረሰባቸውን በደል ቢያስረዱም ከባለስልጣኑ ዘንድ ምንም አይነት እርዳታ አላገኙም።

- ወደ ተለያዩ የህግ አካላት በመደወል #ከ40_ደቂቃ በኃላ አንድ የፓሊስ ፓትሮል ሊመጣ ችሏል።

- የመጡት የፖሊስ አባላት ችግሩን ለመስማት የሞከሩ ሲሆን " የዘራፊዎችን ማንነት እና ስም " ከተፈራፊዎች ይጠይቃሉ። እነሱም መንገደኛ በመሆናቸው ገልጸው የዘራፊዎቹን ማንነት በስምና በአድራሻ ለይቶ ለፓሊስ መናገር የሚችሉበት መንገድ ስላልገባቸው ቢያንስ የተወሱ ወጣቶች የወጡበትን ግሮሰሪ እና ፑል ቤት አሳዩ።

- ከፍተኛ #ክርክር እና አለመግባባት ከተፈጠረ በኃላ የፖሊስ አባላቱ የተፈፀመውን ነገር የዕለት መዝገብ ላይ እንዲያስመዘግቡ በማለት ወደ ታቦር ክፍለ ከተማ ፓሊስ ማዘዣ ጣቢያ እንዲሄዱ አድርገዋል።

- ፖሊስ " የፑል ቤቱ ባለቤቶች  " አንዳንድ ነገር ሲናገሩ በመስማታቸው አስረዋቸዋል። ነገር ግን ዋናዎቹ የተደራጁትን የዘራፊ ቡድኖች የያዘም ሆነ በወቅቱ ለመከታተል የሞከረ አካል የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መልዕክት ከተመለከተ በኃላ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ፤ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ አሁን ላይ በከተማዋ ዉስጥ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች በጅጉ የተሻለ ሰላም ያላት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ጠቅሰዋል።

ተፈፅሟል የተባለውን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ ሲያዩት #ማዘናቸዉን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ ችግር ተፈጥሮ ከሆነ በተዋረድ ለሚመለከተዉ አካል ማቅረብ እንደሚቻልና በተለይ እንዲህ ያለዉን ጉዳይ እንኳን ፖሊስ የትኛዉም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ከማስቆም ወደኋላ እንደማይል ገለጸዋል።

አሁንም " ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን " የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሯቸዉም ሆነ ስልካቸዉ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተጎጅዎች እንዲያመለክቱና ቃላቸውን እንዲሰጡ የተደረጉበትን የታቦር ክ/ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን አነጋግሯል።

እሳቸው በሰጡት ምላሽ በወቅቱ መኪናችን ተመታብን ያሉት አካላት ወደፖሊስ ጣቢያዉ በመምጣት ባስመዘገቡት መሰረት በአካባቢዉ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ተይዘዉ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢ/ር ወንድዬ ፤ የተጠቀሱት ንብረቶች መሰረቃቸዉን በወቅቱ አለመስማታቸውን እና አለመመዝገባቸዉን አስታውሰዉ አሁንም ቢሆን ጉዳዩን በአግባቡ ወደሚመለከተዉ የህግ አካል በማቅረብ በተያዘዉ ምርመራ እንዲካተት ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ተጎጅዎች " በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል " የሚሉት የተሳሳተ መሆኑን የሚያነሱት ኢንስፔክተሩ በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር #ታሪክ_የሆነ ጉዳይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#Hawassa

" . . . ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ አይችልም ፤ እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት ይችላል " - የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ

" ጉዳዩ በውስጣዊ አሰራር ህግና ደንብ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ነው። " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

" ... ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብዬ እየጠበኩ ነው። " - ኢኒስፔክተር ተስፋዬ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱት የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ማስተባበሪያ ኃላፊዉ ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ደምሴ ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ ታግደዋል።

ይህ በተመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬን እና ጉዳዩ ይመለከታቸው ያላቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት አድግጓል።

ከሰሞኑ የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ በተለቀቀዉ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ነጻና ገለልተኛ ሁኖ ማህበረሰቡን የሚያገለግለዉን የፖሊስ ንብረት በግላቸዉ ለሚከተሉት ሀይማኖታዊ አገልግሎት በማዋላቸዉ ምክኒያት ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ መታገዳቸዉ ይገልጻል።

በወቅቱ ስብሰባዉን የመሩት የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ባስተላለፉት መልእክት ፤ ማንም አካል በመንግስት ንብረት የግል ፍላጎቱን ማራመድ እንደማይችልና እንዲህ አይነት ፍላጎት ያለዉ አካል ስልጣኑን ለቆ ፍላጎቱን ማሳካት እንደሚችል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጰያ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቀዉ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩ በዉስጣዊ አሰራር ህግና ደንባቸዉ መሰረት ተይዞ በሂደት ላይ ያለ መሆኑን አሳውቋል።

ይሁንና ከሰሞኑ በነበረዉ ስብሰባ ወቅት የተነሳዉን የኢንስፔክተር ተስፋዬን ከስራ መታገድ በተመለከተ ለጊዜዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ስለሁኔታው ምን ምላሽ እንዳላቸው በስልክ ጠይቋቸው " ኢየሱስ ይመጣል የሚለዉን መልእክት ባስተላለፍኩበት ወቅት እንዳያችሁት በተፈጠረዉ ሁኔታ ከስራ ታግጃለሁ ፤ ለጊዜዉ በሌለሁበት ከስራ እንድታገድ ወስነዉብኛል። " ብለዋል።

" ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ ብዬ እየጠበኩ ነው እግዚያብሄር መልካም ነዉ " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Hawassa

በፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በፆታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት አበባየሁ ጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ውሳኔው የከተማውን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ስለታሰበ ነው መፍትሄ ያገኘው ብለዋል።

አበባየሁ ጌታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

-  ሚዲያ ላይ ባለመውጣታቸው ብዙ ተሸፋፍነው የቀሩ የጠለፋ ወንጀሎች በከተማው አሉ።

-  ይህ ውጤት የተገኘው በተለያዩ መንገዶች በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ከፍተኛ ትኩረት ስላገኘ ነው።

-  ጉዳዩ አነጋጋሪ የሆነው የከንቲባው የግል ጠባቂ ከመሆኑ፣ የመንግስትን ንብረት ተጠቅሞ በመሆኑ በከተማው ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለነበረው ነው ይህ ጉዳይ እልባት ያገኘው።

-  ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተጠርጣሪው በተከሰሰባቸው ሁለት ወንጀሎች ማለትም በጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ ተብሏል።

- በመቀጠል ታህሳስ 08 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ላይ ከሁለቱም ወገኖች የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ እንዲያቀርቡ ተደርጎ ነበር።

-  በዛሬው እለት ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ተሰጥቷል።

ባለሙያው በአጠቃላይ ፆታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ምን አሉ ?

* ወደሐዋሳ አካባቢ መሰል ችግሮችን በሽምግልና መፍታት እና ከባህል ጋር የማያያዝ አዝማሚያ አስቸጋሪ ነው። እንደዚህ አይነት ነገሮች በሽምግልና መፈታት የለባቸውም።

* የህግ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ የማይጮኹ ጉዳዮችንም ትኩረት አለመስጠት እና ተባባሪ አለመሆንም መስተካከል ይገባዋል።

* በትምህርት፣ በስልጠና እና በመሰል አስተማሪ ቅጣቶች ለፆታዊ ጥቃቶች ትኩረት መስጠት ይገባል።

የዳሸን ባንክ ሰራተኛ እንዲሁም የአላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችው ፀጋ በላቸው ፤ ግንቦት 15 ቀን 2015 ከስራ ስትወጣ በወቅቱ የከተማው ከንቲባ የግል ጠባቂ በነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም የተባለ ግለሰብ በመኪና ታግታ መወሰዷና አድራሻዋም ሳይታወቅ ለቀናት መቆየቱ የሚታወስ ነው።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በወቅቱ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከፀጥታ ሀይል ለማምለጥ ሲል በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ እና ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው ከነበሩ አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና ሽጉጥ ጋር  ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. መያዙን የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቆ ነበር።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Hawassa #ጤና

በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ " ፓነሲያ ሆስፒታል " 2,094 የሀሞት ከረጢት ጠጠር በቀዶ ህክምና ከአንዲት 40 ዓመት ሴት በሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት በዶ/ር ፀጋዬ ቸቦና በስራ ባልደረቦቻቸው የቀዶ ህክምና ቡድን አማካኝነት ወጥቷል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት ዶ/ር ፀጋዬ ፤ ይህ በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በቁጥር ብዛት የመጀመሪያ የሆነና እስከዛሬ ያልተመዘገበ ከ2,094 በላይ ቁጥር ያለው የሀሞት ከረጢት ጠጠር (Symptomatic Multiple Cholelithiasis) ነው ብለዋል።

ቀዶ ህክምናው 2 ሰዓታት ከ30 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ መቻሉን አስረድተዋል።

የሀሞት ከረጢት ጠጠሮቹ በቀዶ ህክምና ቡድን የተቆጠሩ ሲሆን ጠጠሮቹን ለመቁጠር ከ45 ደቂቃ በላይ መፍጀቱን ዶ/ር ፀጋዬ ገልጸዋል።

የ40 ዓመት እድሜ ያላት ታካሚዋ ለ3 ዓመታት የቆየ በአብዘኛው ጊዜ ቅባታማ ምግቦችን ከተመገቡ በሗላ የሚከሰት ለረጅም ሰዓታት የሚቆይ ፦
- የሆድ የላይኛው ቀኝ ክፍል የመውጋትና የማቃጠል ህመም ፣
- ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች ፣
- የቀኝ ትከሻ እና የጀርባ ህመም ስለነበራቸው ነው ወደ ሆስፒታሉ ያቀናችው።

አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገላት በኃላ ነው የሀሞት ከረጢት ጠጠር (Symptomatic Cholelithiasis) እንዳለባቸው በመታወቁ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት የተነገራት።

የቀዶ ህክምናው ውስብስብነት ላይ ውይይት ከተደረገና በቂ መረጃ ከተሰጣቸው በኋላ ተጨማሪ ስምምነት ፈርመው ነው ቀዶ ህክምናውን ለማደረግ የወሰኑት።

የታካሚዋ ቀዶ ህክምና ከባድና ውስብስብ ያደረገው ምንድነው ?

* በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ሶስት ጊዜ (3x) የእንቅርት ዕጢ/ካንሰር ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው መሆኑ
* ከቀዶ ህክምናው በሗላ በታካሚዋ ላይ የነበረባቸው ተጓዳኝ የጉሮሮ ነርቭ  ጉዳት ፤
* የድምፅ ለውጥ/የድምፅ ኃይል መቀነስ እና አልፎ አልፎ የነበረባቸው የአተነፋፈስ ችግሮች የድህረ- ቀዶ ህክምናው ፅኑ እንክብካቤ እና እርዳታ ውስብስብ አድርጎታል።

ምንም እንኳን ቀዶ ህክምናው ታካሚዋ በነበረባቸው  ተጓዳኝ ችግሮች ውስብስብ ቢሆንም በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ቡድን ቅንጅት ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

🔹በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳይንሳዊ መጽሔቶች እና ምርምር ሪፖርቶች ላይ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው የሀሞት ከረጢት ጠጠር በህንድ በሪከርድነት ተይዞ ይገኛል።

🔹በአፍሪካ ጆርናሎችና ሳይንሳዊ ወረቀቶች ወስጥ በዚህ ደረጃ ብዛት ያላቸው የሀሞት ከረጢት ጠጠር ተመዝግቦ አልተገኘም። እስካሁን ባሉ መረጃዎች በኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ጆርናሎች ላይ 146 የሃሞት ጠጠር ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቦ ይገኛል።

በፓነሲያ ሆስፒታል-ሀዋሳ በቀዶ ህክምና የወጣዉ ከ2,094 በላይ ብዛት ያለው የሀሞት ከረጢት ጠጠር በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በቁጥር ብዛት በሳይንሳዊ መጽሔቶች እና ምርምር ወረቀት ሪፖርቶች ላይ አዲስ ሪከርድ ሆኖ ሊመዘገብ የሚችል መሆኑን ዶ/ር ፀጋዬ ቸቦ ተናግረዋል።

ለጥንቃቄ . . .

በአብዘኛው ጊዜ ቅባታማ ምግቦችን ከተመገቡ በሗላ የምከሰት ለረጅም ሰዓት የሚቆይ የሆድ ህመም ካላ ፦
☑️ በሆድ የላይኛው ቀኝ ክፍል ድንገተኛ የመውጋትና የማቃጠል ህመም ፣
☑️ በቀኝ ትከሻ ላይና በትከሻ መሳቢያዎች መካከል የጀርባ ህመም፣
☑️ የሆድ መነፋት ስሜት እና ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች ካሳየና ካለዎት ፤ ይህ የሀሞት ከረጢት ጠጠር ህመም (Symptomatic Cholelithiasis) ምልክት ሊሆን ስለምችል ባፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ማቅናት ያስፈልጋል።

@tikvahethiopia