TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በደባርቅ ከተማ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና እንደማይሰጥ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።4ኛው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዲራዘም ለመጠየቅ የተጠራው ሰልፍ በነገው ዕለት እንደሚደረግ አዘጋጅ የሰ/ጎንደር ዞን አማራ ወጣቶች ህብረት አስታውቆ ነበር።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኔ ትውልድ ኮንሰርት‼️

የሮፍናን የኔ ትውልድ የሙዚቃ ኮንሰርት በር ላይ ከፍተኛ #መጉላላትን አስከተለ። በዲጂታል መልክ የትኬት ስያጭ የተከናወነው የሮፍናን የሙዚቃ ኮንሰርት #በኔትዎርክ ችግር ምክንያት ትልቅ #መጉላላትን አስከትሏል። ትኬቱን ቆርጠው የሙዚቃ ዝግጅቱን ለመከታተል ወደ ጊዮን ሆቴል የተጓዙት ከ4ሺ በላይ የሚሆኑ የፎፍናን አድናቂዎች ከፍተኛ በመስተጓለ እየደረሰባቸው ይገኛል። የፅጥታ ሃይልም ጊዮን ሆቴል መግባት ባልቻለው ታዳሚው ላይ ድብደባ #እየፈፀመ ይገኛል። ሮፍናን ምሽት 2 ሰዓት ስራዎቹን ለማቅረብ የታቀደ ቢሆንም ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ መድረክ ላይ #አልወጣም

Via ዳሰሳ አዲስ
ፎቶ፦Danny(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ...

"ፀግሽ ከሮፍናን ኮንሰርት እየተመለስኩ ነው። ቦታ ሞልቷል ብለው #አባረሩን። በጣም #ያሳዝናል!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግሮች‼️

#በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮች እና ቅስቀሳዎች ለብዙዎች ሞት፤ ለበርካቶች መፈናቀል እና ለዘመናት የተገመዱ ማኅበራዊ ትስስሮች መላላትን ንብረት መውደም ምክንያት መሆናቸው በከፍተኛ መጠን ማደግ ምክንያት መሆናቸው ተነገረ።

በብሄር አደረጃጀት የተዋቀረው የሃገሪቱ የፖለቲካ ስርአተ ማህበር የችግሩ ዋነኛ ምንጭ በመሆኑ የህግ ማእቀፎችን ከማውጣት በላይ መዋቅሩ ላይ መስራት እንደሚገባም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ስለ ጥላቻ ንግግር ምንነ፤ #የጥላቻ_ንግግር በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ እንዴት ይታያል፤ የማኅራዊ ሚዲያ መስፋት አጠቃቀም እና የጥላቻ ንግግር አዝማሚያዎች ምን ይመስላሉ? በሚሉ እና ከማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምጋር በተገናኙ ያሉ ክፍተቶችን ለመዳሰስ ዛሬ ውይይት ተደርጓል።

ብሄርን እንደ #አቀጣጣይ ነገር መጠቀም፤ ከዚህ በፊት ተበድያለሁ የሚል ስሜት ማደግ እና የማኅበራዊ መገናኛዎችን በስፋት የመጠቀም ባህል እያደገ መምጣት ችግሩን ተቆጣጣሪ አልባ እያደረገው መሆኑም በውይይቱ ተዳስሷል፡፡

የብሄር ማንነትን እንደ ስነልቦናና ማህበራዊ ወሳኝ እሴት በማየት ቋንቋ የሚጎለብበት፤ ባህል የሚዳብርበትና ታሪክ ጥበቃ የሚደረግበት ተቋማዊ ቅርጽ መፍጠር ለችግሩ መቃለል እንደመፍትሄ ተቀምቷል በውይይቱ።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ🔝

#የድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ በሕክምና ሙያና በኪነ ሕንጻ ትምህርቶች በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን 53 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኪነ ሕንጻ በመደበኛ የትምህርት መርሃግብር ለ5 ዓመታት አስተምሮ ካስመረቃቸው 36 የኪነ ሕንጻ ተማሪዎች መካከል 12ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ከኪነ ሕንጻ ተመራቂዎች በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው ለ3ተኛ ጊዜ በሕክምና ዘርፍ ያስተማራቸውን 17 ተማሪዎችንም በሕክምና ዶክተር አስመርቋል፡፡

Via ENA
ፎቶ፦ ena & flagot(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ በሚወሰደው እርምጃ የሚያጋጥሙ ግድፈቶችን የሚያጣራና #እርምት የሚሰጥ ግብረሃይል ወደ ስራ ገብቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአምቦ ከተማ #16ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 12ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል «የባህል ስፖርት ተሳትፎአችን ለሰላምና ለአንድነታችን» በሚል መሪ ቃል በአምቦ ስታዲየም ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ፎቶ፦ Yonas , EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ነው #የግጭት_ትርፉ! ይህን እንኳን አይተን እንማር፤ እኛ ላይ ሲደርስ ደም እንባ ከምናነባ ሁላችንም ለኢትዮጵያ ሀገራችን #ሰላም ዘብ እንቁም!
.
.
#ሰውነት ከብሄር፣ ከዘር፣ ከቀለም ይቅደም!
.
.
ፎቶ ቁጥር 1. #ሶሪያ
ፎቶ ቁጥር 2. #ኢትዮጵያ/የሶርያ ስደተኛ ህፃን-አዲስ አበባ/

#እኔ ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ የምትሉ የቤተሰባችን አባላት ይህቺን🕊የሰላም ምልክት የሆነችን እርግብ ተጫኗት!

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia