TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥቆማ‼️

ስብስቤ ዋሻ-#ባሌ_ዲንሾ_ፓርክ አቅራቢያ ወይም ወደ ዲንሾ በሚወስደው መንገድ ከፍታ ቦታ ላይ #እሳት እንድተነሳ ጥቆማ ደርሶናል። የሚመለከተው አካል ጉዳዩን ይመልከተው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል መንግስት‼️

የአማራ ክልል መንግሥት በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች #የተፈናቀሉ ዜጎችን በሁለት ወራት ውስጥ ወደ ቀያቸው ለመመለሥ እየሠራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ #አሰማኸኝ_አስረስ ተናገሩ፡፡

አቶ አሰማኸኝ እንዳሉት በክልሉ ያሉት አጠቃላይ ተፈናቃዮች ቁጥር 90 ሺህ 736 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 60 ከመቶ አካባቢው ተፈናቃዮች ደግሞ ከማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር የተፈናቀሉ ናቸው፡፡

ተፈናቃዮችን በሁለት ወራት ውስጥ መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሆነም አቶ አሰማኸኝ አስታውቀዋል፡፡

በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር የተቃጠሉ ቤቶችን ለመገንባት ከሚፈለገው የቤት ክዳን ቆርቆሮ 50 ከመቶውን መንግሥት መግዛቱን ያስታወቁት አቶ አሰማኸኝ ቀሪውን መንግሥት ከለጋሽ አካላት እየጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በማዕከላዊ ጎንደር 4 ሺህ 361 ቤቶች እና በምዕራብ ጎንደር 1 ሺህ 500 ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግሥት 5 ሺህ 861 ቤቶችን ገንብቶና መንደር መሥርቶ ዜጎችን ሊያቋቁም መሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

የሚገነቡት ቤቶች እንደ ቤተሰብ ብዛት የሚለያዩ ናቸው፤ አራትና ከዚያ በታች አባላት ላሉት ቤተሰብ ባለ 40 ቆርቆሮ፣ ከአራት በላይ የቤተሰብ አባላት ላሏቸው ደግሞ ባለ 60 ቆርቆሮ ቤት እንደሚገነባ ነው የተናገሩት፡፡

#የመከላከያ_ሠራዊትና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ኃላፊነቱን ወስደው በዞኖቹ እየሠሩ እንደሆነ አስታውቀው ‹‹ከዚህ በኋላ ወንጀለኞችን ለአንድም ደቂቃ ቢሆን አንታገስም›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
በአማራ ክልል ከሚገኙ 90 ሺህ 736 ተፈናቃዮች 25 ከመቶው በመጠለያ ይገኛሉ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በዘመድ ወዳጅ ተጠግተዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ናቸው፡፡

ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል #የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው #ለመመለስም እየተሰራ መሆኑን አቶ አሰማኸኝ አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር ውጤታማ #ምክክር እየተደረገ ነው ብለዋል። አፈጻጸሙም የተፈናቀሉት ወገኖች ጋር መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ የሚተገበር ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ናቸው ተብለው የፈረሱ ቤቶች ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ትናንት ምሽት ድረስ 3,800 ቤቶች ፈርሰዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ቤቶቹ #በሕገወጥ መንገድ የተሰሩ በመሆናቸው የወሰድኩት #እርምጃ ሕግን የማስከበር ሥራ ነው ብሏል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው ከ10 እስከ 19 ዓመት ቤት ገንብተው መኖራቸውን የአፈር ግብር ለመንግሥት እንደሚከፍሉና ውሃና መብራትን ጨምሮ መሰረተ ልማት የከተማ አስተዳደሩ እንዳሟላላቸው ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወቃል፡፡ ነዋሪዎች ቤታችን በመፍረሱ ጎዳና ላይ ወድቀናል የሚል #እሮሮ እያሰሙ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊውን ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ሸገር 102.1 ራድዮ በጉዳዩ ዙሪየ አነጋግሯቸዋል።

Via Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሐይማኖቶች #የሰላም ባለቤቶች ናቸው፡፡ በሀገራችን ሀይማኖት ብቻ ሳይሆኑ የእርስ በርስ የባህል ልውውጥ ማዳበሪያ፣ ችግሮችን #መሻገሪያ ድልድይ ናቸው” የኢትዮጵያ ሐይማኖቶች ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ #ዘሪሁን_ደጉ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ አቶ #ንጉሱ_ጥላሁን እና የኦዲፒ ስራ አስፈፃሚ አባልና የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው አቶ #አዲሱ_አረጋን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሚያ ክልል የስራ ሃላፊዎች በለገጣፎ ጉበኝት እያካሄዱ ነው።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport አሰልጣኝ #ዲዲዬ_ጎሜዝ እና ኢትዮጵያ ቡና ተለያዩ፡፡ በኢትዮጵያ ቡና ያልተሳካ የውድድር አመትን በማሳለፋቸው ከደጋፊዎች ተቃውሞ የበረከተባቸው አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ ቀሪ የሁለት አመት ኮንትራት እየቀራቸው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር መለያያታቸው ተሰምቷል፡፡

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቬንዙዌላ ድንበሯን ዘጋች‼️

የቬንዙዌላ ፕሬዘዳንት #ኒኮላስ_ማዱሮ #በሰብዓዊነት ስም በተቃዋሚ ፓርቲዎች አማካኝነት ከአሜሪካ የሚደረገውን እርዳታ ለማስቆም አገራቸው #ከብራዚል ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷን አስታወቁ፡፡

በዚህ ምክንያትም በርካታ ተሽከርካሪዎች በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ ቆመው እንዳሉም ተገልጿል።

ፕሬዘዳንቱ በአገራቸው ከመንግስት አቅም በላይ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሌለና ምንም አይነት የእርዳታ ጥሪም እንዳልተደረገ ገልፀዋል፡፡

በአገሪቱ በተፈጠረው #አለመረጋጋት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ግራ ዘመሙ መሪ #ማዱሮ በአገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ ወጥተው እንደገለፁት የተቃዋሚ መሪዎች በሰብዓዊ እርዳታ ስም ከአሜሪካና ሌሎች አጋሮቿ የሚላከውን ለማስቆም የኮሎንቢያ ድንበርንም ጨምረው እንደሚዘጉ ገልፀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ጁዓን ገይዱ በበርካታ አውቶቡሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ታጅቦ ከቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ ወደ #ኮሎንቢያ ድንበር ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት‼️

በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት #ተጠናክሮ መቀጠሉን የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር #ሂሩት_ወልደማርያም ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሠላማዊው የመማር ማስተማር ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከዚህ ቀደም ችግሮች ይስተዋሉባቸው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉባቸውን ችግሮች አመራሮቻቸው የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ለመፍታት ተሞክሯል ብለዋል።

ተማሪዎችም የእረፍት ጊዜ እንዲወስዱ በማድረግም ችግሮቹን ለማርገብ መሰራቱን ገልጸው፤ ሠላሙን ዘላቂ ለማድረግም የተማሪዎች አመለካከት ላይ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹን ሊያነቃቁ የሚችሉ ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ ውይይቶችም በተለይም ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጎን ለጎንም በአመለካከተ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ድራማና ሌሎች የጥበብ ሥራዎችም በስፋት እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎች ከኅብረተሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ለማድረግም የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑም መደረጉን ሚኒስትሯ አስረድተዋል።

ይህም ደግሞ ተማሪዎች ዓላማቸውን በደንብ አጥብቀው እንዲይዙ በማድረግ በየትኛውም ኃይል ተጠልፈው እንዳይወድቁ ለማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 45 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሚክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ወቅታዊ #ሀገራዊና #ክልላዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም የድርጅትንና የመንግስት ተግባራትን #በአርባምንጭ ከተማ ላይ እየገመገመ ይገኛል፡፡ የደኢህዴን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከየካቲት 12/2011 አስከ የካቲት 14/2011 ዓ.ም ድረስ በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እና የድርጅትና የመንግስት አፈፃፀሞች ላይ የመከረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በተመሳሳይ አጀንዳዎች ላይ #እየተወያየ ይገኛል፡፡

Via SEPDM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ50 አመት በፊት በሃገሪቱ በነበረ አፋኝ ስርዓት ምክንያት ሃገር ለቆ የወጣው #የአፍረን_ቀሎ የባህል ሙዚቃ ቡድን አሁን በሀገሪቱ በመጣው ለውጥ ወደ ሃገሩ መመለሱ ይታወሳል፡፡ በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች ዝግጅቶቻቸውን ሲያቀርቡ የየቆዩት የቡድኑ አባላት የካቲት 17/2011 #በሀረር_ከተማ በመገኘት የተለያዩ ሙዚቃዊ ዝግጅቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ለዝግጅቱ የተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን በኮሚቴው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አሰተባባሪ የሆኑት አቶ #ቡሽራ_አሊዪ ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ #የሴቶችን_ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ በሙሉ በሴቶች #የሚመራ በረራ ወደ ኖርዌይ #ኦስሎ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia