TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ሃይልና በአየር የታገዘ የፖሊስ ቡድን እሰከማቋቋም የደረሰ የአደረጃጀት ማስተካከያ አደረገ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሸው_ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ የኮሚሸኑ ተቋማዊ ሪፎርም ሂደት እና የደረሰበትን ደረጃ አብራርተዋል።

የሰው ሃይል፣ ቴክኖለጂ፣ ስልጠና፣ ሎጅስቲክስ እና ከባለደርሻ አካላት ጋር የሚኖር ግንኙነት ላይ መሰረት ያደረገው #ሪፎርም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በረፎርሙ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አሰፋፈር እና አደረጃጀት #መከለሱን እንዲሁም በአራት አቅጣጫ በአራት ክላስትሮች እንዲከፋፈል መደረጉን ነው የገለፁት። ክላስተሮቹም፥ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምእራብ እና ማእከላዊ ክላስተር ናቸው።

በሪፎርሙ መሰረት የከተማ ልዩ የፌደራል ፖሊስ ሃይል እና #በአየር የታገዘ ክትትል ለማድረግም የፌራል ፖሊስ የአየር ሃይል ክንፍ ( AIR WING ) #ይደራጃልም ብለዋል ኮምሽነር ጀነራሉ።

የጦር መሳሪያ ትጥቅን በተመለከተም የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ እና ልዩ ሃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች ምን አይነት መሳሪያ ሊታጠቁ ይገባል የሚለውን የሚመልስ አዋጅ በመዘጋጀት ላይ ነው።

የሪፎርሙ አካል የሆነ የምርመራ ስርኣትን በሚመለከትም የምርመራ ማንዋል ተዘጋጅቶ በቅርቡ ወደ ትግባራ እንደሚገባ ተነግሯል።

#ፌዴራል_ፖሊስ ካሁን ቀደም ከምርመራ ጋር የተያያዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ካሜራ የተገጠመላቸው፣ በመስታውት የተከለሉ፣ ሶስተኛ ወገን ምርመራውን መከታተል የሚችልባቸው የምርመራ ክፍሎች መዘጋጀታቸውም በመግለጫው ተነስቷል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀዩንዳይ ሞተር ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለስራ ጉብኝት #ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ የከፈተውን የሀዩንዳይ መኪኖች መገጣጠሚያ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ይከፍታሉ።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል~ሀዋሳ🔝

"ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር!" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ የተካሄከው ሰለማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ ላይ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ፦ “ህገ መንግስቱ እንዲከበር፤ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ እንዲሰጠው፤ የሪፈረንደም ቀን በአስቸኳይ ተወስኖ ለህዝብ እንዲነገር ጠይቀዋል።

በሰልፉ ላይ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፦

•ሲዳማነት ከሌለ #ኢትዮጵያዊነት የለም!

•ለውጡን እንደግፋለን!

•በኮሚሽን የሚመለስ ጥያቄ የለንም!

•ለማንም ዘረኛ የማንበረከክ በባህላችን የምንኮራ ህዝን ነን!

•ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር!

•የሪፈረንደም ቀን #ተቆርጦ ይነገረን!

•የሲዳማ ህዝብ መንግስትን እንዳከበረ መንግስትም የሲዳማን ህዝብ ያክብር!

•ሁሉንም #ብሄር እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•ሁሉንም #ሀይማኖት እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•የሁሉንም #ባህል እንወዳለን፤ እናከብራለን! የሚሉት ይገኙበታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም እየተመለሱ ነው~ሀዋሳ!!

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ ላይ ለመካፈል ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ ሰልፈኞች ወደየመጡበት #በሰላም በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅግጅጋ🔝

በስምንተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ራስን በማስተዋወቅ #ተሸላሚዎች

ከ20ሺህ በታች የህዝብ ቁጥር ያላቸው ከተሞች (ምድብ አራት)፦

1ኛ:- ዱከም ከተማ
2ኛ:- ወራቤ ከተማ
3ኛ:- ሱሉልታ ከተማ

20ሺህ እና በላይ ህዝብ ባላቸው ከተሞች (ምድብ ሶስት)፦

1ኛ:- ፍቼ ከተማ
2ኛ:- ከሚሴ ከተማ
3ኛ:- ሞጆ ከተማ

በምድብ ሁለት በULGDP 2 የታቀፉ 26 ከተሞች ውስጥ፦

1ኛ:- ሰበታ ከተማ
2ኛ:- አሰላ ከተማ
3ኛ:- ሆሳዕና ከተማ

በምድብ አንድ ULGDP 1 የታቀፉ 18 ከተሞች ውስጥ፦

1ኛ:- ሀዋሳ ከተማ
2ኛ:- ሻሸመኔ ከተማ
3ኛ:- አዳማ ከተማ ተሸላሚዎች ሆነዋል።

Via ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ #የዘጠነኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አዘጋጅ ሆና ተመረጠች። ከየካቲት 9-14/2011 በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ሲካሄድ የቆየው ስምንተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። በማጠናቀቂያው የቀጣዩ ፎረም አዘጋጅ ለመሆን 12 ከተሞች ባቀረቡት ፕሮፖዛል መሠረት ለውድድር ቀርበው የነበረ መሆኑ በመድረኩ በአወዳዳሪ ኮሚቴው ተነግሯል። ከቀረቡ 12 ከተሞችም በሰነድ ጥራት፣ በከተሞች ሳቢነት፣ ፎረሙን ለማዘጋጀት ባለ ብቃት፣ ከመሠረተ ልማትና ሌሎች መስፈርቶች መለኪያነት በሶስተኛነት ወላይታ ሶዶ ከተማ እንዲሁም በሁለተኛ እጩነት ጅማ ከተማ እጩ የነበሩ ሲሆን በአንደኛነት የአሶሳ ከተማ ተርጣለች ተብሏል። የአሶሳ ከተማ ከንቲባም ከጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ የፎረሙን አርማ ተረክበዋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ~ድሬዳዋ ቅርንጫፍ‼️

በሕገ-ወጥ መንገድ ከድሬዳዋ ተጭኖ ወደ ሐርጌሌ ሊጓጓዝ የነበረ ነዳጅና አምስት #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ አቶ #ሞገስ_አያሌው ለኢዜአ እንዳመለከቱት ከከተማው ሊወጣ ሲል የተያዘው 20ሺህ ሊትር ናፍጣ፣ 16 ጀሪካን የሞተር ዘይትና በድርጊቱ የተጠረጠሩት ግለሰቦች ናቸው፡፡ በተለይ ነዳጁ የተያዘው በአንድ የጭነት መኪና ከነተሳቢው በጄሪካን ተጭኖ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ነዳጁን በከተማው ከሚገኝ አንድ ነዳጅ ማደያ ገዝተው ሊያጓጓዙ የነበሩት ግለሰብና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ለግለሰቡ  ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ መሰጠቱ አግባብ  አለመሆኑን ያስረዱት ባለሙያው፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ነዳጅን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚከናወነውን እንቅስቃሴ በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም ሕገ-ወጥ ተግባር ለፖሊስ በማሳወቅ ትብብሩን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ነዳጁ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ጥቆማ ከሰጡት አንዱ ለኢ ዜ አ  እንዳስታወቁት በከተማዋ #የነዳጅ_እጥረት የሚከሰተው በሕገ ወጥ መንገድ በሚካሄደው ንግድ ነው፡፡ ”የቤንዚኑ ችግር ሳይፈታ ናፍጣ ቢወደድ ሌላ ችግር ስለሚፈጥር ጉዳዩን ጠርጥረን ለፖሊስ አሳውቀናል። ትብብራችንም ይቀጥላል”ብሏል፡፡

#ሐርጌሌ በሶማሌ ክልል ከድሬዳዋ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ መንገድ ሊጓዝ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ይቀይራል የተባለለት የወንዝ ዳርቻዎችን መልሶ የማልማት ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ይደረጋል። ፕሮጀክቱ 29 ቢሊዮን ብር ወጭ ይጠይቃል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...እንኳን በአገር ውስጥ ያለ ይቅርና በውጭ አገር #በወንጀል የተጠረጠረ ካለ ይዘን እናቀርባለን"~ጄነራል #እንደሻው_ጣሰው
.
.
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እስካሁን ድረስ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦች ቢዘገይም ነፃ እንደማይሆኑ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንደሻው_ጣሰው ሐሙስ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በኮሚሽኑ መሥሪያ ቤት በሰጡት መግለጫ፣ የእስር ትዕዛዝ ለወጣባቸው ግለሰቦች ትዕዛዙን ለማድረስ ሲኬድ ያጋጠሙ ችግሮች እንደነበሩ በመግለጽ፣ በእንደዚህ ዓይነት ወቅት መታኮስ አስፈላጊ ስላልነበር የተለያዩ አማራጮች ላይ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹አንዳንድ ጉዳዮች በመደበኛ የፖሊስ ሥራዎች ብቻ የሚፈቱ አይደሉም፡፡ የተለያዩ ቦታዎች ሔደው #የተደበቁ ሰዎች አሉ፡፡ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው በኋላም የእስር ማዘዣውን ቦታው ድረስ ሄዶ ለመስጠት ሲሞከር ያጋጠሙ #እንቅፋቶች አሉ፡፡ በዚህ ወቅት አትታኮስም፡፡ ሁኔታው አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ በጥሞና እንዲታይ ይደረጋል፡፡ ይኼ #ለሰላም_ሲባል ነው፡፡ ይኼ የሚደረገው አጠቃላይ ነገር እንዳይበላሽና እንዳይደፈርስ ሲባል ነው፡፡ ይኼ ማለት ግን ሄዶ ሄዶ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ሰዎች #ነፃ ይወጣሉ ማለት አይደለም፡፡ እንኳን በአገር ውስጥ ያለ ይቅርና በውጭ አገር በወንጀል የተጠረጠረ ካለ ይዘን እናቀርባለን፤›› ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ይኼንንም ለማስፈጸም ከተለያዩ ክልሎች ጋር አስተዳደራዊ ውይይቶች እንደተደረጉ በማስታወቅ፣ ‹‹ጉዳዮቹ ጊዜ ተሰጥቷቸው የክልል መንግሥታትም የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ይደረጋል፤›› ብለዋል፡፡

ይሁንና በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ይዘው የሚያስረክቡ ክልሎች እንዳሉም ያወሱት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፣ በተቃራኒው የሚደብቅ፣ የሚሸሽግና አካባቢዬ ላይ ተጠርጣሪው የለም ብሎ የሚያብር ሰው መልካም ተሞክሮ እንዳልሆነ፣ ብሎም የተጀመረውን ለውጥ የሚያናጋና የሚያበላሽ እንዲሁም የወንጀል መከላከል ሥራ ላይም ጥላ የሚያጠላ ጉዳይ ስለሆነ #በሚታረምበት መንገድ #ይታረማል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ማራቶን ሞተርስ ኢንጀኒነሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ያስገነባው #የሃንዳይ_መኪና የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ዛሬ ተመረቀ። ግማሽ ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ የተደረገበት የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካው #በአዲስ_አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ነው የተገነባው።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia