TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UpdateSport የ20 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ #ሳሙኤል_ተፈራ በበርሚንግሐም የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰን አሻሻለ። ሳሙኤል ውድድሩን በ3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ላለፉት 22 አመታት አይነኬ ሆኖ የቆየው እና በሞሮኳዊው ሒሻም ኤል ጎሩዥ ተይዞ የነበረው ክብረ-ወሰን 3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ18 ማይክሮሰከንድ ነበር። ባለፈው ሳምንት ክብረ-ወሰኑን ለማሻሻል 0.01 ሰከንድ ብቻ ሲቀረው ውድድሩን ያጠናቀቀው ሌላው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ዮሚፍ በዚህ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰንን የማሻሻል ዕቅድ ነበረው። የአውስትራሊያው ስቴዋርት ማክስዌይን ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል። ሳሙኤል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ "ይኸን ማመን አልችልም። በውጤቱ ተደስቻለሁ። የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት መሆን የተለየ ስሜት ይፈጥራል" ሲል ተናግሯል።

via dw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በየቤታችን እንወያይ! የዚህች ሀገር ችግር ተመዞ አያልቅም። ከእናተው ጋር ሆኜ ብዙ እየሰማው እና እያየሁ እንደመዋሌ ላለፉት 3 ዓመታትም በየቀኑ እዚሁ ከናተው ጋር መረጃዎችን ስቀባበል ስውል እንደተረዳሁት ትልቁ ችግራችን ስለሰው ክቡርነት በሀገራችን ብዙ ስራ አልተሰራም። ዛሬ ዝርፊያው፣ ማሳደዱ፣ መግደሉ፤ ማፈናቀሉ...የምንሰማቸው ዘግናኝ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ሁሉ ሰው ምን ምንድነው የሚለውን በጥልቀት…
ከቡሌ ሆራ...

"እኔ እንደማስበው ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ሁሉም ሰው ለአዕምሮው ሰላም የሚሰጠውን ተግባር መለየት አለበት። አዕምሯች ሰላም የሚያገኘው ሌሎች ላይ መጥፎ በማድረግ ነው ብለን ካሰብን አብደናል። በሌሎች ስቃይ ህሊናችን ደስታ የሚያገኝ ከመሠለን ልክ አደለንም። አዕምሯችን ሰላም የሚያገኘው ለሰወች መልካም በማድረግ እንጂ ሰወችን እያናከስንና ህሊናቸው ላይ መርዘኛ አስተሳሰብ በመተው እንዳልሆነ ማወቅ አለብን። ሁሉም ሰው ያለፈውን ጥሩም መጥፎም ተሪክ በበጎ ከመነዘርነው ሰላማችን በእጃችን ናት። ያኔ ኢትዮጵያ ውስጣቸው ሰላም ያላቸው ሰዎች የሚኖሩባት ሀገር ትሆናለች። ሰላም የሚጀምረው ከራስ ነው። ወርቅነህ ነኝ ከቡሌ ሆራ። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...

"ወንድሞቼ ከላይ ያነሱት ሀሳብ እዳለ ሁኖ የኔ እይታ #ሀይማኖት ተቋማት ላይ በደንብ መሠራት አለበት፡፡ ወጣቶች ሀይማኖቱን በሁለቱም አለም ስኬታማ የሚሆንበትን ጉዳይ ትቶ ዛሬ ገደል የሚከተውን መጤ መንገድ ተከትለናል። በተለይ ወጣቱን ወደ ሀይማኖቱ የማምጣት ስራ ቢሠራ በየቸርቹ፣ በየመስጅዱ ትምህርቱ ከአንድ ሰሞን የዘለለ ቢሆን ባይ ነኝ! ሙሀመድ ከአርባምንጭ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH አባላት በተነሳው የውይይት ርዕስ ላይ እያቀረባችሁት ያለው ሀሳብ ይቀጥል?? እየተከታተላችሁ ነው?? ~~ አይቀጥል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቀለ...

"የሐገር መሠረት ቤተሰብ ነው፡፡ አያትና ቅድመ አያቶቻችን በአንድነት ና በፍቅር ሆነው የኢትዮጵያን እና የጥቁር ህዝቦችን #ነፃነት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው አቀዳጁን፤ እኛ ታዲያ ልጆቻችንን እሕት ወንድሞቻችንን ከቤት እስከ ጎረቤት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ድሮም #አንድ አድርጎ ያስተሳሰረን ውድ ፍቅራችንን ፣ #እሴቶቻችን መንገርና በተግባር ማሳየት ያቅተናል? እኛ የተሳሳተ አስተሳሰብ እንጂ #የሰው_ጠላት_የለንም፤ ሰው በሰውነቱ እኩል ነው ፤ የሃሳብ ልዩነቶቻችንን በሰከነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እየቻልን ጥላቻንና በቀልን በመዝራት ሞትን፣ ውድመትንና መከራን ስለምን እናጭዳለን?? እኛኮ ውድ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጆች ነን፤ እኛኮ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት አርማ ኩራታቸው ነን፤ አባቶቻችን በታላቅ መስዋዕትነት የገነቡትንና ያወረሱንን ድንቅ ታሪካችንን በመገዳደልና በመዘራረፍ ለአለም ሕዝብ #መሳለቂያ መሆን #ያሳፍራል፤ ተው ወገን ይህም ያልፍና ቀጣይ ትውልድ ይታዘበናል...የአገራችን ሰላም በእጃችን ነው አንድም ለማፍረስ አንድም ሰላማችንን ለማስቀጠል፡፡ አሸናፊ ግርማ ከመቖለ ዩኒቨርሲቲ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዳማ...

"እየተጠላላን አንዳችን ለአንዳችን #እየተደማማን መኖር #ይብቃን እባካችሁ ወገኖቼ መጪው ትውልድ ታሪካችንን አንብቦ እንዳይወቅሰን። ወንድም ወንድሙን ገድሎ #መፎከር ይብቃ እስቲ ተያይዘን አብረን እንደግ ሀገራችን በቂያችን ነች ከሀገር የወጡ ወገኖቻችን እኮ ወደው አይደለም ከሰራን ከተለወጥን እነሱም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ቤታችን ይደምቃል። እህቶቻችን እኮ ወደው አይደለም ከሰው ሀገር የሚንከራተቱት ተባብረን ባለመስራታችን እንጂ አበቃሁ! #አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግ! መሀመድ ከአዳማ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሸገር...

"ስር ነቀል የአመለካከት ለውጥ ያስፈልገናል። Radical Attitude Change.. Not just a change...ሁላችንም እጣታችንን እንጠቁማለን አርቲስት፣ አስተማሪ፣ አገር መሪ ምንምን እያልን ምክንያቱም ስህተታችንን መቀበል ስለማንፈልግ #ስኬት ቢሆን ኖሮ እኔ እንል ነበር። ስለዚህ ይህ ሁሉ ችግር የየራሳችን ትንንሽ አስተዋፅዎ ውጤት ነው። ለምሳሌ ቆሻሻን እንይ...የሚጠራቀመውና አላሳልፍ የሚለን የኛው ጥፋት ነው አዋጥተነው። ሁሉም የየራሱን ቆሻሻ በአግባቡ ቢጥል ምንም ክምር ቆሻሻ አይኖርም ነበር። አገራችንን እንዲሁ ናት የእያንዳንዱ ዜጋ ውጤት ናት። ሁላችንም በተሰማራንበት የተሻልን ብትሆን ሁል ጊዜ ቀና ብናስብ "ለራሳችን እንዲደረግልን የምንፈልገውን ማንኛውምን ነገር ለሌላ ሰው ብናደርግ" ውድድራችን ከራሳችን ዕቅድ ጋር ቢሆን እንዴት እንለውጥ ነበር!¡!¡!¡ ኃይለ ገብርኤል ሸገር"

@tsegabwolde @tikvahethiopi
ከድሬዳዋ...

"ለዚህ ሁሉ ቀውስ ምክንያት የሚመስለኝ አንደኛው እና ዋነኛው ስግብግብ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብዛትና ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለራሳቸው ጥቅም መሮጣቸው። ሁለተኛው ዘር ላይ ያተኮረው የፖለቲካ ስርዓታችን እና በዘር ላይ የተመሰረተው ፌደራሊዝም ነው። ሶስተኛው የሃይማኖት ተቋማት ፖለቲካ ውስጥ መግባትና ለህዝብ አለመቆማቸው ነው። ያነሳዋቸው ሶስቱም ሀሳቦች ብዙ ትንታኔ ይወጣቸዋል። ጨመቅ አድርጌ ነው የፃፍኩት። አመሰግናለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ...

"እኛ ኢትዮጵያዊያን በሚያሳዝን ሁኔታ ለሰው ያለን ክብር እየተሸረሸረ ነው። አሁን አሁን ሁሉም ነገር ከብሔር ጋር ተያያዘና #ሰውነት ቦታን አጣ። በሚገርም ሁኔታ አሰፋ መዝገቡ የሚነግረን የትራፊክ አደጋ መረጃ ብቻ ሆኗል ብሔር ሳይለይ ይሄን ያህል #ሰው ሞተ እና ቆሰለን የምንሰማበት። ሌላው ነገር ሁሉ ከብሔር የተገናኘ ሆኗል።
መፍትሔ የሚመስለኝ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወደ ቀልቡ ይመለስ። ድሮ ይወድ የነበረውን ወንድሙን ለምን ጠላሁ ብሎ ይጠይቅ?? ያኔ ወደየቀልቡ ይመለሳል። አማኑኤል ከሐዋሳ ዪኒቨርስቲ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፦

ለሁሉም ነገር መሰራት ያለበት ከአዕምሯችን ነው። መልካም እና ገንቢ ሀሳብ ካልተዘራብን አፍራሽና ጠባብ አስተሳሰብ ይዘን የትም መራመድ አንችልም። የያዝነው ክፉ ሀሳብ ከኛ አልፎ ለሌሎችም እንቅፋት ነውና ነቅለን ጥለን በፍቅር፥በተስፋ እንዲሁም በእምነት ለዚህች ሀገር የግላችንን አበርክቶት እናኑር። ከራስ ቅላችን በላይ እናስብ። ተስፋዬ ፈለቀ @UoG GONDAR"
.
.
ከእኔነት እሳቤ መላቀቅ! አያቶቻችን ለሠሩት ስህተት(ምናልባት ከሰሩ) ይሄን ትውልድ እዳ ከፋይ አለማድረግ። እኛ ብሎ ማሰብ መጀመር ያስፈልገናል። ከሁሉ በፊት ሰው መሆናችንን ማመን። ሕገ መንግስቱን ማሻሻል። ፓርቲዎች ክርክራቸውን ከሕገመንግሥቱ ይልቅ ፖሊሲዎች ላይ ቢያደርጉ መልካም ነው።
.
.
የተሰራን ነገር ማፍረስ እንደመገንባት አይከብድም..ጦርነት ቀላል የሰላም መንገድ ረጅም ነው፡፡... ሁላችንም እንደ መንጋ ሳይሆን እንደ ግለሰብ ቆም ብለን ነገአችንን ማሰብ ካልቻልን ዘመናችንን በሙሉ ከድህነታችን ጋር ተጣብቀን ስንኗፏቀቅ መጃጀታችን ነው..ስለ ጭለማ ማውራት ብርሃን አያመጣም የልዩነት ሃሳቦችን ትተን አንድ የሚያረጉን ነገሮች ላይ ትኩረት ብናረግ ጥሩ ቀን ይመጣል ብዬ አስባለሁ ገና ብዙ የቤት ስራ ያለብን ህዝቦች ነን፡፡ፈጣሪ ሃገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን! ዳዊት ነኝ ከሰላሌ ፍቼ
.
.
አሁን በሀገራችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለቀጣዩ ትውልድም የሚተርፍ መዘዝ ያለው በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው። ብዙ ግዜ እንደተባለው ይህች ሀገር ከቀጣዩ ትውልድ የተዋስናት እንጂ እኛ ብቻ ኖረን ምናልፍባት አይደለችም። ታድያ ዛሬ ፍቅር እና መቻቻልን ያላስተማርናቸው ልጆቻችን እና በእድሜ ታናሾቻችን ነገ ከየት አምጥተው ይኖሩታል? ከሁሉ በላይ ሰውነትን እናስቀድም። ጩኸታችን እና ስብከታችን ሁሉ ስለ ፍቅር ይሁን። ለምን? ምክኒያቱም የነገ ሀገር ተረካቢዎች ከኛ ይማራሉ። መጥፎም ሆነ መልካም ከታላላቆቻቸው ይማራሉ። ጥላቻን አውርሰን ሰላም የሌለው ህይወት እንዲኖሩ አንፍረድባቸው! ልዩ ከሻሽመኔ
.
.
እኔ በበኩሌ ሁሉም ሰው የየራሱን ስራ ቢሰራና ሀላፊነቱን ቢወጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አስባለው። ምክንያቱም ምንም ነገር ከግለሰብ ነው ሚጀምረው። ሁላችንም እሱ ምን አደረገ፤ እነሱ ምን አደረጉ ሳንል እኔ ምን አደረኩኝ ምን ማድረግ አለብኝ ብለን ብናስብና ለስራ ብንነሳ ከኛ ለውጥ ይጀምራል። ስለዚህ ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንወጣ ለስራም እንነሳ። ሔኖክ ነኝ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
.
.
እንደ ሚመስለኝ የአይማኖት አባቶች ትልቅ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል እራሳቸውን ከፖለቲካ አንጃ አውጥተው ስለ ሰላም መስበክ አለባቸው የትኛውም እምነት ግደሉ በድሉ ዝረፉ አይልም ።
የተረሳ ሆኗል ስለሰላም መስበክ ስለ አንድነት ማውራት ችላ ተብሏል ። ወጣቱ የበለጠ ሊሰማ የሚችለው የእምነት አባቶችን ነውና በዚላይ ቢሰራ ባይ ነኝ። ሳብር
.
.
ለዚህ ተጠያቂ ሁላችንም ሁነን ሳለን ለችግሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ለችግሩ ሌላ ባለቤት ፈልገን እጃችን ለመቀሰሰር መጣራችን ይበልጥ አባብሶታል። ሰውን አርክሰን ለሌሎች ነገር የተሻለ ዋጋ ሰጥተናል። ሁላችንም ጥፋቶቻችን እንመን ከዛ ይቅር እንባባል በመቀጠል ተባብረን እንስራ!
.
.
ወንድሞቼ ያነሱት ሀሳብ እንዳለ ሆኖ
በየአካባቢው የምኖር ሰዎች ችግር ወይም ግጭት ሳይባባስ ቶሎ ብለው ወዴ መፍትሄ መሄድ አለበት ላሳስብ እወዳለሁ። ምሳሌ ብንወስድ
በድሮ ጊዜ ነው አንድ ፎቅ ባለ አራት ደረጃ ከላይ በአራተኛው እሳት ይነሳና ይቃጠላል ሥስተኛ እኔ ምን አገባኝ ይላል ከዛን ወደ ሥስተኛው መጣ ይቃጠላል ሁለተኛ ምን አገባኝ ይላል እሱ ጋ እንደዚህው ተቃጣለ አንደኛ ላይ እኔ ምን አገባኝ እያለ ላለው እሱ ጋ መጣ #ምሳሌው እኔ ምን አገባኝ የምንለው ነገር ነገ የከፋ ነገር ያመጣብናል ስለዚህ #ትንሽ #ትልቅ #ተማሪ #ነጋዴ #ሹፈሩ ወዘተ በሀገራችን መስራት አለብን
አመሰግናለሁ :#ፀግሽ
.
.
የመጀመሪያው ጥፋተኛ እኔ ነኝ። ለምን ተጠራጣሪና ስግብግብ ስለሆንኩ። ለምን የምኖረውና የማስበው በተከለልኩበት የማንነት አጥር ውስጥ ስላለው። እስኪ ትጋትን ሲሆን እኔ ድክመትን ሲሆን እነ ሱ ከሚለው ቆልማማ አመለካከት እንላቀቅና" እኛ" በሚለው ተያይዘን እንጒዝ። የሸበበን ብሄር ያነቀን ጎስ ይስቀመጠንን ጎጠኝነት ትተን ከአጥሩ ባሻገር ያለው ሰፊውን የፍቅር ሜዳን እንመልከት። ክፉዎች ሊለያዩን ያጠሩብንን ግንብ ድልድይ እንገንባና ዳግም እንተያይ...የእውነት መሰረቱ መፋቀር ብቻ ነው..ሰውን ለማገልገል እንጂ ለምን ክብርን እሻለው...ትግላችንና ግዴታችን ፍቅር ይኑርበት... ሁሉን ማስተካከል የሚቻለው እርስ በእርስ በመዋደድ ብቻ ነው። ጌታነህ ከመቂ!
.
.
እሺ ወንድሜ፡ ዋናው የአሁኑ ለደረስንበት ውጥቅጥ መጀመሪያ የነበረው ከሁንም ያለው ራስ ወዳድነታችን ነው ፡ የምር እኛ በቀደድነው ቀዳዳ ሌቡች ይገባሉ ሀገርን ለማቃወስ እኛ አሁን ወላሂ መንቃት አለብን የድርጅት ደጋፊ ብቻ መሆን መዘዙ ይህ ነው አሁን ያለንበት ሁኔታ እውነትን እፈልግ ሀሳብ ያሸንፍ ለሀሳብ እድል እንስጠው ፡ አገሬ ኢትዮጲያ ለዘላለም በልጆችሽ ኮርተሽ ትኖራለሽ ፡ በርግጠኝነት እናሳካዋለን ፡ እኔ ባለሁበት ለዚህም ቁርጠኛ መሆኔን እገልፃለሁ፡ ሰላም ፍቅር ለኢትዮጵያ ህዝብ ቸው ፡ ዩኑስ ነኝ ከቡታጅራ
.
.
የሚጋፋ ሃሳብ ወይም የሌላዉን ወገን ህልዉና የሚነካ ንግግሮች እና ዘለፋዎች ከስነ-ስርዓት አልበኝነት የሚመጣ ሲሆን እያንዳንዳችን ሌላዉ ላይ ጣታችንን መቀሰር ትተን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ መክረን መመለስ ባንችል እንኳን ክፉ ከመናገር በመቆጠብ ታላቁን ሰላም እንጋራ፡፡ ኤልያስ፡ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር
.
.
እኔ እንደማስበዉ ከሆነ ለዚሁሉ ችግር ዋንኛው ተጠያቂ ት/ቤቶቻችን ናቸዉ፡ጥላቻን እንድናውቅ እያደረጉን ነው.ከዚ ቀደም የደርግን ስርአት እየተቸ ነበር ያስተማረን ደርግ ምንም ጥሩ ነገር እንዳልሰራ፡አሁንም ቢሆን ያለፈው ስርአት አንተች በጣም ብዙ ጥሩ ነገር አንደሰራም እንወቅ ባይ ነኝ፡ስለዚህ የትምህርት ስርአቱ ላይ መሠራት አለበት።
.
.
ህብረተሰብ የሚለውን ቃል ብንመረምር ህብረት እና ሰብ የሚሉት ቃላት ዉህድ ነው። "ሰብ" የሚለውም መጨረሻው እና ማሰሪያው ነው። ህብረታችን ቁምነገሩ ሰውነታችን ላይ ነው። ስለሆነም የህብረታችን ማሰሪያ የሆነውን "ሰውነት" ወደ ዉስጥ መመልከት ስንችል የምናስተውለው የአፈጣጠራችንን ረቂቅ ጥበብ፣ ሃሳብ ነው። ዘር፣ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ እዚያ ዉስጥ አንዳቸውም ቦታ የላቸውም። ይህንን ስንገነዘብ የሰውን ልጅ ቅድሚያ በሰውነቱ ሲቀጥል በሃሳቡ እናየው ዘንድ እንችላለን።
.
.
ሰላም ሰላም የሀገሬ ህዝቦች ዘር ሳልቆጥር ቀለም ሳለይ ውውድድድ ነውው የማረጋቹ የማይረሳ የአድዋን ድል አስገኝታቹልናልና እና እኔ ምለው ሰላም ለማምጣት እርስ በእርስ ህዝብ ለህዝብ መደማመጥ እና ዘረኝነት አስወግዶ ሁሉንም አንድ የሚያረግ አስተሳሰብ በህዝብ ዘንድ መምጣት አለበት ይህ እንዲመጣ ደሞ የmedia ሺፋን ትልቁን ቦታ ይወስዳል እደዚሁም social midia ዎችም የራሳቸውን አስተዋፅሆ ያደርጋሉ በሰላም ላይ እንደማመጥ እንከባበር ሁሌም ሰላም ከኛ ጋር ናት ድል ሰላም ወዳድ ለሆነው የሀገሬ ህዝብ አቤል ነኝ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን!!

ሀሳባችሁ እንዚህ ላይ ያልተለጠፈ ወዳጆቻችን ሀሳባችሁን በቀጣይ ለሚነሱት የውይይት ርዕሶች የመነሻ ሀሳብ ሆነው ይቀርባሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ TIKVAH-ETH🗓ዛሬ በቴሌግራም ያደረግነው ውይይት በቅርቡ በሁሉም ከተሞች በአካል ተገናኝተን ለምናደርገው ሰፊ ውይይት ስንቅ ይሆነናል። ሁላችሁም በያላችሁበት እየተዘጋጃችሁ! ስንገናኝ ስለሰውነት እንነጋገራለን - አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበን ብቻ እንነጋገርም ሰፈር ውስጥ መንደር ውስጥ እየገባን ስለችግሮቻችን ቁጭ ብለን እንነጋገራለን! ይህን ሀላፊነት የምነወጣው በየአካባቢው የምንገኝ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እንሆናለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ሲኖር ሐገር አለ!
ሰላም ሲኖር ልማት አለ!
ሰላም ሲኖር እድገት አለ!
ሰላም ሲኖር ቤተሰብ አለ!
ሰላም ሲኖር መቻቻል አለ!
መቻቻል ሲኖር መተሳሰብ አለ!
መተሳሳብ ሲኖር መፈቃቀር አለ!

የሰላም ዋናው ምንጭ ከግለሰቦች ነው የሚጀምረው እና ወንድም እህቶቼ ከምንም ነገር በፊት ለሰላም ቅድሚያ እንስጥ እላለሁ። #Afandi_Sufiyan

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ🔝

#የሃዋሳ_ዩንቨርሲቲ የህክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎች 10ኛ ዙር #የምርቃት_ኘሮግራም በአሁን ሰአት በመከናወን ላይ ይገኛል።

©Suleyman&AMED(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia