TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እስቴ🔝

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢና የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ ኢንጅነር ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እና ሃጂ ሱልጣን መሃመድ አማን ዛሬ #በእስቴ በመገኘት መስጊዱ የተቃጠለባቸውን ህብረተሰቦች፣ የንግድ ተቋሞቻቸው የተዘረፈባቸውን ሙስሊሞችን ሱቆች ጎብኝተዋል። ጠዋት ላይም የአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ብርጋዴር ጄነራል #አሳምነውን በጽ/ቤታቸው በመገኘት ስለችግሮቹ ዉይይት ተደርጓል። ህዝበ ሙስሊሙን #በማስተባበር የተቃጠሉትን መስጊዶች እንደሚያሰሩ በመግለፅ የህዝቡን ሞራል በማነሳሳት ተስፋ ሰጥተዋቸዋል።

Via አህመዲን ጀበል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ‼️

#ግምታዊ_ዋጋቸው 300 ሺህ ብር የሆኑ #የምግብ_ዘይት እና የተለያዩ #የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ። ዛሬ የካቲት 08 ቀን 2011 ዓ ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ የሰሌዳ ቁጥራቸው ኮድ 3- 37064 ኦሮ እና 02872 ሐረ የሆኑ ሚኒባስ እና አይሱዙ ጭነት ተሽከርካሪዎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን በመያዝ እና መነሻቸውን ከጅግጅጋ አቅጣጫ በማድረግ ወደ ሐረር ከተማ ሊገቡ ሲሉ ጅግጅጋ እና ሐረር መካከል ቦምባስ በምትገኝ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሚኒባስ ተሸከርካሪ ውስጥ በርካታ የምግብ ዘይት ሲያዙ በአይሱዙ የጭነት ተሸከርካሪ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ልባሽ ጨርቆች ተይዘዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹም ለጊዜው #እንዳመለጡ ታውቋል፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን የፈዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የጉምሩክ ፈታሾች በጋራ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ከገቢዎች ሚኒስቴር የተኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
”ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በዘመናት ሁሉ ያጋጠሙትን የውጭም ሆነ የውስጥ #የሉዓላዊነት_ፈተናዎችን በከፍተኛ ወኔና ቁርጠኝነት የተወጣ፣ የሃገር #መከታና #አለኝታ የሆነ ተቋም ነዉ።” - ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታንዛኒያ የሚገኙ 541 #ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን አገራቸው እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ #ነቢያት_ጌታቸው የጉዞ ሰነድ የተሰጣቸው 541 ኢትዮጵያውያን በመጪዎቹ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት የታንዛኒያ መንግሥት 1900 ኢትዮጵያውያንን ከእስር ለመልቀቅ መወሰኑን አስታውቆ ነበር። አሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተዘጋጅተዋል የተባሉት 541 ኢትዮጵያውያን የታንዛኒያ መንግሥት በምኅረት ከለቀቃቸው መካከል ስለመሆናቸው #የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቀ ሰላም ውይይት ተጀመረ!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ነጋዴ ባሕርና አካባቢው የሚኖሩ #የአማራና #የቅማንት ህዝቦች ተወካዮች የእርቀ ሰላም ውይይት ጀምረዋል፡፡ ውይይቱ ነጋዴ ባሕር ከተማ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ የእርቀ ሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ያደረጉት ከሁለቱም ወገኖች የኃማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ የውይይቱም ዓላማ አሁን ላይ ያለው #አለመግባባት እንዲያበቃና ወደቀደመው መከባበርና አንድነት ለመመለስ ነው፡፡ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት እንደማይጠቅምና ተጎጅዎችም ራሳቸው መሆናቸውን ተወያዮቹ ተናግረዋል፡፡

#ከግጭት ይልቅ የቀደመውን #አንድነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹የጥፋቱ መንስኤ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከሆነ ህግን ተከትሎ መንግስት ሊፈታው ይገባል፤ እኛ ሰላማዊ ነዋሪዎች ነን፤ ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባናል›› ነው ያሉት፡፡ በጥፋቱ የሚጠየቁ ግለሰቦች ካሉም በጋራ ሆነን ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እናደርጋለን ብለዋል ተወያዮቹ፡፡

‹‹መንግስት የሚደርሰው ጥፋት ከተከሰተ በኋላ ነው፤ ስለዚህ ለጥፋቱ የድርሻውን ይውሰድ፤ እኛም ችግሩን ወደ ሌላ ሳንገፋ የድርሻችንን ልንወስድ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ለዘራፊዎች በራቸውን መክፈት ሳይሆን ሰላማቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #አማረ_ገብሩ በውይይቱ ላይ ተገኝተው የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ህይዎትን_ለማትረፍ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ከሌለ ሀገር የለም፤የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚችል መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው አለ፤ ከሕዝብ የምንጠብቀው ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠትና ለችግሮች መፍትሔ መስጠት ነው›› ብለዋል፡፡ ሰራዊቱን ሕዝቡ እንዲደግፈውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#በእርቀ_ሰላም ውይይቱ እንዲሳተፉ ከአካባቢው 16 ቀበሌዎች ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር ተገልጧል፡፡ አብዛኛዎቹ ተሳትፈዋል፤በተለያዩ ምክንያቶች ከሁለቱም ወገኖች ለውይይት ያልተገኙ የቀበሌ ተወካዮችም አሉ፡፡ ሁሉን አቀፍ የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግም ለየካቲት 15/2011 ዓ.ም ሕዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዓረና‼️

በሀገር-ዓቀፍ ደረጃ የተጀመረው #ሪፎርም ወደ ክልሎችም በበቂ ደረጃ እንዲወርድ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ ሉዓላዊነት ፓርቲ ገለፀ፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update በምዕራብ ወለጋና ካማሺ ዞን ለረጅም ወራት ዘልቆ የቆየው #ግጭት በዘላቂነት እንዲፈታ ተቋርጦ የነበረ የሕዝብ፣ ለሕዝብ የጋራ ውይይትና የባህላዊ ዕርቅ ሥነ ስርዓት ተካሄደ። በሥነ ስርዓቱ ላይ የታደሙ የሁለቱም ዞን ተወካዮች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የነበረው እንቅስቃሴ እንዲጀመር ተግባብተዋል፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር በአዲስ አበባ ዘመናዊ ሙዚየም ሊያስገነባ ነው፡፡ ግንባታውን ለማስጀመርም 20 ሚሊዮን ብር ሰብስቧል፡፡ ለሙዚየሙ ግንባታ ማሕበሩ 740 ስኩዌር ካሬ ሜትር ቦታ አግኝቷል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስከ አርብ ድረስ ብቻ ማዘዝ የሚቻል በራስዎት ስም Bank Of America ላይ አካውንት ተከፍቶ በምርጫዎ "Visacard" ወይም "Master Card" ወይም "American Express Card" በአንድ ሳምንት ውስጥ በስምዎት ይላክሎታል፡፡ verified (አክቲቭ) የሆነ ከሙሉ የባንክ መረጃ ጋር በእጅዎ ይደርሳል፡፡ ፖስታ ሳጥን ቁጥር ላላችሁ በቀጥታ ወደ ሳጥናችሁ ይገባል፡፡ ፖስታ ሳጥን ለሌላችሁ ደግሞ በቀጥታ ደህንነቱ ተጠብቆ ከነማሸጊያው ሳይወጣ በእጅዎ እናደርሳለን:: ከአዲስ አበባ ውጪ ላላችሁ በ EMS እንልካለን፡፡ ትዕዛዝ የምንቀበለው ዛሬ እና ነገ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ያናግሩን @ethioadsense
የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ‼️

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ታሪፍ ላይ #ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

ኢንተርፕራይዙ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የተሻሻለው ታሪፍ ከየካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

ማስተካከያው በክፍያ ጣቢያና በተሽከርካሪ አይነት የተደረገ ሲሆን ከ2 እስከ 16 ኪሎ ሜትር ለተሽከርካሪ 1 እና 2 የተደረገው የዋጋ ተመን 15 ብር ነው።

ከ2 እስከ 64 ኪሎ ሜትር ከተሽከርካሪ 5 እስከ 7 የተደረገው የዋጋ ተመን 80 ብር ሆኗል።

ሌሎች የዋጋ ጭማሪዎችን በኢንተርፕራይዙ ድረገጽ www.etre.com.et መመልከት ይቻላል።

ኢንተርፕራይዙ አብዛኛው ለጥገና የሚውል ጥሬ ዕቃ በአገር ውስጥ ስለማይገኝና ከወቅቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አንጻር የውጭ ብድርን በብቃት ለመክፈል የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን አስታውቋል።

ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ግሽበት የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋምና በአገልግሎት አሰጣጥ የተገኙ ልምዶችን በመውሰድ አሳማኝና መጠነኛ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል ነው ያለው።

የመንገዱ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግና የተደረገውን የታሪፍ ለውጥ አውቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ኢንተርፕራይዙ አሳስቧል።

ኢንተርፕራይዙ ለጥገናና ለውጭ እዳ ክፍያ በየዓመቱ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚያደርግ ቢያስታውቅም ለ4 ዓመታት በነበረው ታሪፍ ሲሰራ ቆይቷል።

በተያዘው በጀት ዓመት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ አጥንቶ ተግባራዊ አድርጓል።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን የአዲስ አዳማን የፍጥነት መንገድ የማስተዳደር፣ በክፍያ የመንገድ አገልግሎት የመስጠት፣ መንገዱን የማስጠገንና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፍርድ ቤቶች በጀት የሚያጸድቅበት አሠራር ሊጀመር መሆኑን የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተውቋል፡፡ በዚህም መሠረት የ2012 ዓ.ም በጀት ጥያቄያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው እንደሚያስወስኑ የጀርመን ራድዮ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ እስካሁን ለዳኝነት አካላት ዐመታዊ በጀታቸውን የሚደለድልላቸው ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ነበር፡፡ ሕገ መንግሥቱ ግን ፍርድ ቤቶች የበጀት ጥያቄያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያቀርቡ ነው የሚያዘው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናይጄርያ አጠቃላይ ምርጫዋን ወደ መጪው ቅዳሜ አራዝማለች።

Letter via Silabat Manaye
©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia