TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ🔝

ለ20 ዓመታት ከሃገር ውጭ የነበሩ #የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ የኢሳት ጋዜጠኞቹን የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶ/ር #ሂሩት_ካሳሁን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት አቀባበል አድገውላቸዋል። በተጨማሪም የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸውም ጭምር በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ጋዜጠኞቹ በበኩላቸው ወደ ሃገራቸው በመግባታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው እና በሃገሪቱ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል እና የሚዲያ ሃላፊነቱን ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራው ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ሥራው ከመግባታቸው በፊት #ቃለ_መሃላ እንደሚፈፅሙ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ ቆጠራውን በተመለከተ በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተርና የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ፀሐፊ አቶ #ቢራቱ_ይገዙ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በቆጠራው የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 32ኛው የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የድንበር ኮሚሽን ስብሳባ ውሳኔዎች በማሳለፍ ተጠናቀቀ።

በስብሰባው የድንበር አካባቢ ማህበረሰቦች የፖለቲካ፣ የፀጥታ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማካሄድ በቀጣይ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማሻሻል የሚያግዙ ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በአዋሳኝ ድንበሮቻቸው አካባቢ ያላቸውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ይበልጥ #ለማጠናከር እንደሚሰሩ የጋራ የድንበር ኮሚሽን ስብሰባ ላይ #ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም በድንበር አካባቢ ለሰላም እና ፀጥታ ችግር ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች በጋራ ለመፍታት ከሚመለከታቸው የሁለቱ አገራት መ/ቤቶች እና የተጋሪ ድንበር አካባቢ አስተዳዳሪዎች የአገር ሽማግሌዎች የተውጣጣ የሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ አንዲገባ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

ሁለቱም ወገኖች ስምምነቶቹን ለመተግበር የሚያስችል በልዑካን ቡድን መሪዎቻቸው አማካኝነት ቃለ ጉባኤ ተፈራርመዋል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአራዳ ~ ወረዳ 5 ወጣቶች🔝

አራዳ ወረዳ 5 የሚገኙ #ወጣቶች "በቂ ማስረጃ እጃችን ላይ እያለ፤ ሁሉን ነገር ጨርሰን የድጋፍ ደብዳቤ ተፅፎልን (ኮንቴነር ይሰራ የሚል)፣ ውል ተዋውለን፤ የቲን ቁጥር አውጥተን #ስራ_ከጀመርን በኃላ #አፍርሱ ብለውናል።" ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የሚመለከተው አካል ጉዳዩን በትኩረት ተመልክቶ መፍትሄ ይስጠን ሲሉም ጠይቀዋል።

•ጉዳዩ የሚመለለተው አካል ምልሻ መስጠት ከፈለገ +251919743630 ወይም @tsegabwolde መጠቀም ይችላል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የአዲስ አበባ ጉዳይ #የሚመዘዘዉ የያዝነዉን ዋና አጀንዳ ትተን በሚያባሉን ጉዳዮች ላይ እንድንጠመድ ነዉ፡፡” አቶ #ካሳሁን_ጎፌ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው 31 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ  ስድስቱ ደግሞ  የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ተሳፋሪ ጭኖ ከቁስቋም ወደሽሮሜዳ ሲጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ 10633 ኮድ አንድ የሆነ ሚኒባስ ታክሲ አቅጣጫውን ስቶ ከኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ምሶሶ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በአደጋው ሁለት ተሳፋሪዎች #ሞተዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስት ሰዎች መካከልም ሁለቱ በከባድ መጎዳታቸውም  ተመልክቷል። 

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። 

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነም የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል።

በአደጋው የሞቱት ሴቶች ሲሆኑ የተጎዱት ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ነው ኢንስፔክተር ማርቆስ የጠቀሱት። 

በአደጋው መስተዋቱን ጨምሮ #የተሽከርካሪው አካል መጎዳቱን በቦታው የተገኘው የኢዜአ ሪፖርተር ተመልክቷል።

የዓይን እማኞች እንደገለፁት አደጋው በተሽከርካሪው ፍሬን ችግር የተከሰተ ነው።

በታክሲው ተሳፍረው ሲጓዙ የነበሩት አቶ አንዷለም ለማ እንዳሉት በጠዋት ወደ ቢሮ ለመሄድ በጉዞ ላይ እያሉ አንዲት ተሳፋሪ መውረጃዋ ደርሶ “ወራጅ” ብትልም ታክሲው ሊቆም አልቻለም።

“ከዚያም ከደቂቃዎች ልዩነት በኋላ የታክሲው ረዳት ሰዎችን ከመንገዱ ዞር እንዲሉ ማስጠንቀቅ ጀመረ፤ ሹፌሩም የመኪናውን መሪ ይዞ ሲታገል ነበር “ያሉት አቶ አንዷለም ከዛ በኃላ መኪናው ተጋጭቶ ሲቆምና ከመኪናው ውጪም የተጎዳ ሰው ማየታቸውን ያስታውሳሉ።

ተሳፋሪው ከተረጋጋ በኃላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን እንደሰሙም አክለዋል።

አሽከርካሪዎች ሲጓዙ የቴክኒክ ፍተሻ በማድረግ ራሳቸውንና ኀብረተሰቡን ከአደጋ መጠበቅ እንዳለባቸውም አቶ አንዷለም መልዕክት አስተላልፈዋል። 

ምንጭ፦ ኢዜአ
ፎቶ፦NTU(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዲ ኢሌ‼️

ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል የቀድሞ ርእሰ መስተዳደር  #አብዲ_መሀመድ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ያቀረበውን አቤቱታ ተቀበለ።

ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ በተመለከተ ምርመራ ተጠናቆ ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

ክስ ከተመሰረተባቸው 47 ግለሰቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የተነበበላቸው አብዲ መሀመድ ዑመር፣ ራህማ መሀመድ ሀይቤ፣ አብዱራዛቅ ሰሀኔ ኢልሚ፣ ፈርሃን ጣሂር በርከሌ ናቸው።

ጉሌድ ኦበል ዳውድ እና ወርሰሜ ሼህ አብዲ የፍርድ ቤቱን የስራ ቋንቋ ባለማወቃቸው ምክንያት እስካሁን ድረስ ዐቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ እንዲረዱት አልተደረገም።

ፍርድ ቤቱም ዛሬ በዋለው ችሎት የሶማሊኛ ቋንቋ አስተርጓሚ በቋሚነት እንደሚመደብ አዟል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮች ከተከሳሾች መዝገብ ጋር በማያያዝ በምስክሮች ላይ ሞራላዊ፣ አካላዊ እና የደህንነት ስጋት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ለማድረግ እና ህጉም የሚፈቅድ መሆኑን በማስረዳት የተከሳሾች ማንነትና አድራሻ እንዳይገለፅ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ተቀብሎታል።

የተከሳሽ ጠበቆችም የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ለተከሳሾች እንዲገለጹ የተጠየቀበት ምክንያት የተከሳሾችን ህገ-መንግስታዊ መብት ለማስከበር እና ከጉዳዩ ጋር ለማጣጣም መሆኑን ነው ለፍርድ ቤቱ ያስረዱት።

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም ያልቀረቡ ተከሳሾችን እንዲቀርቡ ለመጠባበቅና ክሳቸው ያልተነበበላቸው በአስተርጓሚ እንዲረዱት ለማድረግ እንዲሁም ተገቢውን ትዕዛዝ ለመስጠት ለየካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን ከፌደራል አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia