TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምስራቅ ጎጃም‼️

በምስራቅ ጎጃም ዞን #ነዳጅና #ሲሚንቶ ጭነው ይጓዙ የነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተገልብጠው ንብረት መውደሙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ኢንስፔክተር #ጎበዜ_ይርሳው ለኢዜአ እንደተናገሩት አደጋው የደረሰው ከሱዳን አዲስ አበባ ነዳጅ ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ትናንት በመገልበጡ ነው፡፡

በአደጋው ቦቲው 47ሺህ 950 ሊትር ቤንዚን ጭኖ ከነተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በእሳት መጋየቱን አስታውቀዋል፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 7139 ተሳቢ 10704 ኢትዮጵያ የሆነ መኪና የመገልበጥ አደጋው የደረሰው በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ትግዳር ቀበሌ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪው #በቁጥጥር ሥር ውሎ  የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑንም ኢንስፔክተር ጎበዜ አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ከአዲስ አባባ ወደ ቡሬ ኢንዱስትሪያል ፓርክ  ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 75260 ተሳቢ 18 029 ኢትዮጵያ የሆነ ተሽከርካሪ መኪና 400 ኩንታል ሲሚንቶ እንደጫነ በማቻከል ወረዳ በአማሬ ቀበሌ በመገልበጡ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

የካቲት 6/2011 ከሌሊቱ ሰባት ስአት በደረሰው የመገልበጥ አደጋም በተሽከርካሪውና በተጫነው ሲሚንቶ   ምርት ጉዳት ደርሷል፡፡

አሽከርካሪውም የመቁሰል አደጋ ደርሶበት በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል ብለዋል።

የሁለቱም ተሽከርካሪዎች አደጋ ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የቡድን መሪው አስታውቀዋል። 

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፒያሳ ወጣቶች~አዲስ አበባ🔝

"እኛ የፒያሳ ወጣቶች ከባድ ችግር ስለገጠመን #ሀሳባችንን መላው ህዝብ ይወቅልን። እኛ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ተደራጁ ብለው ተስፋ ቆርጠን ከተቀመጥንበት ወጣቱን ካለንበት አደራጅተናል ለማለት ይሁን ለወሬ ካደራጁንና ቦታ ሠጥተው ከሠራን በዃላ #ይፍረስ ብለው በህልውናችን በማንነታችን በዜግነታችን ላይ እየተረማመዱብን ሜዳ ላይ ሊበትኑን ነው። ስለዚህ እባካችሁን የሚመለከተው አካል ይስማ! ለመላው ህዝብ ብሶታችንን ድምፃችንን አሰሙልን።"

•ጉዳዩ የሚመለለተው አካል ምልሻ መስጠት ከፈለገ +251919743630 ወይም @tsegabwolde መጠቀም ይችላል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ባለፉት ሰባት ወራት 14  ሺህ 412 ጋበቻዎችና 1 ሺህ 223 #ፍቺዎች ምዝገባ ማካሄዱን የከተማዋ ወሳኝ ኩነት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የግጭት ትርፉ፦

🔹ለቅሶ
🔹ስቃይ
🔹መከራ
🔹ረሀብ
🔹ስደት
🔹ሞት
🔹የሚወዱትን ማጣት
🔹ችጋር
🔹በሽታ
🔹እልቂት...ነው!

ስለማንነት ለማውራት፤ ስለብሄር፣ ስለዘር፣ መብትን ለመጠየቅ፤ ስለጎሳ #ለመነጋገር፤ ስለማንነት ለመሟገት፤ ስለቋንቋ ለመነጋገር፤ ስለከተማ፣ ስለመሬት ለማውራት፤ ስለወሰን ለማውራት፤ ስለነፃነት ለመነጋገር፤ ስለዴሞክራሲ ለመነጋገር... በቅድሚያ አስተማማኝ #ሰላም ያስፈልጋል!! ሰላም ከሌለ ሌላው ቀርቶ በቅጡ #ማሰብ እንኳን አንችልም!!

#ሰላም እንድንሆን እንፈልጋለን?? ሀገራችን ሰላም እንድትሆን እንፈልጋለን?? ታዲያ ምን እንጠብቃለን፥ #ለልጆቻችን ስለሰላም ዋጋ አስቀምጠን እንንገራቸው፣ መምህራን ወደ ክፍል ስንገባ ለተማሪዎቻችን #የሰላምን_ዋጋ እንንገራቸው፣ ሴቶች ወንዶች ቁጭ ብለን ስለሰላም እንነጋገር!! ሰላምን ዛሬ ላይ ሆነን ስናስባት ቀላል ትመስለናለች ከእጃችን ከወጣች መልሰን ለማግኘት #ይከብደናልና አሁኑኑ በያለንበት የሀገራችን የሰላም አምባሳደር ሆነን ስለሰላም እንዘምር!!

•ፈጣሪ ከምንም ነገር በላይ ሰላም #አያሳጣን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨዋ ሰራዊት ነው...

"ለደንብ ልብስ #ክፍያ የሚፈጽም ጨዋ ሠራዊት ነው!! የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የሚለብሱትን የደንብ ልብስ ሲያገኙ የነበረው በክፍያ ነበር ያውቃሉ ? አንድ የሠራዊቱ አባል የተሟላ የደንብ ልብስ ለማግኘት 900 ብር መክፈል ይጠበቅበት ነበር። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የወር ደሞዝ እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ ሳለ ወታደራዊ የደንብ ልብሱን ለማሟላት ከደሞዙ ላይ ቆርጦ ይገዛ ነበር። ከዘንድሮው ዓመት ጀምሮ ግን ይህ እንዲቀር ተወስኖ ወታደራዊ የደንብ ልብሱን መንግስት በነፃ ማቅረብ ጀምሯል። እና ምን ለማለት ነው ?የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገሪቱ ከፍ እና ዝቅ ባለችባቸው ጊዜያት በሙሉ በታላቅ ሀላፊነት ረግቶ የተቀመጠ ስነ ስርዓት ያለው ሰራዊት ነው ፤ ክብር ይገባዋል ሲባል ተረት ተረት አይደለም። እናም ለሠራዊቱ ከፍ ያለ ክብር ይገባል ፣ በተለይም ተራው የሠራዊቱን አባላት ሳስብ የበለጠ ከፍ ያለ ክብር እሰጣለው።" #YohannesAnberbir

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም እደሩ!

የካቲት 7/February 14 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ነው! ክብር ለሰራዊቱ አባላት! የሰላም ፀር ሁሉ ይህን #ጀግና_ሰራዊት ሲመለከት #ይንቀጠቀጣል! እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን አደረሰን!
.
.
መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ነው!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia