TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝

‹‹ለፖለቲካዊ ለውጡ ቀጣይነት›› በሚል ርዕስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ ዶር. #አምባቸው_መኮንን፣ ፕሮፌሰር #መረራ_ጉዲና#ክርስቲያን_ታደለና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዶክተር አምባቸው በአንኳር ንግግራቸው ምሁራን ወቅቱ ባመጣው ለውጥ በፖለቲካው ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረታታቸው በመሆኑ እንደዚህ አይነት የሃሳብ ፍጭቶች የሚካሄዱባቸው መድረኮችን ማዘጋጀት ይገባል ብለዋል፡፡

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይቆያል፡፡ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ በሌሎች ምሁራን አማካኝነት ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረጋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የመከላከያ ሰራዊትን ቀንን አስመልክቶ ህዝባዊ ውይይት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። በዚህ ውይይት የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል🔝 በሀዋሳ ከተማ በ220 ሚሊዮን ብር እየተከናወነ የሚገኘው የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል #የማስፋፊያ_ግንባታ ከላይ #በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#VisitEthiopia #VisitGambella

#Gambella’s waterways lay #claim to the #highest_diversity of fish in Ethiopia, and experts have described the bird life as “astounding.” Gambella is truly a hidden treasure. #LandofOrigins #Ethiopia

©MysticalEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

የት ነው የምትኖሩት?? አካባቢያችሁ፤ ከተማችሁ ውስጥ ምን አይነት ተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሰራሽ መስዕብ አለ?? እናተ ያያችሁት የኢትዮጵያ ድንቅ ቦታዎች ሌሎች እንዲያዩት የምትጠቁሙት ይኖር ይሆን??

•4 ምርጥ ፎቶዎችን ከአካባቢው ስም ጋር በመላክ የምትኖሩበትን አስተዋውቁን። የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶችን ወደ አካባቢያችሁ ጋብዙ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ ሰናይት...‼️

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ፅ/ቤት በቅርቡ ሸገር ሬድዮ ላይ ቀርባ ስለ #መታወቂያ አሰጣጥ አስተያየቷን የሰጠችው ወ/ሮ ሰናይት ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በነበራት ቆይታ ይህን ብላለች፦

"ብዙ ተወርቶ እንደነበረው አስተያየቱን ለሸገር ሬድዮ ከሰጠሁ በሁዋላ ወደ ስራ አልተመለስኩም ነበር። ትናንት ግን #ወደስራ_ተመለሺ የሚል ደብዳቤ ተፅፏል። አሁን ወደ ቢሮ እየሄድኩ ነው። ውጤቱን በሁዋላ እነግርሀለው። ሰዎች #እያስፈሯሯት ነው ተብሎ በሶሻል ሚድያ የተወራው ግን #ሀሰት ነው። እዛ ደረጃ ነገሮች ከሄዱ ወደ መንግስት አካላት እና ሚድያዎች እሄዳለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia