TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአውሮፓ ህብረት ምክትል ፕሬዘዳንት እና የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋር ተወያዩ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ከማህበራዊ ትረስት ፈንድ የቦርድ አባላት እና አርቲስቶች ጋር በመሆን በ ማገገሚያ ማዕከል ያረፉ ልጆች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡

ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ከ32ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ከመካፈል ጎን ለጎን የሚያካሂዷቸውን የተለያዩ ስብሰባዎች ቀጥለዋል። ከፍልስጤም ፕሬዝዳንት #ማህሙድ_አባስ፣ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት #ሲሪል_ራማፎሳና ከኬንያው ፕሬዝዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂደዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደህንነት ካሜራዎቹ ስራ ጀመሩ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ባለው ጎዳና ላይ የተተከሉ #የደህንነት_ካሜራዎች ስራ መጀመራቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ካሜራዎቹ የተተከሉት ከቦሌ ውስጠኛው አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ ባለው መንገድ ግራና ቀኝ በኩል የተተከሉ መሆናቸውን በኮሚሽኑ የአይሲቲ ኢንፍራስትራክቸር ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር #አንድነት_ሲሳይ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በመዲናዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ካሜራዎችን የመትከል እቅድ መኖሩን የጠቀሱት ሃላፊው ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ያሉት ካሜራዎች ከሶስት ቀናት በፊት ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

የካሜራዎቹ ቀረፃና የቁጥጥር ስራውም ያለምንም መቆራረጥ ሌት ከቀን እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክተር ተወካይ ኮማንደር ሁነኛው አየነው ከዚህ በፊት በመዲናዋ ውስን አካባቢዎች የነበሩ ካሜራዎች ከመንገድ ስራ ጋር ተያይዞ መነሳታቸውን አስታውሰዋል።

ሆኖም አገልግሎቱ ዳግም መጀመሩ አዲስ አበባ የበርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የደህንነት ካሜራ አገልግሎት የብዙ ተቋማትን ቅንጅትና በርካታ መዋለንዋይ የሚፈልግ በመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በአንድ ጊዜ ማዳረስ አዳጋች ቢሆንም በቀጣይ ግን በተለይ የኢንዱስትሪ መንደሮች ባሉባቸው ከተሞች ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትናንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት በአቢዬ ጊዜያዊ የደኅንነት ሀይል ግቢ ውስጥ በሂሊኮፍተር አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አስክሬን ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ መሸኘቱ ተገለጸ፡፡ የሱዳንና በደቡብ ሱዳን ተወካዮች ለተጎጂ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ሂሊኮፍተሯ ትናንት የተከሰከሰችው 23 የሠላም አስከባሪ አባላትን አሳፍራ በአካባቢው ቅኝት እያደረገች ሳለ መሆኑና ምክንያቱ እስካሁን አለመታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል። በአደጋው የአራት ሰላም አስከባሪዎች ህይዎት አልፏል አስሩ ደግሞ ተጎድተዋል። ተጎጂዎች ለሰለም አስከባሪዎች አገልግሎት ወደ ሚሰጠው ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም ዘገባው አስታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ የሠላም አስከባሪ አባላት MI-8 በተባለች ሄሊኮፕተር ካዱግሊ ከተባለ ሥፍራ ወደ አብየ ግዛት ለመደበኛ ቅኝት ተሰማርተው እያሉ ነው አደጋው እንደደረሰ የተዘገበው። አደጋው የደረሰው በተባበሩት መንግሥታት የአብየ ግዛት ሰላም አስከባሪ ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ነው። በአብየ ግዛት የተመድ ሰላም ማስከበር የተልዕኮና ግዳጅ ተጠባባቂ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ገብረ አድሃና ወልደእዝጉ የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ - ተመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ስነተዋልዶ ጤና ክሊኒክን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia