TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅግጅጋ🔝

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በይፋ ትጥቁን ፈታ። የትጥቅ መፍታት ስነ-ስርዐቱ የሱማሊ ክልል ባለስልጣናት እና የኦብነግ መሪዎች በተገኙበት በትላንትናው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ተከናውኗል። ኦብነግ በትጥቅ መፍታት ስነስርዐቱ ላይ 1740 ታጣቂዎቹን ለመንግስት #አስረክቧል። የኦብነግ ሊቀመንበር የታጣቂዎችን ሰነድ ለሱማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አስተክበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በዛሬው ዕለት በጽ/ቤታቸው ተወያዩ። በኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እየተደረገ ባለው ርብርብ የዓለም የጤና ድርጅት እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አድንቀዋል። ትብብሩ ከዚህ በበለጠ ተጠናከሮ እንደሚቅጥል እምነታቸው መሆኑንም ክቡር ሚኒስተሩ ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው በአትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል። ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ከተመሰረተበት ከ 1940 ዓ.ም ጀምሮ የድርጅቱ የረዥም ጊዜ አባል በመሆን በመስራት ላይ ትገኛለች።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ #አንቶኒዩ_ጉተሬዝ 32ኛውን አፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የአፍሪካን ችግር ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄዎች አስፈላጊ መሆናቸውን እንደሚያምቱ ዋና ጸሃፊው ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ ውስጥ ቀውሶች እንዳይፈጠሩ እና ግጭቶችን በማስቆም ለአህጉሪቱ ልማት መፋጠን የሚያደርገውን ጥረት የመንግስታቱ ድርጅት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወደቦችን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን መልሶ ለመገንባት የ20 ሚሊዮን ዩሮ #ድጋፍ ማድረጉን የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ሁለቱን ሀገራት ለመደገፍ #ቁርጠኛ መሆኑን የህብረቱ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኔቨን ሚምካ ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በማጠናከርና ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ለሁለቱ ሀገራት ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ20 ዓመታት በኋላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተወያዩ። በሁለቱ ሀገራት መካከል የሁለትዮሽ ትብብር እኤአ ከ1995 ጀምሮ የተመሰረተ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ የኖርዌይ ትልቋ አለምአቀፍ ትብብር እንድትሆን አስችሏታል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ይህንኑ ትብብር በማድነቅ የስካንዲኔቪያ አገራትን የ # መደመር ተሞክሮ አገራቱ በጋራ እንዲያድጉ እድል እንደከፈተላቸው አውስተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት እንደገለፀው ይህም ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ውህደት እንደ ተምሳሌት የሚወሰድ ነው ብለዋል። የኖርዌይ ጠ/ሚኒስትር በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥና የከባቢው ውህደት ጅማሮዎችን በማድነቅ አገራቸው የምታደርገውን እርዳታ በተለይም በትምህርት ዘርፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
The account is #hacked.The team ICT is working on to fix.

#TakelUmaBanti
ወታደራዊ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር #ተከስክሶ ሶስት የበረራ ሰራተኞች ሞቱ። ሔሊኮፕተሩ #በአቢዬ ግዛት ሲከሰከስ 23 መንገደኞች ጭኖ ነበር። የተባበሩት መንግስታት የአቢዬ ግዛት ጸጥታ ጥበቃ ተልዕኮ አካል ነበር።

via Esehete Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን አቢዬ ግዛት #ተከስክሶ ሶስት ሰዎች ሞቱ። በአደጋው የሞቱት #ሶስት ሰዎች የሔሊኮፕተሩ የበረራ #ሰራተኞች ናቸው። ከቆሰሉ ስምንት ተሳፋሪዎች ሶስቱ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

የምዝገባ ቁጥሩ UNO 379P የሆነው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል (UNISFA) ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከሰከሰበት ቅፅበት 23 መንገደኞች ጭኖ ነበር። የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል እንዳስታወቀው ኤምአይ ስምንት (MI-8) የተባለው ሔሊኮፕተር በተከሰከሰበት ቅፅበት ካዱግሊ ከተባለ ቦታ ወደ አቢዬ በመቀየር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አሳፍሮ ነበር። 

በአደጋው ስምንት መንገደኞች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሶስቱ በአስጊ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአስጊ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙት ተሳፋሪዎች በካዱግሊ በኩል ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውንም አክሎ ገልጿል። በመግለጫው መሠረት ቀሪዎቹ አምስት መንገደኞች በአቢዬ በሚገኝ ሆስፒታል እገዛ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ሔሊኮፕተሩን ለመከስከስ ያበቃው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሐና ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑን ተናግረዋል። "ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተፈጠረው ክስተት እጅግ አዝነናል። በአደጋው ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን" ብለዋል ሜጀር ጄኔራል ገብሬ። 

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር የተከሰከሰው መደበኛ የወታደሮች ዝውውር መርኃ-ግብር ተሰማርቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ያወጣው መግለጫ አትቷል። ለተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ወታደሮች #በብቸኝነት ያዋጣቸው ኢትዮጵያ 4,500 አባላት ያሉትን ኃይል አሰማርታለች።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

የከንቲባ #ታከለ_ኡማ(ኢ/ር) የግል የፌስቡክ ገፅ ሃክ (በግል ለመገልገል ስላዳገተ) በመደረጉ ምክንያት የሚተላለፉ መልክቶችም ሆነ ሃሳቦች የእሳቸው እንዳልሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"የከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) የግል የፌስቡክ ገፅ ላይ "ፌስቡክ ገፄ #አልተጠለፈም" ተብሎ ቢገለፅም አሁንም ገፁ #ሃክ እንደተደረገ መሆኑን እንዲታወቅ እና ማንኛውም የሚተላለፍ መልዕክትም ሆነ ሃሳብ ከንቲባውን እንደማይወክል በድጋሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡"

ከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia