TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢንጅነር ታከለ ኡማ‼️

ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ በተባለ ተቋም የአፍሪካ ከንቲባዎች እና መሪዎች አለም አቀፍ ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው ተመረጡ፡፡

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየሰሩት ባለው የልማትና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ስራዎች እና የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰሩ ባለው ስራ የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለምአቀፍ ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው እንዲመረጡ እንዳስቻላቸው የተቋሙ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጂብሪል ዲያሎ አስታውቀዋል፡፡

ተቋሙ በቀጣይነት ኢትዮጵያ የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፍ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በማጣመር ወጣት የከተማዋ ነዋሪዎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንደሚንቀሳቀስ መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ @mayorofficeAA (ትክክለኛ የከንቲባ ፅ/ቤት የቴሌግራም ቻናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የቀድሞው የአርሰናል ክለብ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በሚቀጥለው ወር በአሰልጣኝነት ወይም የእግር ኳስ ዳይሬክተር በመሆን ወደ እግር ኳስ ስራቸው ሊመለሱ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ አርሰናልን ለ22 አመታት ያሰለጠኑት ፈረንሳዊው አርሰን ቬንገር ሶስት የፕሪሚየር ዋንጫ ካሸነፉበት የሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር የውድድር አመቱ ከመጀመሩ በፊት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ዘ ታይምስ ዘገባ አርሰን ቬንገር ከአራት ያላነሱ የቅጥር ጥያቄዎች የደረሷቸው ሲሆን ሁሉም ግን ከእንግሊዝ ክለቦች ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ አሰልጣኙ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለመሩት አርሰናል ካላቸው ክብር የተነሳ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወት ተቃራኒ ክለብ ማሰልጠን አይፈለጉም ነው የተባለው፡፡ የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ክለብ ከፖርቹጋላዊው የፓስ ሴንት ክለብ የእግር ኳስ ዳይሬክተር አንቴሮ ሄኔሪኬ ጋር መለያየቱን ተከትሎ አርሰን ቬንገርን ለቦታው እንደሚፈልገው ነው የተጠቆመው፡፡ ከፓሪሱ ክለብ ውጪ አንድ ስሙ ያልተገለፀ ብሄራዊ ቡድንም የአንጋፋውን አሰልጣኝ ግልጋሎት እንደሚፈልግ ታውቅል፡፡ አርሰን ቬንገር ለማራኪ እግር ኳስ ካላቸው ፍልስፍና ባየር ሙኒክ፤ኤሲ ሚላን እና ሪያል ማድሪድ በመሳሰሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስማቸው ሲያያዝ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር~አዘዞ‼️

በጎንደር ከተማ አዘዞ አካባቢ 50 በላይ እንስሳት ላይ የቃጠሎ አደጋ ማጋጠሙን የዓይን ምሥክሮች እና ፖሊስ ተናገሩ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ነዋሪ የሆኑ የዓይን ምሥክሮች እንደተናገሩት ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ አካባቢ ልዩ ሥሙ ግራር ሰፈር በሚባል ቦታ በእንስሳት ማድለቢያ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 የሚደርሱ የደለቡ ከብቶች ተቃጥለዋል፤ በጣት የሚቆጠሩ ከብቶችን ብቻ በሕዝቡ ጥረት ማትረፍ ተችሏል፡፡

የዓይን ምሥክሮቹ እሳቱን ለመቆጣጠር የአካባቢው ነዋሪና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥረት ቢያደረጉም መቆጣጠር የተቻለው በዳግማዊ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪና ሠራተኞች እገዛ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የዓይን ምሥክሮቹ አደጋውን ማን እንዳደረሰው በግልጽ ባይታወቅም ከሰሞኑ የአካባቢው ግጭት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሌሊቱን በአዘዞ አካባቢ ተኩስ እንደነበር ያስረዱት የዓይን ምሥክሮቹ ‹‹ተኩሱ ግን እሳቱን ለመቆጣጠር እንዲቻል ጥሪ ለማስተላለፍ ያለመ ነበር›› ነው ያሉት፡፡ በእሳት አደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልጸው በብድር ገንዘብ ተደራጅተው በከብት ማድለብ የተሠማሩ ወጣቶችን ለፖለቲካ ጥቅም መጉዳት ተገቢ እንዳልነበር ተናግረዋል፤ መንግሥት በአፋጣኝ ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲያቀርብም አሳስበዋል፡፡

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ሰይድ ደግሞ ምሽት 5፡00 አካባቢ እሳት ቃጠሎው መነሳቱን አስታውሰው በማድለቢያና እንስሳት እርባታ ድርጅት ላይ በደረሰ ቃጠሎ 51 የቁም ከብቶች መሞታቸውን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል፡፡ ምን ያክል ከብቶች እንደተረፉ ግን ማረጋገጫ እንደሌላቸው ነው መርማሪው ለአብመድ የተናገሩት፡፡

ቃጠሎው በደረሰበት አካባቢ የእንስሳት መኖ መኖሩ ለቃጠሎው መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን የገለጹት ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ‹‹የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የምርመራ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው፤ ወደፊት ውጤት ላይ ስንደርስ ለሕዝብ እናሳውቃለን›› ብለዋል፡፡ በአካባቢው ለእሳት መነሳት ምክንያት የሚሆን ተፈጥሯዊ ምክንያት እንዳልነበረ ግን ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡

ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን በተመለከተ መረጃ መስጠት የሚፈልግ ሁሉ ለፖሊስ ጣቢያው ጥቆማ እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል🔝የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአሁን ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

ፎቶ፦ ትዕግስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈራረመውን የኢትዮጵያውያን የስራ ስምሪት መግባቢያ ሰነድ #አፀደቀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ሶስተኛ ልዩ ስብሰባው መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈራረመውን የኢትዮጵያውያን የስራ ስምሪት መግባቢያ ሰነድ በአብላጫ ድምጽና በ26 ተቃውሞ አፅድቆታል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ 20 አንቀጾች ያሉት ሲሆን በኤምሬቶች ህግ መሰረት በቤት ውስጥ አገልግሎት ምድብ ውስጥ በሚገኙ ስራዎች እንዲሁም በግሉ ዘርፍ ለስራ የሚሰማሩ ሰራተኞችን ያካተተ ስምምነት ነው፡፡

በስምምነቱ መሰረት የሰራተኞች ምልመላና ስምሪት የሀገሪቱን ህግ ያከበረ እንዲሆን የማድረግ፣ የሰራተኞች መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ እና ሰራተኞች ለጉልበት #ብዝበዛ እንዳይጋለጡ የማድረግ፣ ለስራ ውሎች የህግ እውቅና እና ተፈጻሚነት የመስጠት፣ ሰራተኞች ገቢያቸውን ወደ ሀገራቸው እንዲልኩ ማስቻል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዴታ እንደተጣለበት በስምምነቱ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን #በአፍሪካ_ህብረት የመሪዎች ስብሰባ የውሃ ችግር እንዳይከሰት ልዩ ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ መሪዎቹ ስብሰባ የሚያካሂዱበትን አካባቢ ጨምሮ ያርፉባቸዋል ተብለው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለዩ 56 ሆቴሎች ውሃ በአግባቡ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን፥ የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ ወይዘሮ #ሰርካለም_ጌታቸው ተናግረዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ይህ ስራም ከአቃቂ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ውጭ በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የሆቴሎቹን ዝርዝር በመበተን ከጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በዚህ ሂደትም ሆቴሎቹ ውሃ የሚያገኙበትን መስመር የመፈተሽና ሲቋረጥ ያላቸውን የውሃ መጠን በመለየት በቦቴ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚያስችል ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ከጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በማዕከል የሚመራ ኮማንድ ፖስት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

ኮማንድ ፖስቱ ሆቴሎቹ በሚገኙባቸው መገናኛ፣ መካኒሳ፣ አራዳ እና ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ ባጅ በመያዝ እየሰራ ይገኛል።

ልዩ ኮማንድ ፖስቱ በዋናነት በስብሰባው ወቅት ለመሪዎቹ የውሃ አገልግሎት እንዳይቋረጥና በዚህ ሳቢያ የሃገሪቱ ገጽታ እንዳይበላሽ ለማድረግ የሚሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Dagi's Spa
@DagiSpa
ፕሮፌሽናል ማሳጅና ሞሮኮ ባዝ 💆💆‍♂️። የ ካፕል አገልግሎት እንሰጣለን።
0912923692 ወይም 0118510395 ይደውሉ፡፡ ቦሌ ከፍሬንድሺፕ ና ከዲኤች ገዳ ጀርባ።
አቶ በረከት ስምዖን‼️

በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ብክነት የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ ትላንት በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል።

ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን አለማጠናቀቁን አስታውቋል።

ከዚህ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሳቸውን የጠቀሱት አቶ በረከት ሰምኦን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ አንዲሆን ጠይቀው ነበር።

የዳሽን ቢራ ሁሉም ሰነዶች ተሟልተው እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ታደሰ ካሣ በበኩላቸው መነግሥት አስረን አናጣራም፤ አጣርተን ነው የምናስረው ማለቱን ጠቅሰው የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ አነሱን በእስር ለማቆየት ብቻ መሆኑን በመጠቆም ውድቅ አንዲሆን ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን ውስብስብነትና መረጃዎች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ መገኘታቸውን ከግምት በማስገባት የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮውን ፈቅዷል።

አቶ በረከት ስንገባም ስንወጣም አየተሰደብንና ስማችን እየጎደፈ ነው ብለዋል።

ጠበቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ እንዲያቆምላቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የመገናኘት ዕድል እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ለመፃፍ የሚያስችላቸው ኮምፒዩተር እንዲገባላቸው ጠይቀዋል። አቶ በረከት በማረሚያ ቤት ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲሉም ተደምጠዋል።

የሚደርስባቸውን ዘለፋ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የሚደርስባቸውን ዘለፋ ለማስቆም እንደሚሰራ አስታውቋል።

ምንጭ:- BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት የናይጄሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደሚመሩ በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚሽነር አስታወቁ። ኮሚሽነሯ ሚናታ ሳማታ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ በቅርቡ ወደ ናይጄሪያ በማቅናት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለመላክ ከስምምነት ደርሰዋል። የናይጄሪያ ምርጫ እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 16 ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅግጅጋ🔝

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በይፋ ትጥቁን ፈታ። የትጥቅ መፍታት ስነ-ስርዐቱ የሱማሊ ክልል ባለስልጣናት እና የኦብነግ መሪዎች በተገኙበት በትላንትናው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ተከናውኗል። ኦብነግ በትጥቅ መፍታት ስነስርዐቱ ላይ 1740 ታጣቂዎቹን ለመንግስት #አስረክቧል። የኦብነግ ሊቀመንበር የታጣቂዎችን ሰነድ ለሱማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አስተክበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia