TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ አረፉ‼️

ኮ/ል #ታደሰ_ሙሉነህ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የ71 ቅጥር አባል ናቸው። በቀደመው አየር ኃይል በሚግ-23 ተዋጊ ስኳድሮን ውስጥ በምሥራቅም ሆነ በሰሜን ግንባር ተሰልፈው ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉት የአገራችን ኢትዮጵያ ባለውለታ አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ።

በ1991 ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ በመቃወም ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን በመምራት በኤርትራና በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ምዕራብ በረሃዎች ሳሉ በኤርትራ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር በመዋላቸዉ ለበርካታ አመታት ደብዛቸው፤ አድራሻቸው ጠፍቶ ነበር።

ከወራት በፊት ኮ/ል ታደሰ ከኤርትራ እስር ነፃ ይሁን እንጂ ጤንነታቸው ታውኮ ሰውነታቸው እንደልቡ በማያዝቡት ሁኔታ በመሆኑ በህክምና #በህንድ ሐገር ሲታከሙ ቆይተው ጥር 27 ቀን 2011 ዓም አርፈዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
6400 ላይ 'A' ብለው በመላክ የጎዳና ልጆችን መልሶ ለማቋቋም የድርሻዎትን ይወጡ፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 'አዲስ አበባ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ' የሂሳብ ቁጥር 1000272444726 ላይ ድጋፍ ያድርጉ፡፡
#update ኤርትራ ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የተውጣጣ የህዝብ ዲፕሎማሲ ልኡክ ወደ ኢትዮጵያ ትልካለች። አባላቱን የካቲት 7/ 2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንደምትካቸው ነው የተገለጸው፡፡ የጉብኙቱ ዋኛ ዓላማ የሀገራቱን ታሪካዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር መሆኑን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል፡፡ የልኡኩ አባላት በኢትዮጵያ ቆይታቸው በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር እና ሀዋሳ ከተሞች የሚዘጋጁ የሙዚቃ ኮንሰርቶችንም ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያን እና የኤርትራን ሰላም ለማክበር በሚደረጉ የባህልና የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ ሁሉም በአገር ውስጥ የሚገኝ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን እንደተጋበዙ ሚንስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ሰባት ኪሎግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሃገራት ገንዘብ #መያዙን ገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ። አራት ተጠርጣሪዎችም #በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር #ቶጎ_ውጫሌ ኬላ ላይ ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጪ አገር ገንዘብ መያዙን ገልጿል።

የአሜሪካ፣ የካናዳና የአውስትራሊያ ዶላር፣ ዩሮ፣ ድርሃምና የሌሎች ሃገራት ገንዘብ ነው የተያዘው ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

ትናንት ምሽት ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የውጪ አገር ገንዘብ ከአራት ተጠርጣሪ ኮንትሮባንዲስቶች ጋር በቶጎ ዉጫሌ ኬላ በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሜን ዕዝ~መከላከያ‼️

የሰሜን ዕዝ የዘንድሮውን 7ኛ የሰራዊ ቀን #ባድመ ላይ ሊያከብር ነው። የኢትዮ-ኤርትራ #ሰላም መፈጠር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ፋይዳ የጎላ ሆኖ ማገኘቱን የሰሜን ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ፡፡

“ህገ መግስታዊ #ታማኘነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችንን ጠብቀን የተጀመረው ለውጥ እናስቀጥል” በሚል እየተከበረ ያለው 7ኛው የሰራዊት ቀን በዕዝ ደረጃ ባድመ አካባቢ ለሚደረገው የማጠቃለያ ስነ ስርዓት በተመለከተ አመራሮቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #ከድር_አራርሳ የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም መፈጠር ህዝቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ከማድረጉ በተጨማሪ ሰራዊቱን ለማሰልጠንና ያለስጋት ስራዎቹን እንዲያከናውን ያግዛል ብለዋል፡፡

#በመከላከያ_ሰራዊት ውስጥ የተጀመረው የማሻሸያ ስራ በተቋም ደረጃ ከላይ እስከ ታች እየሰፋና እየተጠናከረ መሆኑን ተናግርዋል፡፡ሰራዊቱ ኃይሉን እያጠናከረና የብሄር ተዋፅኦውን ይበልጥ እያስተካከለ እንደሚገኝም ምክትል አዛዡ አስረድተዋል፡፡ የሰሜን ዕዝ የሰው ሀብት አመራር ዘርፍ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ገ/እግዚያብሄር በየነ 7ኛው የሰራዊቱ ቀን ከስጋት ነፃ በሆነና የሁለቱም አገራት ወታደሮች ከምሽግ ወጥተው በጋራ መዋል በጀመሩበት የሚከበር በመሆ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በዓሉ ሰራዊቱ ከለውጥ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከበረ ያለ በመሆኑ ሰራዊቱ ቃል ኪዳኑን የሚያድስበት አጋጣሚ አድርጎ እንደሚጠቀምበትም ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ያለው የሰራዊቱ ቀን የማጠቃያ ስነ ስርዕቱን ባድመ ላይ ይካሄዳል፡፡

በበዓሉ ሰራዊቱ ዝግጅቱን የሚያሳዩ የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንቶችና የፓናል ውይይት የሚደረግ ሲሆን ሰራዊቱን ያገለገሉ አባላት የክብር አሸኛኘት ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡ እንደ ኢቢሲ ዘገባ የትግራይ ክልልና አጎራባች ክልሎች ተወካዮች በበዓሉ አከባበር ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጤፍ ላይ የባለቤትነት መብት አለኝ ብሎ ሲሟገት የነበረው የኔዘርላንድ ነጋዴ ዘሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንደተፈረደበት አቶ #ፍፁም_አረጋ በማሕበራዊ ገፃቸው ይፋ አድርገዋል። የጤፍ የባለቤትነት መብት የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ያሉት አቶ ፍፁም ይህን ዕውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውም ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፌደራል የመካከለኛ ገቢ ግብር ከፋዮች ቢሮ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ ወቅትም ሰለ አጠቃላይ እንቅስቃሴው በባለሙያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በወቅቱም ከቢሮው ሰራተኞች ጋር እና ከግብር ከፋዮች ጋር ተገናኝተዋል። ከሳምንት በፊት ከሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር የአፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት፥ የመንግስት ተቋማትና ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እየተወጡ መሆኑን ለማረጋገጥ ይህን መሰል ድንገተኛ ጉብኝት እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ፦ #ለዩኒቲ_ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ~ጉዳዩ የነፃ የትምህርት እድልን ይመለከታል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዲ ኢሌ‼️

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ_መሐመድ የቀረበባቸው ክስ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አሉ። አቶ አብዲ ይህን ያሉት ጉዳያቸውን እየተመለከተ ላለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው።

ችሎቱ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው አቶ አብዲን ጨምሮ በ47 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበባቸውን ክስ በንባብ ለማሰማት ነበር። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በይፋ ክስ የመሰረተው ባለፈው ረቡዕ ጥር 22 የነበረ ቢሆንም የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ባለመገኘታቸው የክስ ንባቡ ለዛሬ ተላልፏል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በሐምሌ 2010 ዓ. ም. በሶማሌ ክልል 59 ሰዎች እንዲገደሉ እና 412 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል ነው ክሱን ያቀረበው።

በዛሬው የችሎት ውሎ ክሳቸውን ያደመጡት አቶ አብዲ ክሱን ተረድተውት እንደሆነ በመሐል ዳኛው ሲጠየቁ “ሆን ተብሎ የተቀነባበረ #ውሸት መሆኑ ገብቶኛል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የእርሳቸውን ምላሽ ተከትሎ ችሎቱን ሞልተው የነበሩ ታዳሚዎች በሹክሹክታ ሲጠያየቁ እንደነበር በስፍራው የተገኘው የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ ታዝቧል። ፍርድ ቤቱ ከአቶ አብዲ ውጭ የሌሎችን ተከሳሾች ምላሽ ያላደመጠ ሲሆን ከክስ መቃወሚያ ጋር ደርቦ ለመስማት ለመጪው የካቲት 20 ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች በክሱ ላይ ያቀረቡትን አቤቱታም አድምጧል። በክሱ ውስጥ የምስክሮች ዝርዝር አለመካተቱን ያነሱት የተከሳሽ ጠበቆች በተገቢው ሁኔታ “እንድንከላከል አያስችለንም” ሲሉ ተቃውመዋል። አቃቤ ህግ ምላሹን በጽህፈት ቤት በኩል እንዲያስገባ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 6 ቀጥሯል።

በዛሬው ችሎት አብዛኞቹ ተከሳሾች በአካል አለመቅረባቸውን ዘጋቢያችን ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ባስቻለው ችሎት ፖሊስ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲያውል የአምስት ቀናት ጊዜ ፈቅዶ ሰጥቶ ነበር። የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ለፖሊስ የደረሰው ከትላንት በስቲያ መሆኑን አቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። “ከቦታው ርቀት አንጻር በቂ ጊዜ ይሰጠን” ሲልም በዛሬው ችሎት አመልክቷል።

ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትናንት ምሽት በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 7 ኪሎ ግራም ወርቅና የተለያየ መጠነ ያለው 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የ8 አገራት ገንዘቦች በቶጎ ዉጫሌ ኬላ መያዙን የገቢዎችና ጉምሩክ አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia