ከባድ የመኪና አደጋ ተከሰተ‼️
በ21 #ቦሆሮ_ቀበሌ ልዩ ስሙ #አሚድ በተባለ ቦታ #ከጧቱ 1፡00 አካባቢ በተከስተ #የመኪና_አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 2 (ሁለት) የሰዉ ህይወት ማለፍና ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት መዉድም መድረሱን ለመስማት ተችሏል።
ምንጭ፦ North Wollo RayaKobo Communication Office
@tsegabwolde @tikbahethiopia

ምስራቅ ዕዝ~መከላከያ‼️
ሰራዊቱ ከህዝቡ ጋር የጀመረውን ሰላምና ልማትን የማስቀጠል ስራዎችን #በተጠናከረ መንገድ እንደሚያስቀጥል የምስራቅ ዕዝ አመለከተ። 7ኛውን ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀንን በማስመልከት በህዝባዊ ውይይቶች፣ በጽዳት ዘመቻና በሌሎች በጎ እድራጎት ስራዎች በመከበር ላይ ነው።
የምስራቅ ዕዝ የኢንዶክትሬሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮረኔል ፍስሐ ተክለሐይማኖት ዛሬ እንደገለጹት በዓሉ ሰራዊቱንና ህዝቡን የሚያገናኝ በዓል ነው። 7ኛው ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀን ባዓልም እስከ የካቲት 6 ቀን 2011 በምስራቁ አገሪቱ ክፍል በሚገኙ ዞኖች፣ክልሎችና አስተዳደር ከተሞች በፓናል ውይይት፣በጽዳት ዘመቻና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እየተከበረ ይገኛል፤ ሰራዊቱም የሰላምና የልማት ሐይል እንደመሆኑ ችግሮች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደርስ እንደከዚህ ቀደሙ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያከናውነውን የሰላምና የልማት ስራዎችን የሚያጠናክርበት እና የሚያጎለብትበት በዓል ነው።
በተለይ በተለያዩ አካባቢዎች በአዋሳኝ ስፍራዎች፣ በመልካም አስተዳደርና በሌሎች የተነሱት አለመግባባቶች በእርቅና እንዲፈቱ የሰላም አምባሳደር ወጣቶችን ከክልልና ዞንና አመራር አካላት ጋር በመመልመልና ስልጠና በስጠት እንዲፈቱ የሚደረግበት መሆኑን ተገልጿል። እንዲሁም በየቦታው የሚታዩ አለመግባባቶች፣ ስርዓት አልበኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ገንዘብ ዝውውርና ሌሎች በህዝቡ ላይ ጉዳት በሚያደርሱ ተግባራትን ከአመራሩና ከህዝቡ ጋር ሰፊ የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሮ ችግሩ የሚወገድበት መንገድ የሚመቻችበት እንደሆነ አመልክተዋል።
ሰራዊቱም #ህዝባዊነቱን የተቸገሩ ወገኖችን #የሚረዳበት፣ በሆስፒታል የሚገኙ #ህሙማንን የሚጎበኙበት በደም እጦት እናቶች ህይወታቸውን እንዳያጡ ደም የሚለግሱበትና ሌሎች የበጎ አድራጎስ ስራዎች የሚከናወኑበትና አለኝታነቱን የሚያስመሰክርበት ነው ሲሉ አብራርተዋል፤ ህዝቡም ከሰራዊቱ ጋር እየተወያየ በየአካባቢው እየታየ የሚገኘውን ሰላምን የማጠናከር ስራ ማጠናከር ይጠበቅበታል ብለዋል። “ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንንና ህዝባዊ ባህርያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን” በሚለው መሪ ቃል በሚከበረው 7ኛው ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀን በዓል የካቲት 7 ቀን 2011 በአየር ሐይል እና በኦሮምያ ክልል አዘጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት #በአዳማ ከተማ ይከበራል።
ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የሜቴክ አመራሮች ላይ ክስ ተመሰረተ‼️
ለሁለት ስኳር ፋብሪካዎች የውሃ መርጫ መሳሪያ ሳያስፈልግ በራሳቸው ፍቃድ እንዲገዛ በማድረግ ከ15 ሚሊየን ብር እንዲባክን አድርገዋል የተባሉ ሶስት ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመሰረተ።
ክሱ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ የወንጀል ችሎት ለተከሳሾቹ እንዲደርሳቸው ተደርጎ በችሎት ተነቧል።
ተከሳሾቹ 1ኛ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ የማኑፋክቸሪንግ እና ማሽን ግንባታ ስራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ተሰማ ግደይ፣ 2ኛ በሜቴክ ማኑፋክቸሪግና ግንባታ ስራ ምክትል ስራ አስኪያጅና የግብይትና ሽያጭ ክፍል ሃላፊ ሻለቃ መስፍን ስዩም እንዲሁም 3ኛ በንግድ ስራ የተሰማሩት አቶ ክፍላይ ንጉሴ ናቸው።
1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ከ2004 እስከ 2008 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ለፊንጫና ወንጂ ስኳር ፋብሪካዎች የውሃ መርጫ መሳሪያ ሳያስፈልግ በራሳቸው ፍላጎትና በወቅቱ የማምረት ፍቃድ ከሌለው ከ3ኛ ተከሳሽ ክፍላይ ንጉሴ ውል በመዋዋል ግዥ እንዲፈጸም ማድረጋቸው በክሱ ተጠቅሷል።
በዚህ መልኩ በተፈጸመ ያለአግባብ ግዥ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ እንዲባክን ማድረጋቸውን እና የውሃ መርጫ መሳሪያው እስካሁን አገልግሎት ላይ ሳይውል መቀመጡ በክሱ ተመላክቷል።
ተከሳሾቹ የተነበበላቸው ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመመልከት ችሎቱ ለየካቲት 6 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ FBC

መቀለ🔝
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ልዑክ አባላት ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቀሌ ሲደርስ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል። የመቀለ 70 እንደርታ ደጋፊዎችም በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ተቀብለዋቸዋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ላይ መካሄድ የነበረበት እና በይደር ተራዝሞ የቆየው የፋሲል ከነማ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ሀሙስ ጥር 30/2011 ዓ.ም በተስተካካይ መርሃ ግብር ከቀኑ 9:00 በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
ምንጭ፦ የፋሲል-ከነማ-ስፖርት-ክለብ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ጉባኤው በሠላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን እና የፀጥታ ሃይሎችን ያሳተፈ ኮማንድ ፓስት መቋቋሙን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ ተናግረዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው እየሰጠ ያለው ድጋፍ አበረታች መሆኑን ጠቁመው፥ ይህ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የሀገሪቱን ብሎም የከተማዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት አኳያም ጉባኤው የራሱ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ፥ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጐን በመቆም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዩች ሲያጋጥሙት በስልክ ቁጥር፤ 011-126-43-77፣ 011-126-43-59፣ 011-827-41-51 ፣ 011-111-01-11 እና 991 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችልም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም በሚከተሉት መንገዶች ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፤
ከአየር መንገድ – ቦሌ ቀለበት መንገድ – ፍሬንድ ሺፕ – ጃፓን ኤምባሲ – ወሎ ሰፈር – ኦምሎፒያ – ፍላሚንጎ – መስቀል አደባባይ – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – 1ኛ/ ከፓርላማ መብራት – ሜክስኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ።
ከብሄራዊ ቲያትር – በፍልውሃ – በብሄራዊ ቤተ መንግስት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤
ከፓርላማ መብራት – ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፤
ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ከጦር ሃይሎች – በሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች፤
በኮካኮላ ድልድይ – በአብነት ተክለኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ፤
ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፥ ሳር ቤት በቴሌ አድርገው ቀለበት መንገድ በሳር ቤት ወደ ቄራ ጎተራ፤
የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፥ በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ ሲግናል – ቀለበት መንገድ ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ ቀለበት መንገድ – መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ – ቀለበት መንገድ መገናኛ አድዋ ጎዳና አዋሬ አራት ኪሎ – ከፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መጠቀም ይቻላል።
ከዚህ በተጨማሪም እንግዶች በአጀብ በሚያልፉበት ወቅት አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለፖሊስ አባላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ምንጭ፦ ፋና ብሮድስቲንግ

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች‼️
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ# እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑና አማራጭ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዘርዝሯል።
በዚህም መሠረትዝግ የሚሆኑት መንገዶች፦
1ኛ. ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦምሎፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድ ሺፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ ኤርፖርት
2ኛ. ከፓርላማ መብራት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ በፍልውሃ፣ ብሄራዊ ቲያትር፣ ሜክስኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ
3ኛ. ከፓርላማ መብራት፣ በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፣ ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን
4ኛ. ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
አማራጭ መንገዶች፦
• ከጦር ሃይሎች - በሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች፡፡
በኮካኮላ ድልድይ - በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ
• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ
ሳር ቤት በቴሌ አድርገው ቀለበት መንገድ
በሳር ቤት ወደ ቄራ ጎተራ
• የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች
በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ ሲግናል
ቀለበት መንገድ ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ
ቀለበት መንገድ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ
ቀለበት መንገድ መገናኛ አደዋ ጎዳና አዋሬ

ትብብር‼️
ኢትዮ ቴሌኮም(ዋናው መስሪያ ቤት) ውስጥ ወይም ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ በየትኛውም የስራ እርከን የምትሰሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ካላችሁ ወይም እዛው የሚሰሩ ወዳጆች ካሏችሁ በ @tsegabwolde መልዕክት አኑሩልኝ። ትብብራችሁ ያስፈልገኛል!

#update ለአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንም 41 እጩ አባላት፦
1.ዶክተር ሙላቱ ተሾመ- የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት
2.ዶክተር አሰፋ ፍሥሐ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
3. ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
4.ፕሮፌሰር ጥላሁን እንግዳ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
5.ፕሮፌሰር ይስሐቅ አሰፋ-
6. ዶክተር ጣሰው ገብሬ- የቀድሞው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት
7.ወይዘሮ መዓዛ ብሩ- ጋዜጠኛ
8.አምባሳደር ሸምሰዲን አህመድ- ዲፕሎማት
9. ዶክተር ኦባንግ ሜቶ - የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
10. ዶክተር መስፍን አርአያ - በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ
11.ወይዘሮ አማረች አግደው -አማካሪ
12. ኡስታዝ አቡበክር አህመድ - የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ አማካሪ
ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
13.ፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በእውቀት - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር
14.ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ - ፖለቲከኛና የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት
15.ወይዘሮ ራሔል መኩሪያ -
16. ዶክተር ያእቆብ አርሳኖ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
17. ዶክተር አረጋዊ በርሔ - ፖለቲከኛ
18. ዶክተር ደመቀ አጭሶ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
19. ዶክተር ካሳሁን ብርሃኑ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
20. ፕሮፌር ገብሩ ታረቀኝ - ፖለቲከኛ
21. ዶክተርያዕቆብ ኃይለማርያም - ፖለቲከኛ
22. ዶክተር በቀለ ቡላዶ - የቀድሞ ሜቴክ ዋና ዳይሬክተር
23. አቶ ሌንጮ ለታ - ፖለቲከኛ
24. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና - ፖለቲከኛ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
25. አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ - ፖለቲከኛ
26. አቶ ጉደታ ገለልቻ -
27. አቶ አበበ እሸቱ - ፖለቲከኛ
28. ዶክተር ጳውሎስ ሊቃ - የህክምና ባለሙያ
29. አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ -- የህክምና ባለሙያ
30. ፕሮፌሰር ፍሥሃጽዮን መንግሥቱ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
31. ዶክተር አበራ ደገፉ - መምህር
32. ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ - ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
33. አቶ የሺዋስ አሰፋ - ፖለቲከኛ
34. አቶ ውብሸት ሙላት - የህግ ባለሙያ
35. ፕሮፌሰር መቀለ ከተማ
36. አቶ ፋንታሁን አየነው
37. ወይዘሮ ወርቅነሽ ዳባ
38. ዶክተር ዳዊት መኮንን
39. ዶክተር ብርሃኑ በላይ
40. አቶ ዘገየ አስፋው
41. አምባሳደር አብዱል ዋሴ

ከ30 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ሊተላለፉ ነው‼️
.
.
በቀጣይ ስድስት ወራት ከ30 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች #ለማስተላለፍ ዝግጅት ላይ መሆኑን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር አስታወቀ።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ #ጃንጥራር_አባይ በምክር ቤቱ ቀርበው የሚኒስተሩን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው፥ በቀጣይ 6 ወራት ግንባታቸው የተጀመሩ የመኖሪያ ቤት ልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውቀዋል።
እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያም 44 ሺህ ቤቶችን ለማስተላለፍ ቢታቀድም በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ከ30 ሺህ በላይ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች እንብደሚተላለፉ ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በዚህም17 ሺህ የሚሆኑት የ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክት ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ የ20/80 መሆናቸውን ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልፀዋል።
በዚህ ዓመት የሚተላለፉት መኖሪያ ቤቶች አሁን ላይ ግንባታቸው በአብዛኛው ወደ ማለቁ ሲሆን፥ የአሳንሰርና የማጠናቀቂያ እቃዎች መግጠም እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መሰረተ ልማት ስራቸው እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ቀደም ሲል ሙሉ የቤቱን ዋጋ የከፈሉ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑ በመመርያ የተለየ ቢሆንም ከተከሰተው የዋጋ ጭማሪ አንፃር የቤቱን ሙሉ ዋጋ የከፈለ ተመዝጋቢ አለ ማለት አይቻልም ብለዋል።
በዚህም መሰረት በተለይም በ40/60 የቤቶች መርሃ ግብር ተመዝግበው በመቆጠብ ላይ የሚገኙ ፈላጊዎች 40 በመቶ መቆጠብ ከቻሉ በእጣው መካተት እንደሚችሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም 1 ሺህ 700 የኪራይ ቤቶች ግንባታ በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ እና በለቡ እየተካሄደ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።
ከዚህ ባለፈ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከወናቸውን ተጨማሪ ስራዎች ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ሚኒስትሩ ፥ ባለፉት ስድስት ወራት ተቋሙን እንደ አዲስ የማደራጀት፣ የአመራር ስልጠና እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ስልጠና መሰጠቱን አስታውቀዋል።
ከዚህ ውጪም በ6 ወሩ በከተሞች የስራ እድል ፈጠራ በአጠቃላይ ለ589 ሺህ 215 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል ያሉ ሲሆን፥ ይህም ከተያዘው እቅድ 62 ነጥብ 8 መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስርን ለመፍጠር በተሰራው ስራም በ6 ወራቱ የ8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የገቢያ ትስስር መፍጠር ተችሏል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ኢንተርፕራዞቹ 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር እንዲቆጥቡ መደረጉንም ገልፀዋል።
ለ103 ሺህ ጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሶችም ብድር እንዲመቻች መደረጉንም ነው ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት ያብራሩት።
የሊዝ አዋጅን በተመለከተም በአዋጁ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሊዝ አዋጁን የማሻሻል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።
በአሁኑ ወቅትም የሊዝ አዋጁ ክለሳ ተጠናቆ ለሚለከተው አካል መላኩን እና በቅርቡም ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
ሰነድ አልባ የከተማ መሬቶችን በተመለከተም በ6 ወራቱ ለ60 ሺህ ሰነድ አልባ መሬቶች ሰነድ ለመስጠት ታቅዶ ለ20 ሺህ 153 መሬቶች የህጋዊ ይዞታ ማረጋገጫ መሰጠቱን አስታውቀዋል።
የከተሞች ፎረምን በተመለከተም ከየካቲት 9 እስከ 14 2011 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እንደሚዘጋጅ የገለጹት ሚኒስትሩ ከ800 በላይ ከተሞች እንዲሳተፉ ይደረጋል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ህገ ወጥ ይዞታዎችን ስርዓት እንዲይዙ የማድረግ ስራ መሰራቱንም አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#ETHIOPIA
#ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ!
.
.
እኛ ያለ ኢትዮጵያ ቦዶ ነን፤ ኢትዮጵያም ያለኛ ባዶ ነች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ!
.
.
እኛ ያለ ኢትዮጵያ ቦዶ ነን፤ ኢትዮጵያም ያለኛ ባዶ ነች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራትን #ለማጠናከርና ለነዋሪዎቹና ለአባላቱ የቅርብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል 1ሺ 332 የሸማቾች ሱቆችን ለመገንባት ቦታዎች ተለይተው ወደ ግንባታ እየተገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #ሲሳይ_አረጋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ሱቆቹ የሚገነቡት በ243 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ ሲሆን፤ የግንባታውን ወጪ የሚሸፍኑት የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ይሆናሉ፡፡
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሰላም እየተፈጠረ ባለበት በምዕራብ ወለጋ ዞን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራውን ያለምንም ስጋት በአግባቡ እንዲጀምር የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ #ዘሪሁን_ተክሌ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ በዞኑ ውስጥ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ያስቸገረው የባንኮች ሥራ አለመጀመር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሰላምና መረጋጋት የተፈጠረ በመሆኑ ቀድሞ የነበረው ዘረፋና የመንገድ መዘጋት አይስተዋልም፡፡ አንዳች የሚያሰጋ ነገር ባለመኖሩም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለምንም ስጋት የገንዘብ እንቅስቃሴውን ማድረግ ይችላል ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሕገወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ የነበረ 24 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ሥር መዋሉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ሕገወጥ ዶላሩ አህመድ የሱፍ መሀመድ ከተባለ ተጠርጣሪ ጋር ጥር 27/2011 ዓ.ም ምሽት 2፡00 ሰዓት በክልል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ቅ/ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡
ምንጭ:- የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ:- የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ ማስጠንቀቂያ‼️
በኬንያ የአሜሪካ ኢምባሲ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት በምዕራባዊያን ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል #አስጠንቅቋል፡፡ ጥቃቱ በተለያዩ #የምስራቅ_አፍሪካ ሃገራትም ሊኖር እንደሚችል ኢምባሲው ገልጿል፡፡ በናይሮቢ በመናፈሻ እና በባህር ዳርቻዎች ላይ ባሉ ቦታዎች እና የውጭ ጎብኝዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ በተጨማሪ ብሪታንያ ዜጎቿ ወደ ሶማሊያ እና ኬንያ ድንበር እንዲሁም ወደ ባህር ዳርቻዎች አካባቢ እንዳይጓዙ የተጓዦች አማካሪ ገጿን አድሳለች፡፡
ምንጭ፦ አልጀዚራ

#update በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ለፀደቀው #እርቀ_ሰላም ኮሚሽንን ለመምራት ለፓርላማው 41 አባላት ያሉት እጩዎች ቀርበዋል፡፡
1. ብፅህ አቡነ አብርሃም - ከኦርቶዶክስ
2. ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ- ከካቶሊክ
3. ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ- ከእስልምና
4. ዶ/ር ቤተ መንግስቱ - ከወንጌላዊያን
5. ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ - ከወንጌላዊያን
6. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል - ከእስልምና ወጣት ምሁራን
7. አቶ ታምሩ ለጋ - ከኦርቶዶክስ ወጣት ምሁራን
8. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ - የቀድሞ ጠ/ሚንስትር
9. ዶ/ር ምህረት ደበበ - ከሀሳብ መሪዎች
10. መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ -ከሀሳብ መሪዎች
11. የተከበሩ የአለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን - ከምሁራን
12. ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ - ከምሁራን
13. ዶክተር አበራ ዴሬሳ - ከምሁራን
14. ዶክተር ኡባህ አደም - ከምሁራን
15. ፕሮፌሰር ደስታ ሓምቶ - ከምሁራን
16. ፕሮፌሰር አሰፋ ኃይለማርያም -ከምሁራን
17. ዶ/ር ደረጀ ገረፋ - ከምሁራን
18. አርቲስት ደበበ እሸቱ - ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች
19. ዶክተር ሙሴ ያእቆብ - ደራሲ
20. ወይዘሮ ብሌን ሳሕሉ - ታዋቂ የሕግ ባለሙያ
21. አቶ ታምራት ኪዳነማርያም - የሕግ ባለሙያ
22. ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም - ከሃገር ሽማግሌዎች
23. ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ - በደቡብ ኢትዮጵያ ታዋቂ የበጎ አድራጎት ሰው
24. አቶ አባተ ኪሾ - ከሲዳማ የሃገር ሽማግሌዎች
25. ካኦ ደምሴ - ከአገር ሽማግሌዎች
26. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ - ፖለቲከኛ
27. ደራሲ አያልነህ ሙላቱ - ከኪነ ጥበብ
28. አትሌት ደራርቱ ቱሉ - የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
29. ዶ/ር ግደይ ዘርዓጽዮን - ፖለቲከኛ
30. ፕ/ር አህመድ ዘከርያ - ከምሁራን
31. ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ - ከታዋቂ ሰዎች
32. ሡልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ - ከአገር ሽማግሌዎች
33. አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም - ከአትሌቶቶች
34. ልዑል በዕደማርያም መኮንን - ከታዋቂ ሰዎች
35. ወይ. ትርሐስ መዝገበ - ከበጎ አድራጎት
36. አቶ ዳሮታ ደጃሞ
37. አባ ገዳ ጎበና ሆላ
38. ዶ/ር ኃ/ማርያም ካሕሳይ
39. ዶ/ር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ
40. ዶ/ር ሰሎሞን አየለ ደርሶ
41. ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ
ምክር ቤቱ በቀረቡት ዕጩ አባላት ላይ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡