TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Alert ወላይታ ሶዶ‼️

ከሩፋኤል ዝቅ ብሎ ወይም ሀቢታት አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የአየሩ ሁኔታ ንፋስ የተቀላቀለበት በመሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጎታል። የአካባቢው #ህብረተሰብ እሳቱን ሙሉ በሙሉ #ለመቆጣጠር እና #እንዳይሰፋ ለማድረግ ከፍተኛ #ጥረት እደረገ ይገኛል። የሚመለከታችሁ አካላትም ይህን ጥቆማ ሰምታችሁ ትብብር እድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

©z(TIKVAH-ETH ወላይታ ሶዶ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሳቱ ሳይሰፋ መቆጣጠር ተችሏል‼️

አደጋውን ሳይሰፋ ለመቆጣጠር የሀቢታት አካባቢ ህብረተሰብ እጅግ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል። የከተማው እሳት አደጋ መኪና #ዘግይቶ ቢደርስም አደጋውን ለመቆጣጠር ጥረት አድርጓል። አደጋው የደረሰበት ሰፈር አቀማመጥ እንዲሁም እየነፈሰ ያለው ሃይለኛ ንፋስ አደጋውን ለመቆጣጠር ፈታኝ አድርጎት ነበር።

መረጃውን ያዳረሱት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የአካባቢውን ነዋሪ ላደረገው ርብርብ አመስግነዋል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በቴፒ በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች ተገደሉ‼️

በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች #መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

የግጭቱ መንስዔ ከሥልጣንና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዘ የማንነት ጥያቄ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ በፊት የፀጥታ ችግር በፈጠሩ ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ ያለመውሰድ እና የህግ የበላይነትን ያለማስከበር ግጭቱ ዳግም እንዲቀሰቀስ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ በከተማው አሁንም ውጥረት እንዳለና ቱኩስ እንደሚሰማ የከተማው ነዋሪዎች ይናግራሉ፡፡

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

የስራ ባልደረባውን #የገደለው የፖሊስ አባል #በጽኑ_እስራት ተቀጣ፡፡ በጋምቤላ ክልል ልዩ ቦታው ደንቦስኮ በተባለው አካባቢ ከምሽቱ 3፡00 በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ የስራ ባልደረባውን የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 3 ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ተከሳሹ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሲሆን ከሌሎች አስራ ሁለት አባላት ጋር ለግዳጂ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ሙኒ ከተባለ ቦታ የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ለማደር ተገኝው ባሉበት ወቅት ሰው ለመግደል አስቦ በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ ሁለት የስራ ባልደረቦችን አንደኛውን ሆዱ እና ሁለተኛውን ጭንቅላቱ ላይ በመምታት ደም ፈሷቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረጉ እና በ3ኛ ክስ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት በሌላ ሰው አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ 3ኛውን የስራ ባልደረባውን ተኩሶ ግራ ታፋውን በመምታት እንዲቆስልና የህመም ስሜት እንዲሰማው በማድረጉ በፈጸመው አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡

ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎትም ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM እንዳስታወቀው የህይወት አድን ሠራተኞች ከሁለቱ ጀልባዎች ተጨማሪ አስከሬኖችን በማግኘታቸው ትናንት 43 የነበረው የሟቾቹ ቁጥር ዛሬ ወደ 52 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። ድርጅቱ አንደኛዋ ጀልባ 130 ሰዎችን አሳፍራ ነበር የሚል እምነት አለው። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ያነጋገረው አንድ ከአደጋው የተረፈ የ15 ዓመት ወጣት ቁጥራቸው 80 ከሚሆን ኢትዮጵያውያን ጋር በአንደኛው #ጀልባ ተጭኖ እንደነበር ገልጿል። የጀልባዋ ነጂ ሞተሩ ከባድ #ችግር እንዳጋጠመው ከተናገረ በኋላ ጀልባዋ መስመጠም መጀመሯን እርሱ ግን ከባህር ውስጥ በጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ #ተጎትቶ መውጣቱን ወጣቱ ተናግሯል። ጦርነት እየተካሄደባት ቢሆንም ወደ #የመን የሚደረገው ስደት እንደቀጠለ ነው።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake Page Alert‼️

Status: fake!
Number of likes: 22,600

ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ፦ የኢትዮጰያ መከላከያ ሀይል Ethiopian Defense Force

via Eliyas Mesert Taye
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፋና ቴሌቪዥን!!

አሁን ከህ/ተ/ም/ቤት የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዓቢይ_አህመድ የሚያቀርቡትን ጥያቄዎች በቀጥታ እያስተላለፈ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስራ ላይ የምትገኙ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው እየቀረበላቸው ላለው ጥያቄ የሚሰጧቸውን ማብራሪያ ቀጥታ በፋና FM መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰድስት ወራት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌተናል ጀነራል ጥጋቡ‼️

ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀነራል #ጥጋቡ_ይልማ_ወንድማገኝ በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ አዛዥ በመሆን ተሾሙ። ሌተናል ጀነራል ጥጋቡ ከዚህ ቀደም በቦታው ሲያገለግሉ የነበሩትን ሌተናል ጀነራል በስግዬ ኦዎዬሲጊይሬን በመተካት ነው የተሾሙት። ጀነራል ጥጋቡ ከትናንት ጀምሮ ስራቸውን ተረክበው ስራ መጀመራቸወቅ ተነግሯል። ጀነራሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የ34 ዓመት ልምድ ያላቸው ሲሆን፥ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥም ማገልገላቸው ተገልጿል። የስራ ርክክብ በተከናወነበት ጀነራሉ የተሰጣቸው ተልዕኮው ፈታኝ ቢሆንም ከዳር እንደሚያደርሱ ተናግረዋል። በትምህርት ዝግጅታቸው በቢዝነስ አድሚስትሬሽን ሁለተኛ ዲግሪ፣ በሊደርሺፕ እና በወታደራዊ ሳይንስ የመጀመሪ ዲግሪ እንዲሁም በህግ ዲፕሎማ አላቸው።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት ዋነኛው ተዋናይ #መንግስት ነው። በተለይም በአገሪቱ የሚያጋጥሙ ማንኛቸውንም ችግሮችን ደግሞ መንግስት በሃይል ሳይሆን #በትእግስትና #በሰላም የመፍታት ተግባር ደግሞ ዋነኛው ተግባር ነው ብለዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tivahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከፓርላማ አባላት ለተነሱት ጥያቄ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ዴሞክራሲን ለመገንባት መንግስት አርቆ አሳቢና ሆደሰፊ መሆን አለበት

• 20 የሚጠጉ የታጠቁም ያልጠተቁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ተመልሷል፣ ይህንን እንደ ድል ማየት ያስፈልጋል፡፡ እሱን ድል ዘንግተን ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ ችግሮች ላይ ማተኮር የለብንም

• የቀረበው የሰላም ጥሪ የሰላም መርህን የተከተለ ነው

• ከሁሉም ፓርቲዎች ጋር ተመሳሳይ መርህን የተከተለ ድርድር ነው የተደረገው፡፡

• ውግያ አያስፈልግም፣ ለበርካታ ዓመታት ሲንዋጋ ቆይተናል፤ የጦር መሳሪያ ድምጽ መሰመት የለበትም፣ በሀሳብ እንወያይና እናሸንፍ ነው ያልነው

• ከውጭ የገቡት ፓርቲዎች ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚሰሩ አሉ፣ ያን የማያደርጉ አንድ እግራቸውን አዲስአባባ አንድ እግራቸውን ውጭ አድርገው የሚጫወቱ አሉ እሱ አካሄድ ውጤታማ አያደርግም፡፡

• በሀሳብ አሸናፊ ለመሆን ነው መስራት ያለብን፡፡

• ችግር እየፈጠሩ ከችግር ለማትረፍ የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ

• የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፊቷል፣ ረጅም ርቀት መሮጥ የማይችሉ ፓርቲዎች ትንፋሽ ያጥራቸዋል፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ያላቸው ምርጫ ሀሳብ ወዳላቸው ፓርቲዎች ሰብሰብ ማለት ነው

• ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ዴሞክራሲ ሰላም ነው የሚንሰረው፤ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነገር ሲኖር የማያደጋም እርምጃ እንወስዳለን

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia