ፎቶ🔝ርዕሰ መስተዳድር #ገዱ_አንዳርጋቸው እና ርዕሰ መስተዳድር #ለማ_መገርሳ በኔዘርላንድ በሚገኙ ኩባንያዎች ያደረጉት ጉብኝት።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ዩጋንዳ የፖሊስ አመራሮችና አቃቤ ሕጎች የሶስት ቀናት አውደጥናትን ዛሬ #በኤርትራ_አስመራ ተጀምሯል፡፡ አውደጥናቱ የፖሊስ የኮሙኒኬሽን ስርዓትና የሕግ ማዕቀፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ውይይት እንደሚያደርግ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል በቲዊተር ገፃቸው በኩል ገልጸዋል፡፡
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የነዳጅ ምርቶች ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል‼️
በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት እና በህዳር ወር ተደረገው ዋጋ #ማስተካከያ ዝቅተኛ በመሆኑ፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ #መጠነኛ_ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም መሰረት፡-
•ቤንዚን በሊትር 19 ብር ከ69 ሳንቲም የነበረው 20 ብር ከ19 ሳንቲም
•ነጭ ናፍጣ በሊትር 17 ብር ከ78 ሳንቲም የነበረው 18 ብር ከ03 ሳንቲም
•ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 15 ብር ከ41 ሳንቲም የነበረው 15 ብር ከ66 ሳንቲም
•ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 14 ብር ከ90 ሳንቲም የነበረው 15 ብር ከ15 ሳንቲም
•እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 20 ብር ከ62 ሳንቲም፣
•ቤኒዚን ኢታኖል ድብልቅ በሊትር 19 ብር ከ89 ሳንቲም እንዲሁም ኬሮሲን በሊትር 18 ብር ከ03 ሳንቲም ሆኗል፡፡
የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ከነገ ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚሆንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 22/2011 ዓ.ም.
በሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ #መሃመድ_ዑመርን ጨምሮ በ47 ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመስርቷል።
.
.
ለከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትን ‹‹ቪ8›› መኪኖች በሌሎች አዳዲስና ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች የመተካቱ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው #አለመረጋጋት እና የተቃውሞ ቀናት ጉዳት ሳይደርስበት በሀሰት ጉዳት የደረሰበት በማስመሰልና ይህንን የሃሰት ፎቶ በማህበራዊ ድረ ገፅ በመልቀቅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
.
.
በቅርቡ የፀደቀውን የስደተኞች አዋጅ በመቃወም በአዲስ አበባና በጋምቤላ #የተቃውሞ_ሠልፍ ሊደረግ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
በሶማሌ ክልል ግጭት፣ ግድያና ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የነበረው #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን "ግዴታዬን እወጣለሁ ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ!" በሚል መርህ ቃል የከተማ አቀፍ የታክስ ንቃናቄ መድረክ ተካሂዷል።
.
.
ከኮንሶ ዞን ወደ ሶያማ ቡርጂ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ላይ ባልታወቁ #ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በትላንትናው ዕለት የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።
.
.
#በምሥራቅ_ወለጋ_ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም መለገሳቸውን የነቀምቴ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
.
.
የመልካም አስተዳደርና የሥራ አጥነት መሠረታዊ ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ የሚያግዝ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናግረዋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ #በማራገብ ሂደት #ፖሊስ እና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ተብሏል።
.
.
15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በጂቡቲ ተጀምሯል፡፡
.
.
ትናንት በሶማሌ ክልል መዲና- ጅግጅጋ የሃይማኖት ክብረ በዓልን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
.
.
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው #በኔዘርላንድ የሚገኙ ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል።
.
.
የኢትዮጵያ #ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሚበሩበት አዉሮፕላን የቴክኒክ #እክል ገጥሞት መዘግየቱ ተሰምቷል።
.
.
ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምት በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 11 ሺህ ሊትር ነዳጅ መያዙን የኢሉገላን ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል በአምሀራ ሳይንት ወረዳ በአጅባር ከተማ በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ስራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ #ምትኩ_በየነን ጨምሮ አምስት ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
.
.
የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ዩጋንዳ የፖሊስ አመራሮችና አቃቤ ሕጎች የሶስት ቀናት አውደጥናትን ዛሬ #በኤርትራ_አስመራ ተጀምሯል፡፡
.
.
በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት እና በህዳር ወር ተደረገው ዋጋ #ማስተካከያ ዝቅተኛ በመሆኑ፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ #መጠነኛ_ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ምንጭ፦ etv፣ fbc፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ ኢዜአ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

#update ከትራንስፓርት ሚንስቴርና ከሌሎች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የሉኡካን ቡድን የጅቡቲ ወደብን ጎበኘ። በጉብኝቱ ወቅት ስለወደቡ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በጂቡቲ ወደብ ላይ የሚያጋጥመውን መጨናነቅ ለመቅረፍ በተለይም የነዳጅ፣ ማዳበሪያና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች በፍጥነት ማመላለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክሯል። የትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የሉኡካን ቡድኑ ወደ ጅቡቲ መምጣት የአገራቱን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ በቅንጅት ለመስራት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️
ለፌደራሉ መንግስት
ለደቡብ ክልል መንግስት
ለሀገር መከላከያ
ለፌደራል ፖሊስ
.
.
የክልሉ መንግስት እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት በቴፒ ያለውን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለTIKVAH-ETH አሁን የተላኩ መልዕክቶች ያስረዳሉ። ሁኔታዎችን አሁን ካሉበት ወደሌላ ደረጃ ሳይሸጋገሩ መንግስት #መፍትሄ_ሊያበጅ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

Audio
#update ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል። የተኩስ ልውውጡ የተፈፀመው በምዕራብ ጉጂ በምትገኘዉ ዱግዳ ዳዋ ወረዳ እንዲሁም በምሥራቅ ጉጊ ሰባ ቦሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል። አቶ ጂራታ የተባሉ የዱግዳ ዳዋ ወረዳ ነዋሪ ተከሰተውን ሁኔታ ለVOA አስረድተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንታርቲካ በረዶ መቅለጥ ስጋት እየሆነ ነው‼️
በቅርቡ በአንታርቲካ ጥናት ያካሄደው የአሜሪካ ብሄራዊ አካዳሚ ሳይንስ ተቋም እ.አ.አ ከ1979 ጀምሮ ለአለፉት 40 አመታት በአካባቢው የበረዶ መቅለጥ በየ አመቱ በ6 እጥፍ እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል፡፡
ተቋሙ የአለማችን የሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣትን በምክንያትነት ጠቅሶ ከ1979-2017 ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ የባህር ጠለል በ 1.4 ሴንቲ ሜትር ከፍ እያለ መምጣቱን በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
ተመራማሪዎቹ በቅርቡ በ 18 የአንታረቲካ ቦታዎች በመርከብ በመዘዋዎር ባካሄዱት ጥናት በአካባቢው በየጊዜው የበረዶ መቅለጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን አረጋግጠዋል፡፡
የአንታርቲካ የበረዶ መቅለጥ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በቀጣይ ጥቂት አመታት ውስጥ የባህር ጠለል መጠን በከፍኛ መጠን እንደሚጨምርና በአለም ላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆችም ዋነኛው የአደጋ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ጨምረው አስቀምጠዋል፡፡
በዚህ መሰረት ተመራማሪዎች ከ1979-1990 ድረስ የአንታርቲካ የበረዶ ግግር በየአመቱ በአማካኝ 40 ቢሊዮን ቶን እንደሚቀንስም አረጋግጧዋል፡፡
ከ2009 ወዲህ ለአለፉት አመታት ከነበረው 6 እጥፍ በላይ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱም ተረጋግጧል።
ሌላው በዘርፉ ጥናት የአካሄደው የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ተቋም በበኩሉ የሳተላይት አሰሳዎችንና የአውሮፕላን ቅኝቶችን በማድረግ የተለያዩ ፎቶ-ግራፎችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ የሁኔታውን አሳሳቢነት በመጠቆም፤ በቀጣይም የአለምን የአየር ንብረትን በማስተካከልና የበረዶ መቅለጥን በመቀነስ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ቀደም በመስኩ የተካሄዱ ጥናቶች ወደ ፊት እ.አ.አ በ 2100 በባህር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ከተሞች ቅድመ ጥንቃቄ ካልተድገላቸው በጎርፍ እንደሚጠቁና ብዙ ነዋሪዎችንም ከመኖሪያ ቀያቸው ሊያፈናቅል እንደሚችል ሰጋታቸውን ማስቀመጣቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡ አልጄዚራ

#update ሳውዲ አረቢያ የፀረ-ሙስና ዘመቻዋን እንዳጠናቀቀች አስታወቀች። ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ በፀረ-ሙስና ዘመቻው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር አሊ-አላሙዲንን ጨምሮ በመቶዎች ሚቆጠሩ የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባላት እና ቢሊየነር ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል። የባህር ሰላጤዋ ንጉሣዊ ግዛት አስተዳዳሪዎች እንደሚሉት በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት 87 ግለሰቦች የቀረበባቸውን ክስ በማመናቸው ከመግባባት ላይ ተደርሷል። 8ቱ የቀረበባቸውን ክስ ስላላመኑ ጉዳያቸው ለአቃቤ ሕግ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን የ56 ሰዎች ጉዳይ ደግሞ ውሳኔ ያላገኘ የወንጀል ክስ ስላለባቸው ጉዳያቸው አልተጠናቀቀም ተብሏል። የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከቀናት በፊት ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። ሳዑዲ ወደ 200 የሚጠጉ ልዑላንን፣ ሚንስትሮችን እና የንግድ ኃላፊዎችን ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከቡ 'ዘ ሪትዝ ካርልተን' ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር አቆይታ ነበር። የፀረ-ሙስና ዘመቻው የተጀመረው ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው እየጨመረ በመጣው በልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ነው።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የፀደቀውን #የስደተኞች_አዋጅ በመቃወም ነገ በጋምቤላ ከተማ ሊደረግ ለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ #ከልክሏል።
via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ሺህ ነጋዴዎች ግብር ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ግብር ስረዛው ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከፍተኛ የግብር ተመን ተጥሎባቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩትን ነጋዴዎች ያካትታል፡፡ ሰረዛው የተደረገው የከተማው ገቢዎች ባለስልጣን የታክስ ንቃናቄ መድረክ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ሌሎች ውሳኔ የተላለፈባቸው እና ገና በሂደት ላይ የሚገኙ 1 ሺህ 780 ነጋዴዎች ደሞ ዕዳ እንዲሰረዝላቸው እና ክሳቸው እንዲቋረጥ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጋር ምክክር ተጀምሯል።
via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትናንት ከሪል ስቴት አልሚዎች በመከሩበት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ የሪልስቴት ዘርፉ የከተማውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እንደ አጋዥ ፕሮጀክት የሚጠቅም መሆኑን ገልጸው፤ የከተማ አስተዳደሩ ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል እስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል፡፡
Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ‼️
አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ ሊጀመር መሆኑን የማዕከላዊ እስታስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ።
ቆጠራው የሚጀመረው ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 20 ሲሆን ቤት ለቤት በመሄድ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የማዕከላዊ አስታስቲክስ ዋና ዳሬክተር አቶ #ቢራቱ_ይገዙ እንደለጹት፣ ለቆጠራው የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል።
የአሁኑን ቆጠራ ከሌሎች ጊዜያቶች ቆጠራ የሚለየው የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ቆጠራው ሲካሄድ በአርብቶ አደር አካባቢና በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ከተያዘው የመደበኛ ጊዜ ዘግይቶ የሚደረግ ሲሆን በአሁኑ ግን በተመሳሳይ ጊዜ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ነው የተገለጸው።
በተጨማሪም ባለፉት የቆጠራ ጊዜያቶች አንድ ቋንቋ ብቻ በመጠቀም ቆጠረው ይካሄድ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ገድሞ አምስት የክልል ቋንቋዎቸን በመጠቀም ቆጠራው እንደሚካሄድም ተጠቁሟል።
ለዚህም ስራ በሁሉም ክልሎች 1መቶ 82ሺህ በላይ ለሆኑ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
ምንጭ፦ ኢዜአ

አሳ ዛኝ ዜና‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።
የጃማ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ አደጋ መርማሪ እንደገለጹት ሲኖትራክ ተሽከርካሪው በቶ ከተባለ ስፍራ በጫነው አሽዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደጎሎ ከተማ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር አደጋው ያጋጠመው።
ተሽከርካሪው በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ 14 ቀበሌ ልዩ ቦታው ዝግባ ከሚባል ስፍራ ሲድርስ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በግምት 60 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ በመግባቱ አደጋውም መከሰቱንም አስረድተዋል።
በአደጋው የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ11 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ዋና ሳጅን ተስፋው ነጋ አስታውቀዋል።
ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 13 ሰዎች ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር መላካቸውን ዋና ሳጅን ገልጸዋል፡፡
ዋና ሳጅን ተስፋው አሸዋና ድንጋይ ላይ ሰዎችን መጫን እየተለመደ እየመጣ በመሆኑ በቀጣይ ባለሀብቶችና ሹፌሮች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውን ከጃማ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ fbc