ድሬዳዋ🔝
በድሬዳዋ ከተማ ሰኞ ከሰዐት በኅላ #የተቀሰቀሰው አለመረጋጋትትና ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።
ዛሬ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች የከተማው ከንቲባ ከሀላፊነት እንዲነሳ የጠየቁ ሲሆን አግላይ ነው ያሉትን የከተማዋን የስልጣን ኮታ ድልድል መመሪያም አውግዘዋል።
በፌድራል መንግስት እንደተረቀቀ የሚነገረው የስልጣን ድልድል ኮታ፣ 40% ለሱማሊ ብሔር የከተማው ነዋሪዎች፣ 40% ለኦሮሞ እና 20% ለቀሪው ነዋሪ ያከፋፍላል።
ዛሬ በከተማው የኢንተርኔት አገልግሎት #የተቋረጠ ሲሆን፣ የንግድና የትራንስፖርት አገልግሎትም በአብዛኛው የከተማው ክፍል የለም።
በድሬዳዋ ከተማ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው ወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን በማምራት ላይ በነበረ ታቦት ድንጋይ መወርወራቸውን ተከተሎ መሆኑን የከተማው ከንቲባ በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል።
via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በድሬዳዋ ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ #ከሥልጣን_እንዲወርድ ጠየቁ። ተቃዋሚዎቹ ጎማዎች በማቃጠል እና ድንጋይ በመደርደር መንገዶችን ለሶስተኛ ቀን ዘግተው ውለዋል።
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Leul
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በተመለከተ ከክልሉ ጋር እየሰራን ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
.
.
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ አርብ ጥር 17 ቀን ከሰዓት በኋላ በሰጠው መግለጫ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች ተነስቶ ከነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ሳከናውነው የቆየሁትን ምርመራ #አጠናቅቄያለሁ ብሏል።
በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ተመስገን_ላጲሶ በበኩላቸው ለምርመራው መነሻ የሆነው ከሐምሌ 28 እስከ 30 2010 ዓ.ም የተፈፀሙ ወንጀሎች ቢሆኑም በምርመራው ሂደት አቶ አብዲ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንድንመረምር የሚያስችሉ ማስረጃዎችን አግኝተናል ብለዋል።
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ምርመራውን ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የመረጃ ደህንነት ጽሕፈት ቤት በጋራ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል።
ኃላፊው ምርመራው አምስት ወራት የፈጀው የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የተሳተፉበት በመሆኑ ይህ ወንጀሉን ውስብስብ ማድረጉን አስረድተዋል።
ከሶማሌ ብሔር ውጭ የሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ነበሩ ባሏቸው ጥቃቶች የተሳተፉ ናቸው የተባሉ 46 ተጠርጣሪዎችን ሕገ መንግሥትን ለመናድ በመሞከር፣ በማነሳሳት፣ በአስቃቂ ግድያና በአስገድዶ መድፈር ከሰናል ብለዋል ኃላፊው
ይሁን እንጂ ከተከሳሾቹ መካከል በቁጥጥር ስር ውለው የሚገኙት ስድስት ብቻ ናቸው። ሌሎቹ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ተደብቀው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
አቶ ዝናቡ በቀድሞው የክልሉ መንግሥት በተደራጀ እና በተጠና መልኩ ዕቅድ ተይዞ እና አስፈላጊ የሰው ኃይልም ቀርቦ የተከናወኑ ናቸው ባሏቸው ጥቃቶች በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል፣ ከዚህም ውስጥ በእሳት በማቃጠል፣ አንገት በመቅላት መግደል፣ እንዲሁም በህይወት እያሉ መቅበር ተከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል።
"የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ዑመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምርመራ ሪፖርቱ ተረድተናል" ያሉት አቶ ዝናቡ ከፌዴራል የሚመጣ ኃይልን እንመክታለን በሚል የክልሉ ኃላፊዎች ያስተባብሩ እንደነበርም ገልፀዋል።
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንደተናገሩት የ58 ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 50 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል ብለዋል። እርሳቸው እንዳሉት አርባ ሁለቱ አንድ ላይ፣ ስምንቱ ደግሞ ሌላ ቦታ በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል። በተጨማሪ ሌሎች 200 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ቢገኙም የእርሱ ምርመራ ገና አልተጠናቀቀም።
በምርመራ ተደረሰበት በተባለው ግድያም የኦርቶዶክስ እምነት ካህናት እና ምዕመናን በቤተ ክርስትያን ግቢ ውስጥ ተገድለዋል፤ ተቀብረዋል ተብሏል።
እንደ አቶ ዝናቡ 266 ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 10 ሴቶች ሄጎ በሚባለው ጥቃት አድራሽ ቡድን እና በክልሉ ልዩ ኃይል ተደፍረዋል፤ ይሁንና ይህ ቁጥር መደፈራቸውን የደበቁ ሴቶች የሚኖሩ በመሆኑ ከፍ ሊልም ይችላል ተብሏል።
የተዘረፈ እና የተቃጠለ ንብረት ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል ብለዋል አቶ ዝናቡ።
በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ስለዋሉት አቶ በረከትና አቶ ታደሰን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ምርመራውን የሚያከናውነው የአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ ነው፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አይደለም፤ ስለዚህ የምንለው የለም" ብለዋል።
አክለውም የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተም ካልተያዙ ሰዎች መካከል እንደሚገኙ አመልክተው፤ በመሆኑም ይህንን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራን ነው፤ ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል።
ከጅግጅጋ ብጥብጥ ተጠርጣሪዎች መካከል ደግሞ የተወሰኑት ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ እርሱን በተመለከተም ከክልሉ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል።
አሁን ባለው የምርመራ ሂደት አቶ አህመድ ሽዴ ከተጠርጣሪዎች መካከል እንደማይገኙበትም ጠቁመዋል።
ምንጭ:- BBC

#update በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፈተ። ከዛሬ ጥር 17 ቀን ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዝቢሽን ማዕከል በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል። አቶ ጌታቸውን ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነም ነው የተሰማው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከባድ #የሰብዓዊ_መብት_ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት 14 ሰዎች ላይ አቃቤ ሕግ ለቀዳሚ ምርመራ የጠየቀውን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ። ተጠርጣሪዎቹ በነ ጎህ አጽባሃ መዝገብ በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል በቁጥጥር ስር ከዋሉት 33 ሰዎች ዝርዝር መካከል ከ1ኛ እስከ 16ኛ ያሉት ናቸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ወጣቶች‼️
የዓመታት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸው #በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በድሬደዋ ወጣቶች ባካሄዱት ሰልፍ ጠየቁ፡፡
ወጣቶቹ በተለያዩ የከተማው አስተዳደር አካባቢዎች በመዘዋወር ባካሄዱት ሰልፍ ጥያቄያቸውን ባሰሟቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል፡፡
በዚህም ድሬዳዋ ሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች በፍቅር በአንድነትና በእኩልነት የሚኖሩባትን መሆኗን ጠቅሰው አብዛኛውን ወጣትና ህዝብ ያገለለ የመንግስት መዋቅርና አሰራር ሊፈርስ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በተግባር ላይ ያለው የፖለቲካ የስልጣን ክፍፍልና አሰራር የአብዛኛውን ህዝብና ወጣት ከልማት ተጠቃሚነት ያገለለ መሆኑን ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡
መዋቅሩ ወጣቱን ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር የዳረገው በመሆኑ በፍጥነት እንዲቀየር ጠይቀዋል፡፡
በሰልፉ የተካፈለው ወጣት ሰለሞን መክብብ በሰጠው አስተያየት የአስተዳደሩ ከንቲባ ወጣቶችን ለማናገር የያዙትን ቀጠሮ መሰረዛቸው በወጣቶቹ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ተናግራል፡፡
”እኛ ሁሉም ወጣቶች የሚሳተፉበት ውይይት ነው የምንፈልገው ፤ የወጣቶች ወኪል እየተባለ አዳራሽ የሚሰበሰበው እኛን ስለማይወክሉ የውክልና ውይይት አንፈልግም” ብሏል፡፡
”አንድም ባለስልጣን ቀርቦ #ያናገረን የለም፤ ከተማዋ መሪ የላትም፤ የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን” ያለው ደግሞ ሌላው የሰልፉ ተካፋይ ወጣት ሲሳይ አየለ ነው፡፡ በሁሉም መስክ አድሏዊነት የሌለው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ጠይቋል፡፡
የኢዜአ ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ እንደተመለከተው ዛሬ በከተማ የተካሄደው ሰልፍ ካለፉት ሁለት ቀናት የበለጠ አብዛኛውን የከተማው አካባቢ ያዳረሰ ነው። በነበረው ግርግር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና አገልግሎት መሰጪዎች መሰተጓጎላቸውን ተመልክቷል፡፡
በጤና ጣቢያዎችና በድል ጮራ ሆስፒታል የኢዜአ ሪፖርተር ባደረገው ቅኝት የተጎዱ ሰዎች ህክምና አግኝተው ሲመለሱ አይቷል፡፡
#የመከላከያ_ሠራዊት አባላት የወጣቶቹ ቁጣ በሰላማዊ መንገድ ለማብረድና ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት በሰልፍ አድራጊዎችና በሌላም ህብረተሰብ ዘንድ በአዎንታዊ ጎኑ ድጋፍ አግኝቷል፡፡
በአሁን ሰዓት ሰራዊቱ በድንጋይ የተዘጉትን መንገዶች በማጽዳት ለተሸከርከሪዎች ክፍት እንዲሆኑ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

#update በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገለጹ፡፡ በዞኑ ሻኪሶና ጎሮዶላ ወረዳ የትጥቅ ትግል ሀሳብ የነበራቸው 20 የኦነግ አባላት ትጥቃቸውን በማስቀመጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተመልሰዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንዱስትሪ ፓርኮች❓
ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር አልመው የተቋቋሙት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከፍተኛ #የሰራተኛ_ፍልሰት እየፈተናቸው ነው ተባለ፡፡ ከቀጠሯቸው ሰራተኞች በሩብ አመት ውስጥ እስከ 98 በመቶ መልሰው የለቀቁባቸው ፓርኮች መኖራቸውን ተሰምቷል፡፡
ለዚህ ዋናው ምክንያት ፓርኮቹ ተመርቀው ስራ ከጀመሩ በኋላ በአካባቢው የቤት ኪራይ በከፍተኛ መጠን #መጨመር ነው ተብሏል፡፡
የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለ3 ተከታታይ አመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ያደረገው የክዋኔ ኦዲት ግኝት እንደሚያሳየው በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሰራተኞች ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው፡፡
እንደ ምሳሌም በቦሌ ለሚ ቁጥር አንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ በ2008 ሩብ አመት ከተቀጠሩ ሰራተኞች 42 ነጥብ 5 በመቶ ለቅቀዋል፡፡
በ2009 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እድል ካገኙት 72 ነጥብ 3 በመቶዎቹ ስራውን ትተው ሄደዋል፡፡
በሶስተኛ አመት 2010 ዓ/ም ከቀደሙት ጊዜ በባሰ ሁኔታ የለቀቁት ሰራተኞች ቁጥር 98 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ያሳያል፡፡
እንዲህ ያለው የሰራተኞች ፍልሰት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተቋቋሙበት ዋና ዓላማ የሆነውን ለዜጎች የስራ እድል መፍጠርን ሳይሳካ እንዲቀር ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የፓርኮቹ ምርታማነትና የወጪ ንግዱ ላይም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ተነግሯል፡፡
ወሬውን የሰማነው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ የተደረገውን የክዋኔ ኦዲት ግኝትና የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎችን በተመለከተ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ሲመክር ተገኝተን ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ #ሌሊሴ_ነሜ እንዳሉት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ #የሚለቁ ሰራተኞች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደረገው ዋና ምክንያት የቤት ኪራይ መጨመርና የኑሮ ውድነት ነው ብለዋል፡፡
#የሐዋሳ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ ስራ በጀመረ ጊዜ 300 ብር የነበረው የቤት ኪራይ ከ1 ሺህ 100 ብር በላይ ሆኗል ብለዋል፡፡
የኑሮ ውድነቱ ሰራተኛው ፓርኩን ለቆ በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ላይ በቀን ሰራተኝነት ለማስራት እንዲመርጥ አድርጎታል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡ በመሆኑም መንግስት ለጉዳዩ እልባት በመስጠት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስራ በጀመሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 45 ሺ ሰራተኞች ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1