TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.4K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነጭ ሳር🔝

በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት ተነስቶ የነበረው እሳት #በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ #ሽመልስ_ዘነበ እንደገለፁት #የሀገር_መከላከያ_ሠራዊት እና #የፖሊስ_አባለት ባደረጉት ጥረት የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ እሳቱ የተነሳው "አርፋይዴ" ተብሎ በሚታወቀው የፓርኩ ክፍል ሲሆን 1ሺህ ሄክታር ያህል መውደሙን አቶ ሽመልስ ገልፀዋል ፡፡ #ጂቲዜድ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር እንዲውል የቁሳቁስ አቅርቦት እና አስፈለገውን ወጪ መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ Gamo Zone Adminstration office public Relation unit
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️የሚመለከተው አካል ለድሬዳዋ ከተማ #ትኩረት እንዲሰጥ የከተማይቱ ነዋሪዎች #እየጠየቁ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ🔝

በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሏል። በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶች በተቃጠሉ ጎማዎች፤ በእንጨቶች እና በተከማቹ ድንጋዮች ተዘግተዋል።

ፎቶ፦ S(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳዲስ ሹመቶች‼️

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የመንግስት ሀላፊነት ቦታዎች #ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ መሰረት፦

•አቶ ፍራኦል ተፈራ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ ማተቤ አዲስ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ እዮብ አወቀ የስደተኞና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

•ዶ/ር መብራህቱ ገ/ማሪያም የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ መስፍን ነገዎ የኮንስትራክሽን ስራዎ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ እስማኤል አሊሴሮ በሚንስትር ዴኤታ ማእረግ የሰላም ሚንስትር አማካሪ፣

አቶ ታምሩ ግንበቶ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በማረፊያ ቤት ቆይታችን #ሰብዓ_መብታችንን እና #ክብራችንን የሚነካ ድርጊት #ተፈጽሞብናል›› አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ



አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ ‹‹በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል›› ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሰብአዊ መብት አያያዛቸው እንዲከበርም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ እንደማይወስዱም ነው ተጠርጣሪዎቹ የገለጹት፡፡ በባሕር ዳር ቤት እና ዘመድ ስለሌለን ቤተሰቦቻችን ከአዲስ አበባ ተመላልሰው ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለማገዘ አይመቻቸውም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪ በማረፊያ ጣቢያው ዙሪያ #የተሰበሰቡ ወጣቶች ‹‹ወንጀለኛ፣ ሌባ እና ነብሰ ገዳይ በማለት #ክብራችንን እና ህገ መንግስታዊ መብታችንን የሚነካ ድርጊት ፈጽመውብናል:: በከተማዋ ያለው ድባብ ለደህንነታችን እና ጉዳያችንን በደንብ ተከታትሎ ለመከራከር እክል ይፈጥራል፤ ስለሆነም የክርክሩ ጉዳይ አዲስ አበባ ይታይልን›› ሲሉ ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡ ችሎቱም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ የተጠርጣሪዎቹን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ጉዳያቸውን በባሕር ዳር ሆነው እንዲከራከሩ ወስኗል፡፡

‹‹የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና አመራሮች ወንጀለኛነታችን ሳይረጋገጥ ጉዳዩን በማራገብ የደቦ ፍርድ እንዲደርስብን አድርገዋል›› ብለዋል፡፡ ለአብነትም አቶ በረከት በደብረ ማርቆስ ከተማ በወጣቱ የደረሰውን ሁከት እና ግርግር አንስተዋል፡፡

ጉዳዩን ያየው የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስፈላጊው ጥበቃ እና ክትትል ለተጠርጣሪዎቹ እየተደረገላቸው #በባሕር_ዳር_ማረፊ_ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በመወሰን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናገረ፡፡ ነገ ጥር 18፣2011 ዓ/ም በሁሉም የተቋሙ ቢሮዎች፣ዲስትሪክቶችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለ4ኛ ጊዜ ነፃ የስራ ዘመቻ እንደሚደረግም ከኮሚኒኬሽን ቢሮ ተሰምቷል፡፡ ነፃ የስራ ዘመቻው በበጀት አመቱ የቀሩ ውዝፍ ስራዎችን ያልተሰሩ የኤሌክትሪክ መስመሮች የጥገናና የስርጭት ስራዎችን ማጠናቀቅ ያስችላል ተብሏል። በወቅቱ ያልተፈቱ የህብረተሰቡ ቅሬታዎችም በነፃ የስራ ዘመቻው ትኩረት እንደሚሰጣቸው ሰምተናል፡፡በእለቱ በቢሮዎች መደበኛ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በመስክም ከኤሌክትሪክ መስመሮች ጋር የተነካኩና ያደጉ ዛፎች ይቆረጣሉ ፣ የዘመሙ ምሰሶዎች ይቃናሉ ቆጣሪዎችም ይገናኛሉ ተብሏል፡፡

Via SHEGER 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባምንጭ🔝የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ እየገመገመ ነው። በውይይት መድረኩ ላይ የጤና ሚኒስተር ዶ/ር #አሚር_አማን ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

"ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ የሱማሌ ክልል #ባለስልጣናትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት #ተጠናቋል"- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
.
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ዛሬ ከሰዐት በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት #እንዲጠፋ፣ ህገመንግስታዊ ስርዐትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ንብረት እንዲወድምና በተያያዥ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሌሎቹ 40 ግን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተሸሽገዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ዝናቡ ገለፃ ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በሀገር ውስጥ የተደበቁትንም አፈላልጎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች #ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ መብታቸውን #በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት አቶ ዝናቡ ህዝቡ የተሸሸጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሠላም_ይስጠን!

ሠላም ይስጠን እግዜር ገናና
#ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለሁ እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል ባ'ይኔ

እንደው አንዳንዴ ይገርማል
አረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን ከእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
ራስን መውደድ አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካ'ፋችን
ስናይ እየተጠማ ልባችን

አንቃን...

ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሠላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቀን ወዳጅ አ'ርገህ አንቀን
አንቃን

የት ይደረሳል
ምን ይወረሳል
ይብቃን
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ #ፈተና
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
.
.
ሠላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለሁ እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል ባ'ይኔ

በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜያዊ ከንቱ ዓለም
ዘላ'ለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን

አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሠላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቀን ወዳጅ አ'ርገህ አንቀን
አንቃን
የት ይደረሳል
ምን ይወረሳል
ይብቃን
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
#እግዚኦ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ ፈተና
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
#እግዚኦ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

ድምፃዊ #ጎሳዬ_ተስፋዬ
#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiop