TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኮሎኔል #አለበል_አማረ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ደህንነት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡

via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 16/2011 ዓ.ም.

የሶማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ አንድ የካቢኔ አባልን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮችን #ከኃላፊነታቸው አንስቷል።


በድሬዳዋ የጥምቀትን በዓል ተከትሎ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 84 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።


ድሬዳዋ ዛሬ በተቃውሞ ስትናጥ ውላለች። በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የጥይት ተኩስ ድምጽ ሲሰማ ውሏል። እስካሁን ድረስ በሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት በግልፅ የታወቀ ነገር ባይኖርም የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ተሰምቷል።


አባይ ኢንዱስትሪያል የልማት ማህበር በአማራ ክልል ደጀን ከተማ በ8.8 ቢሊዮን ብር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት ከቻይናው HY እና ከዴንማርኩ FLS ኩባንያዎች ጋር ሥምምነት ተፈራርሟል፡፡


የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ኦነግ ዛሬ እንደገና አምቦ ላይ #ዕርቅ ፈጽመዋል፡፡


ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን #ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች #ተስማምተዋል


የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ #ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። ሁለት ሰዎች ሞተዋል ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።


ዛሬ ዱራሜ ላይ በከፋ ዞን ለሞቱ የከንባታ ተወላጆች የሃዘን መግለጫ እና ሻማ የማብራት ፕሮግራም ተካሂዷል።


የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ጀምሯል፡፡


የጉምርክ አሰራርን #ሳያሟላ ወደ መቀለ ሊገባ የነበረ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።


ኮሎኔል #አለበል_አማረ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ደህንነት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ አብመድ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ ኢ.ዜ.አ.፣ fbc፣ የጀርመን ራድዮ፣ ዋዜማ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት


አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችንም ቸር ትደርልን!!
ጥር 16/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነጭ ሳር🔝በአርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ነጭሳር ብሔራዊ ፓርክ ምሽቱን በተከሰተ #የእሳት_አደጋ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይደመጥ‼️የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም የኬሚካል ኮርፖሬሽን የተበደረውን 3 ቢሊየን ብር በላይ ለሜቴክ አሳልፎ መስጠቱን ሰምቻለሁ ሲል ሸገር ሬድዮ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፍርሀት ደመና በድሬ ስማይ ስር‼️

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድሬዳዋ ከተማ ከባድ የጸጥታና የደህንነት ችግሮችን ተጋርጦባታል። የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት #አብዲ_መሀመድ_ኡመር ከስልጣንናቸው ተነስተው ክልሉ በሰላም እጦት የታመሰ ሰሞን ድሬዳዋም #ከፍተኛ የጸጥታ ችግር አጋጥሟት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታም መሞታቸው ይታወሳል።ይህ የሆነው ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች #በከፍተኛ_ስጋት ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ።

ስለጉዳዩ ዝርዝር ዋዜማ ራድዮ ያሰባሰበውን መረጃ ያንብቡት፦
https://telegra.ph/የፍርሀት-ደመና-በድሬ-ስማይ-ስር-01-25
የመከላከያ ቀን~የካቲት 7‼️

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

ዳይሬክተሩ ሜጀር ጄኔራል #መሐመድ_ተሰማ እንዳስታወቁት፣ በዓሉ ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ታማኝነታችንና ሕዝባዊ ባህርያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን›› በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ ‹‹ዓላማው ሠራዊታችን በሕገ መንግሥቱ የተሰጡትን ተልዕኮዎች መፈጸም የሚያስችል አቅም ዝግጁነት እንዳለው፣ በጎ ገጽታውን በማሳየት ከሕዝቡ ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ደኅንነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉ የሠራዊት አባላትን ለማሰብና የጀግንነት ክብር እንዲያገኙ ማድረግ ነው፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ ምክንያትም በተለያዩ ደረጃዎች የሚካሄዱ የፓናል ውይይቶች፣ ስፖርታዊ ዝግጅቶች፣ የበጎ ተግባር ሥራዎችና ወታደራዊ ትርዒቶች እንደሚኖሩ ታውቋል፡፡
የዘንድሮውን በዓል ለየት የሚያደርገው አገሪቱ #በለውጥ ሒደት ውስጥ መሆኗ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስፖርት🔝

ዛሬ ማለዳ በዱባይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታነህ ሞላ (2:03:34) ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ሲያሸነፍ፤በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡ በሴቶች ዘርፍ ኬንያዊቷ ሩት ቼብጌች ያስመዘገበችው ሰዓትም በሴቶቹ ፈጣን ሆኖ ነው የተመዘገበው፡፡ ለመጀመሪያ ተሳትፎ የአለም ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ያሸነፈው አትሌት ጌታነህ ሞላን ተከትሎ ሂርጳሳ ነጋሳ ሁለተኛ፤አሰፋ መንግስቱ ሶስተኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ ፤ከ5 እስከ 9 ያለውን ደረጃም የያዙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሆነዋል፡፡ በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኬንያዊቷ ሩት በመከተል ወርቅነሽ ደገፋ ሁለተኛ፤ወርቅነሽ ኢዶሳ ሶስተኛ፤ዋጋነሽ መነካሻ አራተኛ፤ስትታየሁ ለውጠኝ አምስተኛ፤ ራህማ ቱሳ ስድስተኛ፤ ሙሉሀብት ፀጋ ሰባተኛ እንዲሁም ሱሌ ኡቱራ ስምንተኛ በመውጣት በድጋሚ በዱባይ ማራቶን የበላይ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡

ምንጭ፦ አፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ፎሬን ፖሊሲ (Foreign Policy) በተባለ ህትመት አለምአቀፍ አሰላሳዮች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩና ጉዳዩ አዲስ አበባ እንዲታይላቸውም ጠይቀዋል፡፡ በምክንያትነት ደግሞ የጤና ችግርና የቤተሰብን ድጋፍ በቅርበት ለማግኘት በሚል አቅርበዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ‹‹ተመዘበረ›› ካለው የሀብት መጠን ከፍተኛነት አንጻር ዋስትና እንዳይሰጣቸውና እንዲሁም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በባሕር ዳር እንዲታይ ለፍርድ ቤቱ ጠይቋል፡፡ ምሥክሮችን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ስለሚያቀርብም የጉዳዩን በባሕር ዳር መታዬት ተገቢነት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የዋስትና መብታቸውን ከልክሎ በጥብቅ ጥበቃ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ወስኗል፡፡ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ዋስትና የከለከለው ፍርድ ቤቱ #የተመዘበረው ሀብት በአማራ ክልል ስለሆነ ጉዳዩ መታዬት ያለበት በባሕር ዳር እንደሆነም ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

በጥብቅ ጥበቃ እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ከነበራቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አንጻር መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል፡፡ #የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ አጠናክሮ እንዲያቀርብ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የዛሬ ውሎውን ችሎቱ አጠናቅቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia