ድሬዳዋ‼️
ድሬዳዋ ዛሬ በተቃውሞ ስትናጥ ውላለች። በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የጥይት ተኩስ ድምጽ ሲሰማ ውሏል። እስካሁን ድረስ በሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት በግልፅ የታወቀ ነገር ባይኖርም የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን DW ዘግቧል።
"እኔ በተገኘሁባቸው አካባቢዎች የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል አምቡላንሶች በተደጋጋሚ ከተለያዩ ቦታዎች ድምፅ እያሰሙ የተጎዱ ሰዎች ሲያመላልሱ ተመልክቼያለሁ" ሲል በከተማዋ የሚገኘው የDW ዘጋቢ ተናግሯል። በዛሬው ተቃውሞ በድሬዳዋ የሚገኘው የ05 ቀበሌ መቃጠሉን፤ ተሽከርካሪዎች መሰባበራቸውን እና ዝርፊያ መበራከቱን ዘጋቢው ገልጿል።
በነዋሪዎች ዘንድ ሥጋት በፈጠረው ኹከት ከድሬዳዋ ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚያመሩ እና የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተዘግተዋል፤ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጧል። የDW ዘጋቢ ተቃዋሚዎች ድንጋይ በመደርደር እና ጎማ በማቃጠል መንገዶች ዘግተው ተመልክቷል። በተቃውሞ የተሳተፉ ወጣቶች "ጥያቄ አለን። ጥያቄያችንን ሊመልስ የሚችል አስተዳደር ከሌለ አያስፈልገንም" ሲሉ ተደምጠዋል። የጸጥታ አስከባሪዎች ተቃውሞውን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ ቢተኩሱም በመላ ከተማዋ የተንሰራፋውን ኹከት መቆጣጠር የቻሉ አይመስልም። የDW የድሬዳዋ ዘጋቢ እንዳለው የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር።
በድሬዳዋ ግጭት እና ኹከት የተቀሰቀሰው ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም. የእግዚአብሔር አብ ታቦትን አስገብተው በሚመለሱ ምዕመናን ላይ ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ ነበር። በድሬዳዋ ቀበሌ 09 ተፈጥሮ ለነበረው ግጭት እና ኹከት ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን 84 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የገለጸው ፖሊስ ኹኔታው መረጋጋቱን ቢያስታውቅም ተቃውሞው ዛሬም እንደገና አገርሽቷል።
ነዋሪዎች በከተማዋ ከሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ለመከላከል የራሳቸውን እርምጃ ወደ መውሰድ መሸጋገራቸው ለዛሬው ቀውስ መነሻ ነው ተብሏል። በድሬዳዋ ከቀናት በፊት ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የከተማዋ አስተዳደር፣ የሐይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ መጀመራቸው ተነግሮ ነበር። የከተማዋ ከንቲባ እና የጸጥታ ኃላፊዎች በድሬዳዋ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎች ጋር ለመነጋገር ለዛሬ ቀጠሮ ይዘዋል የሚል መረጃም ተሰራጭቶ ነበር። ውይይቱ በታቀደለት ጊዜ ሳይካሔድ በመቅረቱ የአዲስ ከተማ አካባቢ ነዋሪዎች በተቃውሞ መንገዶች ዘግተዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update አባይ ኢንዱስትሪያል የልማት ማህበር በአማራ ክልል ደጀን ከተማ በ8.8 ቢሊዮን ብር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት ከቻይናው HY እና ከዴንማርኩ FLS ኩባንያዎች ጋር ሥምምነት ተፈራረመ፡፡ በ24 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው ፋብሪካ በቀን 5,000 ቶን ሲሚንቶ የመፍጨት አቅም አለው ተብሏል። ዓባይ ኢንዱስትርያል የልማት ማህበር በአማራ ክልል መንግስትና በግል ባለሃብቶች ጥምረት የተቋቋመ ኩባንያ ነው።
via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲከፍተኛ ተወካይ ፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋር ስብሰባ አካሂዷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ🔝
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ኦነግ ዛሬ እንደገና አምቦ ላይ #ዕርቅ ፈጽመዋል፡፡ የኦሮሞ አባ ገዳዎች በመሩት ባህላዊ የዕርቅ ስነ ሥርዓት ላይ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት #ሚልኪያስ_ሚደቅሳ (ዶ/ር)፣ ከኦነግ ደሞ ሊቀመንበሩ #ዳውድ_ኢብሳ ተገኝተዋል፡፡
እንደ ባህሉ ኮርማ ታርዶ በተከናወነው ስነ ሥርዓት ሁለቱ ወገኖች ያለፈውን ሁሉ ከኋላቸው ትተው ድጋሚ ደም በመካከላቸው እንዳይፈስ በዕርቅ መንፈስ በጋራ ለመሰራት ተስማምተዋል፡፡ ዝርዝር የስምምነት ነጥቦችም ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
ዛሬ ረፋዱ ላይ ግን የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ አለሙ ስሜ ኦነግ የሠራዊቱንና ትጥቁን ጉዳይ ለአባ ገዳዎች ትቻለሁ ማለቱ ለሰላም ቁርጠኛ አለመሆኑን ያሳያል ሲሉ ለሸገር ተናግረው ነበር፡፡
via wazemaradio

አፋር🕊ሱማሌ!!
ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን #ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች #ተስማሙ።
በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በውይይቱም የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ነው የተገለፀው።
ከዚህ ባሻገርም የተፈጠረውን ግጭት መንስኤ ለማጣራትና ግጭቱ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጣ የጋራ ኮቴ ተቋቁሟል።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኡስታዝ አቡበክር ሁለቱ ህዝቦች በሃይማኖት በባህል እና በጋብቻ ተሳስረው የኖሩ በመሆናቸው በመካከላቸው መሰል ግጭት መፈጠሩ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ስለሆነም የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በቀጣይ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይከሰትና ሰላምና ለማውረድ መስማማታቸውን ገልፀዋል።
ስለሆነም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከስምምነት ባሻገር ወደ ህብረተሰቡ ወርደው ለጋራ ሰላም መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው መንግስት በአካባቢው ግጭት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህ መሰረትም ከሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የግጭቱን መንስኤ ለማጣራት እና ዳግም እናዳይከሰት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህ ባለፈም መንግስት በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን ለሚሰራው ስራ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምንጭ፦ fbc

ፋሲል ከነማ‼️
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ #ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹ ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ በኃላ ወደ ጎንደር እየተመለሱ ጣራ ገዳም በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ነው የመኪና አደጋው ያጋጠማቸው።
በአደጋውም የሁለት ደጋፊዎች ህይወት ሲያልፍ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ደጋፊዎች ላይም የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።
በተሽከርካሪ አደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በጎንደር ሆስፒታል እና በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አስታውቋል።
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በደጋፊዎቹ ህይወት ማለፍ እና በደረሰው ጉዳት የተሰማውን መሪር ሀዘን ገልጿል።
“ለክለባቸው ሲሉ ህይዎታቸውን ያጡ ለክለባቸው ታምነው የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ደጋፊዎች ታሪካቸው በመላው የፋሲል ከነማና የስፖርት ቤተሰብ ስማቸው በወርቅ መዝገብ ተፅፎ እስከወዲያኛው ሲዘከር ይኖራል” ሲልም ክለቡ አስታውቋል።
Via FBC

ቅዱስ ጊዮርጊስ🔝የቅዱስ ጊዮርጊስ #ደጋፊዎች እና #ተጫዋቾች በፋሲል ከነማ ሁለት ደጋፊዎች ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia