TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን የአቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ጉዳይ በክልሉ ፍርድ ቤት እንደሚታይ ገለፀ። አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)ን በጥረት ኮርፖሬት ከደረሰ የሀብት ብክነት ወንጀል ጋር በተያያዘ ጠርጥሯቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገልጿል። የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዝግአለ ገበየሁ ዛሬ ረፋድ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ወደ #ባህር_ዳር መወሰዳቸውን አስታውቅዋል። የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈፀመውም በክልሉ በመሆኑ ጉዳያቸው በክልሉ ፍርድ ቤት እንደሚታይም ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት። ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት በግለሰቦቹ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችለኝን ከበቂ በላው መረጃ ሰብስቢያለሁም ብሏል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ጥንቅሹ በባሕር ዳር ከተማ እንደሚገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አረጋግጧል። የአማራ ክልል የሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኃላፊ አቶ #ዝግአለ_ገበየሁ "ሰዎቹ በክልላችን ውስጥ ገብተዋል በክልላችን ጊዜያዊ ማረፊያም ነው ያሉት" ብለዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጫዋቹ የገባባት አልታወቀም‼️

በ15 ሚሊየን ፓውንድ ካርዲፍ ሲቲን ለመቀላቀል ቅዳሜ ፊርማውን ያኖረው አርጀንቲናዊው አጥቂ #ኤሚሊያኖ_ሳላ በአነስተኛ አውሮፕላን ወደ እንግሊዝ ሲመጣ #የገባበት_አልታወቀም ተብሏል።

የ28 ዓመቱ እግር ኳሰኛ እሱን ጨምሮ ሁለት ሰዎችን በጫነችው አውሮፕላን መሳፈሩ ቢረጋገጥም 'ቻነል' የተባሉት ደሴቶች ጋር ከደረሱ በኋላ ግን አውሮፕላኗ #ደብዛዋ ጠፍቷል።

ተጫዋቹን ከፈረንሳዩ 'ናንት' የክለብ ሪከርድ በሆነ ዋጋ ያስፈረመው የፕሪምየር ሊጉ ካርዲፍ ሲቲ በተፈጠረው ነገር እጅግ ማዘኑን አስታውቋል።

የግዛቲቱ ፖሊስ በበኩሉ አደጋ ደርሶ ሊሆን ይችላል በተባለው ቦታ ከፍተኛ ፍለጋ ቢያደርጉም ምንም ዓይነት ማስረጃ ማግኘት እንዳልቻለና የፍለጋ ሥራውን ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል።

''አውሮፕላኑ ውሃ ላይ አርፎ ከሆነ የተሳፋሪዎቹ በሕይወት መገኘት ዕድል እጅግ የጠበበ ነው'' ብሏል ፖሊስ።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤሚሊያኖ የቀድሞ ቡድን ደጋፊዎች ደግሞ እርግጠኛ መረጃ ማግኘት ባይችሉም ከአሁኑ ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው።

የኤሚሊያኖ ሳላ ወላጅ አባት ሆራሲዮ ስለጉዳዩ ከጓደኛቸው እንደሰሙና ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል።

''ምንም የማውቀው ነገር የለም። እስካሁን የተፈጠረውን ነገር አላመንኩም። ጥሩ ዜና እንደምሰማ ተስፋ አደርጋለው።'' በማለት የልጃቸውን መምጣት እየተጠባበቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

የፍለጋ ሥራውን የሚመሩት ጆን ፊትዝጄራልድ በበኩላቸው የአካባቢውን የአየር ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የአውሮፕላኗን ተሳፋሪዎች በሕይወት ማግኘት የማይታሰብ ነው ብለዋል።

ምናልባት አውሮፕላኗ ውሃ ላይ አርፋ ቢሆን እንኳን የውሃው ቅዝቃዜ ከደቂቃዎች በላይ በሕይወት እንዲቆዩ አያደርጋቸውም ሲሉ አክለዋል።

ካርዲፍ ሳላን በክለቡ ታሪክ ውድ በሆነ ዋጋ ሲሆን ያስፈረመው፤ ትላንት ወደ ከሰዓት ከአዲሱ ቡድኑ ጋር ሥልጠና ይሠራል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር። በተከሰተው አደጋም ተጫዋቾቹ ስለተደናገጡ ለማክሰኞ ታስቦ የነበረው ሥልጠና መሰረዙን የክለቡ ዋና ኃላፊ ኬን ቾ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ‼️

የአማራ ክልል ስነ- ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በነ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ የሙስና ምርመራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የአማራ ክልል ስነ- ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዝግአለ ገበየሁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥረት ኮርፖሬት በ6 ካምፓኒዎች የአክስዮን ግዥ እና አንድ ካምፓኒ ሽያጭ በጥረት የቦርድ አመራሮችና በሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የአመራር ጥሰት በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱ በህግ እንዲጠየቁለት ኮሚሽኑን መጠየቃቸውን አስረድተዋል፡፡

ኮሚሽኑም ይህንን ጥቆማ በመቀበል በኦዲት መረጋገጥ ያለባቸው ኦዲት እንዲደረጉ በማዘዝ የ5 ካምፓኒዎች የኦዲት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ 2 ካምፓኒዎች በኦዲት ምርመራ ላይ መሆናቸውንም ጠቁሟል፡፡

በኦዲት ምርመራ ወቅትም ፡-

1. የአዋጭነት /feasibility/ ጥናት እና የዳሰሳ ጥናት ሳያካሂዱ የአክስዮን ግዥ መፈፀም፡፡

2. ከኮርፖሬቱ የፋይናንስ አሰራር ውጭ በፓርትነር በተመሰረቱ ካምፓኒዎች ያለምንም መያዣ ብድር በመስጠት ሃብት እንዲባክን ተደርጓል፡፡

3. በባለሙያ ከተጠናው የዋጋ ግምት በላይ የአክስዮን ግዥ በመፈፀም ድርጅቱ ላይ ጉዳት ማድረስ፡፡

4. ከውሉ ውጭ የፓርትነሩን የአክስዮን ድርሻ ጭምር ክፍያ መፈፀም በኋላም ያለምንም ምክንያት የጥረትን ድርሻ በዱቤ ክፍያ መሸጥ፡፡ የታዩ ችግሮች መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልፃል፡፡

በእነዚህ ምክንያቶች ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው ወደ ስራ ሳይገቡ የቀሩ ካምፓኒዎች መኖር በአብነት የቀረቡትም፡-

1. ላፓልማ የተባለ ማዕድን ለማምረት፦ ከተቋቋመ ድርጅት ምንም አይነት የካፒታል ዕድገት ባላሳየበት የአክስዮን ድርሻው 22በመቶ ማለትም ባለ1000 ዋጋ አክስዮን ብር 2200 ብር በመግባት 4 ሚሊየን 320 ሺህ ብር አላግባብ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

የዚህ ካምፓኒ የቀድሞ ባለቤቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸው የካፒታል ዕድገት ታክስ ባለመክፈል 1 ሚሊየን 296 ሺህ ብር ባለዕዳ ሆኗል፡፡

ለዚህ ፋብሪካ ግንባታ ተከላ የተገባ 17 ሚሊየን 45 ሺህ 379 ብር ላይ ሳይውል ለብልሽት ተዳርጓል፡፡ በዚህ ካምፓኒ ብቻ 22 ሚሊየን 661 ሺህ 379 ብር (ተመዝብሯል)ጉዳት ደርሷል፡፡

2. በየዳ ሰስቲካል ኬሚካል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

• አንድ የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤት ግለሰብ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ባደረገው ስምምነት በ7000 እጣ በጥረት ስም የተመዘገበ 700 ሺህ ብር አክስዮን ገዝቷል፡፡ ጥረት ግን የ1 ሺህ 400 እጣ ብር 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ክፍያ ፈፅሟል፡፡ በብድር ብር 564 ሺህ 298 ተከፍሏል፡፡ በመጨረሻም የጥረት ድርሻ ያለምንም ምክንያት በዱቤ ሽያጭ በድርጅቱ ባለቤት የትዳር ጓደኛ ተሽጧል፡፡ በዚህም 1 ሚሊየን 173 ሺህ 426 ብር ሳይመለስ ቀርቷል፡፡

3. ባሕር ዳር ሞተርስ መገጣጠሚያ አክስዮን ማህበር፦ የፖርትነር ውል ከመግባቱ በፊት ብር 4 ሚሊየን 90 ሺህ 63 ብር ብድር ተሰጥቷል፡፡ በኋላም ጥረት በአማራ ዲዛይን ቁጥጥር ባለሙያዎች ያስጠናው የካፒታል ግምት ብር 10 ሚሊየን 417 ሺህ 16 ብር ሆኖ እያለ የብድሩን ገንዘብ ጨምሮ ብር 24 ሚሊየን 760 ሺህ 230 እንደገዛ ተደርጓል፡፡ ይህ ፋብሪካ ግዥ ከፈፀመበት ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ምንም እንቅስቃሴ የለውም፡፡

4. ኢስታንቡል ጋዝ ማኒፋክቼሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፦ የአክሲዮን ግዥው በ3 የቱርክ ባለሃብቶች ተቋቋመ የተባለ ድርጅት ነው፡፡ ጥረት በዚህ ካምፓኒ 3 ሚሊየን 641 ሺህ 54 ብር የተከፈለ ካፒታል አለው፡፡ ድርጅቱ ግን ፈርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምንም ተጠያቂ አካል የለም፡፡ ይህ ድርጅት ህጋዊ ድርጅት ስለመሆኑ በመጣራት ላይ ነው፡፡

5. ደሴ መዳዶ ውሃ ፋብሪካ፦ በአሁኑ መጠሪያው ጃሪ ውሃ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 70 በመቶ የአክስዮን ድርሻ በብር 21 ሚሊየን ብር ግዥው በአዋጭነት ጥናት ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ባለቤቱም የባንክ ዕዳ ለመመለስ ባለመቻሉ አበዳሪው ዳሽን ባንክ የኩባንያውን አጠቃላይ ሃብት 9 ሚሊየን እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ኮሚሽኑ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በ5 ካምፓኒዎች ዙሪያ የኦዲት መረጃዎችን አጠናቅሮ ክስ የመሰረተ ሲሆን በዳሽን ቢራ ፍብሪካ እና ዱቬንቱስ በተባሉት ሁለት ካምፓኒዎች ላይ የምርመራ ሂደቱ እንደቀጠለ መሆኑን ጠቁሟል።

በአጠቃላይ ጥረት ኮርፓሬት እየተመራ የነበረው በክልሉ ህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በተወሰኑ ግለሰቦች እና ቡድኖች ፋላጎት መመራቱ ለጥፋት ዳርጎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኮርፖሬሽኑ አሰራር በውስጡ ላሉት ድርጅቶች ብድር የሚፈቅድበት አሰራር ቢኖርም ለሌሎች ካምፓኒዎችም ከመመሪያ ውጭ ብድር ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ በሁሉም ጉዳዮች ምርመራው ባይጠናቀቅም በተጠናቀቁት ጉዳዮች ክስ መመስረት የሚያስችል ማስረጃ በመኖሩ፤ አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች የድርጊቱ ሁሉ ዋና ፈፃሚና አስፈፃሚ በመሆናቸው እና ደፍሮ ቃለ መጠይቅ ማድረግ ባለመቻሉ፤ ጉዳዩ በተጓተተ ቁጥር እንደ ሌሎች ባለስልጣናት ምሽግ አስኪያዘጋጁ መጠበቅ ጉዳት ስለሚያስከትል፤ እና በሌሎች መሰል ምክንያቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቤልጅየሙ ጠ/ሚር ቻርልስ ማይክል ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2020 የአለም የኢኮኖሚ(አፍሪካ) ጉባኤን እንድታስተናግድ #ሥምምነት ላይ ተደረሰ። ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ መስራችና ሊቀመንበር ከሆኑት ከፕሮፌሰር ክላውስ ሻዋብ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ። በዚሁ ውይይታቸውም ቀጣዩን የዓለም ኢኮኖሚክ ጉባኤ ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ ሥምምነት ላይ ደርሰዋል። ጠ/ሚሩና ፕሮፌሰር ሻውብ ቁልፍ የሆኑ ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመፍታት በንግድ፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ፣ በሲቪል ማህበረሰብ ውስጥ የተቀናጀ አሠራርን አስፈላጊነትን መወያየታቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በረራው ተቋርጧል‼️

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ40 ዓመት በኃላ ወደ ሶማሊያ #ሞቃዲሾ ጀምሮት የነበረውን በረራ #ማቋረጡን ሸገር FM ዘገበ።

ተጨማሪ፦ ከትናንት በስትያ ዜግነቱ እንግሊዛዊ የሆነ ግለሰብ ከሞቃዲሾ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ በረራ ላይ #ተቀጣጣይ ነገር ይዞ ሊገባ ሲሞክር በኤርፖርት ጥበቃዎች #ተይዟል#ከአልሽባብ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ተብሎም ተገምቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ #ላልተወሰነ ጊዜ በረራውን አቋርጧል ሲል ሸገር ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዳቮስ~~ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ በዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ መደመር በተሰኘ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

• ፍልስፍናው በ3 ምሰሶዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

• የመጀመሪያው ዲሞክራሲን ማስፋፋት ሲሆን በዚህም ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ከመፍታት ጀምሮ በርካታ ገንቢ እርምጃዎችን ወስደናል፡፡

• በአገሪቱ ማራሚያ ቤት በአሁኑ ጊዜ አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለም፡፡

• በወሰድናቸው የለውጥ እርምጃዎች ምክንያት ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም፡፡

• የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩትን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚዎች አገር ቤት ገብተዋል፡፡

• በአገሪቱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል፡፡

• ባለፉት 9 ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ከማራሚያ ቤት ተለቀዋል፡፡

• ሁለተኛው ኢኮኖሚን ማበልጸግ ሲሆን በዚህ ሂደትም የግሉን ዘርፍ በስፋት እናሳትፋለን፡፡

• የወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን፡፡

•ኢትዮ ቴሌኮምን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና ሌሎችንም የኢኮኖሚ አውታሮች ለውጭ ኢንቬስትመንት ክፍት እያደረግን ነው፡፡

• የምህረት አዋጅን የመሰሉ ሕጎችን አውጥተን አሳሪ ህጎችን እየቀየርን ነው

• ሴቶችን በ50 በመቶ በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ ላይ እንገኛለን፡፡

• የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት፣ በቅርቡ የተቋቋመ የሰላም ሚኒስቴርና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛና ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች በሴቶች እንዲያዙ ተደርጓል፡፡

• የኢትዮጵያ ለውጥ በተቋማዊ እና የሕግ ማሻሻያዎች የታገዘ ነው፡፡

• ቀደም ሲል ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን በመክፈት ላይ እንገኛለን፡፡

• ሶስተኛው ምሰሶ ቀጣናዊ ውህደት ሲሆን ይህም ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ሰላምን ጭምር እንደሚያረጋግጥ እናምናለን፡፡

• ኢትዮጵያ ትልቅ ራዕይ ሰንቃ በለውጥ ላይ የምትገኝ አገር ናት፡፡

• ችግሮች ቢኖሩም ህዝቡ ከጎኔ እስካለ ድረስ የምፈራው ነገር የለም፡፡

• ይህ ለውጥ ወደ አገራችን ትልቅ ካፒታል ይዞልን ይመጣል ብለን እናምናለን፡፡

• እስክ 2021 የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከ8 በመቶ በላይ ዕድገት እያስመዘገበ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዳቮስ~ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በአለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ ነጥቦች ፡-

• ኢትዮጵያ ትልቅ ራዕይ ያላት ሀገር ናት

• የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማካሄድ ላይ ነን፤

• አንድም ጋዜጠኛ በእስር ቤት የለንም፤

• ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲመጡ ሁኔታዎችን አመቻችተናል፤

• መጪው ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን እየሰራን ነው፤

• የሴች ተሳትፎን ማሳደግ ችለናል፤ በታሪካችንም የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝዳንት ፓርላማችን መርጧል፤

• ኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከአፍሪካ ቀዳሚ ናት፤

• ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ሀገራችን በሁሉም መስኮች ጥልቅ ሪፎርም እያካሄደች ነው፤

• የሀገራችን ሪፎርም መሰረት የሚያደርገው መደመር የሚለውን ፍልስፍና ነው፤

• መደመር ማለት አብሮነት ወይም በጋራ አቅም መፍጠር ማለት ነው፤

• ሪፎርሙ ሀገራዊና የህዝቦችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው፤

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በጅግጅጋና አካባቢው #ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው #ወንጀል ዙሪያ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች #በቁጥጥር ስር የሚውሉ አካለትም መኖራቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ከሀምሌ 28 እሰከ 30 በሶማሌ ክልል በጅግጅግናና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ በጋራ ሲያደርጉት የቆዩትን የምርመራ ስራ አጠናቀዋል።

ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሄርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ዙሪያ የድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት ተጨማሪ ትልልቅ ወንጀሎች እንደተገኙ የታወቀ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ተጨማሪ ግለሰቦች መኖራቸውም ታውቋል።

የምርመራው ውጤት በመጠናቀቁም በቁጥጥር ስር ያሉትን የክልሉን የቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ሌሎች አካላት ላይ ክስ መመስረቱ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

የምርመራ ሂደትንና ውጤቱን በተመለከተም አርብ (ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም) በጠቅላይ ቃቤ ህግ ለጋዜጠኞች #መግለጫ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶ/ር አብይ እህት

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

ግለሰቧ #የአዲግራት_ከተማ ነዋሪ ናቸው። እድሜዬ 53 ነው ብለው ነግረውኝ በ1977 አም አካባቢ ወደ አሶሳ እንደሄዱ እና እዛም የትግራይ ሰዎችን አግኝተው ወደ ትግራይ እንዳቀኑ በስልክ አጫወቱኝ። ታሪካቸውን ሲቀጥሉም: "ትውልዴ ግን ከአጋሮ ትንሽ ራቅ ብላ የምትገኘው #በሻሻ ከተማ ነው። አባቴ አህመድ አሊ ሲባል እናቴ ደሞ #ትዝታ_ወልዴ ትባላለች። ዶ/ር #አብይ_አህመድ ታናሽ ወንድሜ ነው። ድሮ ስሜ ዘቢባ ይባል ነበር። ትግራይ ከመጣሁ በሁዋላ ግን ዘውዴ ወደሚል ቀይሬአለሁ። ዶ/ር አብይ ስራም ስለሚበዛበት እሱን ሳይሆን አባቴ በህይወት አለ ሲባል ስለሰማሁ እባክህ እሱን አገናኘኝ።"

ይህንን ኢንፎ ይዤ የዶ/ር አብይ ታላቅ ወንድም #ዳፊስ ጋር ደወልኩ። እሱም ታሪኩን በጥሞና ካዳመጠ በሁዋላ: "ይኸውልህ! እኔ እስከማውቀው ዘቢባ የምትባል ታላቅ እህት እንዳለችን አላውቅም። ለምንኛውም ከፋዘር ጋር ማታ አውርቼ ነገ እንመለስበት።"

በነጋታው: "በቃ ኤልያስ ጉዳዩን #ግደለው። እንደዚህ የምትባል እህት #የለችንም!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው #አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ
.
.
የቀድሞው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸው እንዳስደነቃቸውና በዚህ ደረጃ ያልጠበቁት መሆኑን አቶ #ጌታቸው_ረዳ ተናገሩ።

ለእስሩ ሌላ ምክንያት ካለ በግልጽ እንዲነገር የጠየቁት አቶ ጌታቸው ከሙስና አንጻር የሚጠየቁ ከሆነ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በመጨረሻው ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

በሁለቱ ግለሰቦች መያዝ ላይ አስተያየታቸውን የተጠየቁት የቀድሞው የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እስሩ ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸውምና ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሁሉንም ዝርዝር ነገሮችን አውቃለሁ ወይም በሁሉም ጉዳይ ላይ ተሳትፌያለሁ እንደማይሉ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ የአቶ በረከትና የአቶ ታደሰ የመታሰር ዜና ያልጠበቁት እንደሆነ ተናግረዋል።

"እንደፓርቲው ከፍተኛ አመራር እርምጃው አስደንቆኛል። ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳ በርካታ ሰዎች አሉ፤ መናገር የምፈልገው በረከትና ታደሰ ግን ከዚህ አንጻር በመጨረሻው ደረጃ ላይ ሊቀመጡ የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ስለማንም በእርግጠኝነት መናገር አልችልም።"

"ከዚህ በፊት በረከት ፀረ-አማራ አመለካከት አለው በሚል ሲከሰስ እንደነበር አውቃለሁ" ያሉት አቶ ጌታቸው "ቢሆንም እስሩ ከአንድ ብሔር ወይም ከሌላ ጋር የተያያዘ ነው አልልም፤ ይህ እስር በአብዛኛው ፖለቲካዊ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

ለእራሳቸው ይሰጉ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው በግላቸው ምንም ስጋት እንደሌላቸው ነገር ግን በእሳቸው ላይ የተቀነባበረ ክስ ቢቀርብባቸው ብዙም እንደማይደንቃቸው ተናግረዋል።

ጨምረውም ቢሆንም አመራሩ ይህን ያህል ይወርዳል ብለው ስለማያስቡ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገሮችን ያስተካክላሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።

በዚህ ወይም በዚያ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሰዎች ይኖራሉ ያሉት አቶ ጌታቸው ነገር ግን በረከትንና ታደሰን መክሰስ ግን የማይታመን ነው ሲሉ የተፈጠረባቸውን ስሜት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ተገቢውን ፍትህ ያገኛሉ ብለው እንደሚያስቡ ተጠይቀው ሲመልሱ "ያ ይሆናል ብዬ አላስብም። አንድ ሰው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ወይም የክልል ወይም የፌደራል መንግሥትን የሚተች በመሆኑ ለእስር የሚዳረግ ከሆነ፤ ተገቢውን ፍትህ ያገኛል ብሎ መጠበቅ በእኔ በኩል የዋህነት ነው። ቢሆንም ተገቢውን ፍትህ ያገኛሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia