ሀዋሳ🔝የደኢህዴን ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ምክኒያታዊ ወጣት ለሀገራዊ ለውጥ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው። የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከፊታችን ጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ይካሄዳል። የዘንድሮው የወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 እስከ ጥር 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ይሆናል። ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች የሊግ ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሚካሄድ ይሆናል።
@tsegabwolde @tiivahethiopia
@tsegabwolde @tiivahethiopia
#update የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ያዘጋጀው የእርቀ ሰላም መድረክ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ ላይም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ነው።
Via Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አደጋ ለመቆጣጠር የተንቀሳቀሰው ተሽከርካሪ እራሱ #ለአደጋ ተጋለጠ። ዛሬ ማለዳ ላይ ቁስቋም በተለምዶ ሳንባ ነቀርሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ሲንቀሳቀስ የነበረው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ተሽከርካሪ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ከቤት መኪና ጋር ተጋጭቶ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል። የዓይን እማኞች እንደዳሉት አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ተሳፋሪዎች ወደ ህክምና የተወሰዱ ሲሆን ለህይወት የሚያሰጋ አደጋ እንደዳልደረሰባቸው ገልጸዋል።
via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን🔝"የጉዞ አድዋ" የእግር ተጓዦች #ደብረ_ብርሀን ከተማ ገብተዋል።
ፎቶ፦ ጌትነት አሰፋ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ጌትነት አሰፋ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአለም ኢኮኖሚ ጉባኤ🔝ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሚሳተፉበት የ2019ኙ የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ በስዊዘርላንድ ዳቮስ መካሄድ ጀምሯል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጥቁር ገበያ ሽያጭ ሊቀርብ የነበረ #ነዳጅ ተያዘ‼️
ለጥቁር ገበያ ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ እና ግምቱ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ከህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ መያዙን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ «ትዕግስት ብሩክ ቶታል ማደያ» ውስጥ ጥር 12 ቀን 2011 ዓ/ም በ44 ጀሪካን 995 ሊትር ቤንዚን ከማደያው በመቅዳት ላይ እንዳሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተቀዳውን ከ11 ሺ ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ ቤንዚን እና ሌላ ሊቀዳበት የነበረ 44 ባዶ ጀሪካን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 29642 ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችም ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ እንደገለፁት የማደያው ሰራተኞች ቤንዚን በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ድርጊቱን ፈፅመዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም ልዩ ቦታው አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ ኮድ 3-47453 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከላይ ሲሚንቶ በማድረግ ከስር 63 ጀሪካን ቤንዚን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም ምዕራብ ሆቴል አከባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 80502 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በኮንትሮ ባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ እቃዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ ተይዘዟል፡፡
ፖሊስ መምሪያው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተሽከርካሪው ቢያዝም አሽከርካሪው ግን ለጊዜው እንደተሰወረ እና ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር ጌታነህ ገልፃዋል፡፡
ተሽከርካሪው ሲያዝ በርከታ ጣቃ ጨርቆች፣ 2ሺህ የሞባይል ቻርጀሮች፣ 3480 አይነቱ « ኑር ሴላ» የሆነ ሲጋራ እና 1ሺ የሪሲቨር ሪሞት ኮንትሮል ይዞ #ለማምለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ሀላፊው አስረድተዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ