TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ #በሀዋሣ ከተማ ይካሄዳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያሳዝናል...‼️

36 ሚሊየን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህፃናት #በድህነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ጥናት ተናገረ፡፡ ህፃናቱ የሚያስፈልጓቸው መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንኳን ማግኘት #ብርቅ ሆኖባቸዋል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ከ18 አመት በታች ከሆኑት ከ41 ሚሊየን ውስጥ 36 ሚሊዮኑ በድህነት ውስጥ እንዳሉ የስታትስቲክ ኤጀንሲ እና ዩኒሴፍ ጥናት አስረድቷል፡፡

ጥናቱ በተለያዩ ዘጠኝ ክፍሎች ተለይቷል፡፡ ድህነቱ በምግብ፣ በጤና፣ በውሃ፣ በንፅህና እና በመጠለያ እና በሌሎችም መስፈርቶች የሚገለፅ ነው ተብሏል፡፡

ይህንኑ የከፋ የህፃናቱን ድህነት ለመቀነስና መላ ለማለትም መንግስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የሚመለከታቸውም በሙሉ ጉዳዩ በጣም ትኩረት የሚያስፈልገው እንደሆነ አውቀው በርትተው መስራት እንዳለባቸው ጥናቱን ያወጣው ድርጅት አስረድቷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በብሄር ግጭት 890 ሰዎች ተገደሉ‼️

የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በምዕራብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #በብሔር_ግጭት ሳቢያ ቢያንስ 890 ሰዎች ተገድለዋል።

#ባኑኑ እና #ባቴንዴ በተባሉ ማኅበረሰቦች መካከል ግጭት የተከተሰተው ዩምቢ በሚባለው አካባቢ በሚገኙ አራት መንደሮች ውስጥ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው #ተፈናቅለዋል። ዩምቢ አካባቢ ባለው ግጭት ሳቢያ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ የሚሰጡት መጋቢት ላይ ይሆናል።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ 465 ቤቶችና ህንጻዎች ተቃጥለዋል፤ ፈራርሰዋልም። ከነዚህ መካከል ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋም፣ ገበያ እና የሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቢሮ ይገኙበታል።

ከተፈናቀሉት ሰዎች 16,000 የሚሆኑት የኮንጎ ወንዝን ተሻግረው በኮንጎ ብራዛቪል ተጠልለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባቼት፤ "ይህ አስደንጋጭ ግጭት ተመርምሮ ጥፋተኞቹ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው" ብለዋል። ኮሚሽኑ ምርመራ መጀመሩም ተመልክቷል።

ዩምቢ ለወትሮው ሰላማዊ ግዛት ነበር። በማኅበረሰቦቹ መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው፤ የባኑኑ ማኅበረሰብ አባላት ባህላዊ መሪያቸውን በባቴንዴ መሬት ለመቅበር በመሞከራቸው ነበር።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምርጫን ፌሊክስ ቲስኬዲ ማሸነፋቸው ቢነገርም ሌላው ተቀናቃኝ ማርቲን ፋያሉ "አሸናፊው እኔ ነኝ" ማለታቸው ይታወሳል።

ማርቲን ፋያሉ እንደሚሉት ከሆነ፤ ፌሊክስ ቲስኬዲ ምርጫውን ያሸነፉት ከቀድሞው ፕሬዘዳንት #ጆሴፍ_ካቢላ ጋር #ተመሳጥረው ነው። ሕዝቡ የሰጠው ድምጽ ዳግመኛ ይቆጠር ሲሉም ለፍርድ ቤት አቤቱታ አሰምተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጉዳይ በተመለከተ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ መክሯል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ‼️

ሰላማዊ ትግል ለማድረግ በመወሰን ወደ ሀገር ከገባን በኋላ ወደ ትጥቅ ትግል #የሚመልሰን ምክንያት የለም አሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ #አራርሶ_ቢቂላ

አቶ አራርሶ ቢቂላ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳስታወቁት፥ ኦነግ ያለፈውን እና ወደፊት የሚያጋጥሙትን እድሎች በማገናዘብ የትጥቅ ትግል ምእራፍን በመዝጋት ሰላማዊ ትግልን መርጧል፤ ይህንን ደግሞ የድርጅቱ አባላት፣ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ሀይል እና ደጋፊዎች አክብረው መቀበል አለባቸው ብለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከኤርትራ ወደ ሀገር ሲመለስም በታላቅ እምነት ራሱን ለመንግስት አሳልፎ በመስጠት ነው ሲሉም አቶ አራርሶ ተናግረዋል።

ኦሮሚያ ውስጥ በምንቀሳቀስበት ወቅትም ችግር አጋጥሞን አያውቅም ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ፥ መንግስት ሀላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እየተወጣ እንደነበረም ገልፀዋል።

ከኤርትራ የተመለሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጦር አርዳይታ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ በአሁኑ ወቅት ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛል።

በጫካ ውስጥ ታጥቆ ያለው የኦነግ ሀይል አርዳይታ ገብተው የነበሩ የኦነግ ጦር አባላት አያያዝ ላይ ጥያቄ ነበራቸው ያሉት አቶ አራርሶ፥ ወደ ማሰልጠኛ ካምፕ ከገባን በኋላ አያያዛችን መልካም ካልሆነስ የሚል ጥያቄ እንደነበረም አስታውቀዋል።

ይህ ጥያቄም መንግስት እና ኦነግ ባዋቀሩት የጋራ ኮሚቴ አማካኝነት የኦነግ ታጣቂዎችን ወደ ካምፕ ለማስገባት እየተደረገ የነበረው እንቅስቃሴ እንዲጓተት እና ግጭት እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል።

መንግስትም የሰጠው ጊዜ በመጠናቀቁ እና ከዚህ በኋላ አልታገስም በማለት የህግ የበላይነትን ለማስከበር የፀጥታ ሀይልን በማሰማራቱ የተፈጠረው ግጭት እስካሁን እንዲቆይ አድርጓልም ብለዋል አቶ አራርሶ።

በግጭቱ ጫካ ውስጥ ያሉ የኦነግ ታጣቂዎች፣ በህዝቡ እንዲሁም የኦሮሚያ እና የፌደራል መንግስት የፀጥታ ሀይሎች ህይወት መጥፋት እንዳልነበረበት እና ሁኔታው የሚያሳስባቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኦሮሞ ሀይሎች አንዱ አንዱን ለማዳከም የሚያደርጉት ጉዞ ጠላትን የሚያስደስት በመሆኑ ለችግሩ ትኩረት በመስጠት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ ለመቅረፍ እንደሚሰሩም ነው ምክትል ሊቀመንበሩ የተናገሩት።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ወደ ሀገር የተመለሰው ጦርነት ለመክፈት አይደለም ያሉት አቶ አራርሶ፥ አሁን የትግል ምእራፍ ተዘግቷል፤ በጫካ ያለ የኦነግ ሀይል ወደ ካምፕ አንዲገባ እንፈልጋለን ብለዋል።

እርስ በእርስ መጋጨት፣ መካሰስ፣ መወነጃጀል እና መተኳኮስ ቀርቶ አሁን የተገኘው ለውጥ መሬት መያዝ አለበት፤ ስለዚህ ችግሮቻችንን በውይይት እንፈታለን ሲሉም አስታውቀዋል።

ህዝቡ በተደጋጋዊ በኦዲፒ እና በኦነግ መካከል ያለው ግጭት እንዲቆም ሲጠይቅ ነበር ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ፥ አሁንም ቢሆን ጠላት እንደሚፈልገው ኦሮሚያ የጦርነት እውድማ ትሆናለች በሚለው ስጋት ሊገባን አይገባም ብለዋል።

ትልልቅ ችግሮችን እየፈታን መጥተናል፤ ሁለታችንም ለአንድ ህዝብ የታገልን በመሆኑ የቀሩ ትናንሽ ችግሮችንም በውይይት እንቋጫለን ሲሉም ተናግረዋል።

ስምምነታችን ስራ ላይ ውሎ በሁሉም አቅጣጫ የሚንቀሳቀስ የታጠቀ የኦነግ ሀይል ከምፕ ይግባ ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ፥ እንደ ድርጅት ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወስነን የመጣን በመሆኑ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካላቸው ካምፕ ከገቡ በኋላም ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል።

አቶ አራርሶ ቢቂላ አክለውም፥ “የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኦነግን አናግረው ወደ መንግስት በመሄድ አንድ ላይ ሊያገናኙን እቅድ ይዘዋል፤ ውይይቱም እንደሚሳካ እምነት አለን፤ የሚያሳልፉትን ውሳኔም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንቀበላለን” ብለዋል።

ከዚህ በኋላ ከሰላማዊ ትግል እና ውይይት ውጪ የታጠቀ ሀይል ጫካ ተቀምጦ ድንጋይ እየተንተራሰ የዛፍ ፍሬ እና ስር እየተመገበ መኖር መቆም አለበት፤ አንዱ አንዱን ማዳከምም አማራጭ አይሆንም ሲሉም ተናግረዋል።

በአንድነት በመሆን አሁን የተገኘውን ለውጥ ወደ ትክክለኛ የዴሞክራሲ ምእራፍ ማሻገር የሁላችንም ድርሻ ነው ሲሉም አቶ አራርሶ ቢቂላ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ fbc(OBN)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሰው ልጆች ፍቅር
ለሰው ልጆች ሰላም
ለሰው ልጆች በዓለም ዙሪያ ሁሉ
ሰላም ይሁን ምድሩ ሁሉ።

ፈጣሪ እስከዘላለሙ አፋቅሮ ያኑረን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የጨረቃ ግርዶሽ ይታያል‼️

ጨረቃ ሰሞኑን እጅግ ትልቅ ሆና በአለም ዙሪያ ታይታለች፤ ዛሬ ደግሞ በ10 ዓመታት አንዴ ብቻ የሚከሰተው የጨረቃ ግርዶሽ ይታያል፡፡ “ሱፐርሙን” በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ግዙፏ ሙሉ ጨረቃ ዛሬ #በግርዶሽ ውስጥ ትገባለች ተብሏል፡፡

የጨረቃ ግርዶሽ የሚፈጠረው ምድራችን በፀሀይና በጨረቃ መካከል ስትገባና የምድር ጥላ ጨረቃን #ሙሉ_ለሙሉ አልያም በከፊል ሲሸፍናት ነው፡፡

ዛሬ ማታ ይታያል ተብሎ የሚጠበቀው የጨረቃ ግርዶሽ ከ1 ሰአት በላይ ሊቆይ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

ጨረቃ ከወትሮ ወደ ምድራችን ደምቃና ቀረብ ብላ ትታያለች ተብሏል፡፡ የጨረቃ ግርዶሹ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ እና በአብዛኛው የአውሮፓ አገራት ሙሉ ለሙሉ የሚታይ ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ በከፊል እንደሚታይ መረጃው ያመለክታል፡፡

የአውስትራሊያ እና የእስያ አህጉራት የጨረቃ ግርዶሹን ለማየት አልታደሉም ብለዋል ተመራማሪዎች፡፡ ከዚህ በኋላ የጨረቃ ግርዶሽ ዳግም የሚታየው እኤአ በ2029 ነው፡፡

ምንጭ፡- ዴይሊ ሜይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዓድዋ እግር ተጓዦች ነገ ደብረብርሀን ይገባሉ!

ከአዲስ አበባ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም የተነሱት 48ቱ የዓድዋ የእግር ጉዞ አባላት ዛሬ የአፄ ምኒሊክ የትውልድ አገር በአንጎለላ ከተማ አድረው ነገ ደብረብርሀን ከተማ እንደሚገቡ የጉዞ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል፡፡

ከ1 ሺህ ኪ.ሜ በላይ የሚፈጀው የእግር ጉዞ ተጓዦች ስለፍቅርና የኢትዮጵያ አንድነት እየዘመሩ እስካሁን ከ100 ኪሎ ሜትሮች በላይ ተጉዘዋል።

ከሐረር ከዘመቱ 4 እግረኛ ተጓዦች ጋር የተቀላቀሉት 44 የአዲስ አበባ ዘማቾች መካከል ኤርሚያስ የተባው ተጓዥ በባዶ እግሩ ያለ ጫማ ከመነሻው እስከ አሁን በመጓዝ ላይ ነው።

ይድነቃቸው የተባለው ተጓዥ ደግሞ 30 ኪ.ሜ ገደማ እንደተጓዘ በደረሰበት የእግር ህመም ጉዞውን መቀጠል ተስኖት የዘመቻ ጓዶቹን ተሰናብቶ ወደ አዲስ አበባ በእግሩ ተመልሷል።

የጉዞ ዓድዋ ልጆች በሰንዳፋ በኩል አሌልቱን እንዳለፉ በጉዟቸው ላይ የአንድ ሽማግሌ ቤት የጭቃ ምርግ ስራ ያገዙ ሲሆን ሐሙስ ገበያ ላይ ደግሞ የአንድ ገበሬ ለአጨዳ የደረሰ ማሳን በደቦ አጭደው አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡

በየደረሱበት ከተማ ተጓዦች ለሚደረግላቸው አቀባበል በተለያዩ ቋንቋዎች ምርቃት እየተቀበሉና እየሰጡ ናቸውም ተብሏል፡፡

በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በኦሮምኛ እንዲሁም በሶማልኛ ቋንቋዎች ጋባዦቻቸውን ሲመርቁ እንግዳ ተቀባዮቹም በአማርኛ በኦሮምኛና ጉራግኛ ባህላዊ ምርቃት አድርገው፤ ቋንቋ መመራረቂያ እንጂ መራራቂያ መሆን እንደማይገባው አሳይተዋል።

ኢቢሲ እንደዘገበው በዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ 6 ላይ ገና ከጅማሬው የተላለፈው መልእክት "የምናቋርጣቸው የሀገራችንን መንደሮች እንጂ ድንበሮች አይደሉም" የሚል እንደሆነ የጉዞው አስተባባሪዎች አስታውቀዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት የአለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሊ ጋር ተገናኙ። የአለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያን በምግብ ደህንነት: በተመጣጠነ ምግብና በአቅም ግንባታ ዘርፎች እንደሚረዳ ጠ/ሚሩ አስታውሰዋል። የአለም የምግብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia