ሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት🔝
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው በሰበታ የሚገኘውን የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በጉብኝቱ ወቅትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ውይይት አደርገዋል። በቆይታቸውም በትምህርት ቤቱ አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ እና በመፍትሄዎቻቸው ላይ ምክክር ተደርጓል።
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሻለቃ መስፍን‼️
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በቀድሞው ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ የብረት ማኑፋክቸሪንግ ግንባታ ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሻለቃ #መስፍን_ስዩም ላይ የአስር ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ። ሻለቃ መስፍን ስዩም የቀድሞው ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኒፋክቸሪንግ ግንባታ ኢንዱስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅና የግብይትና ሽያጭ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ስልጣናቸውን በመጠቀም ያለግልጽ ጨረታ ግዥ በመፈጸም ተጠርጥረው ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️
የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡
የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም የፀጥታው ዋና ባለቤት ከሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በዓላቱ በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ለወንጀል እና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ የሰው ኃይል ማሰማራቱን ገልጿል።
በታቦት ማደሪያ ስፍራዎች በተለይም በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት ጃን ሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ተከፍተው አግልጋሎት የሚሰጡ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ፀበል በሚረጭበት ወቅትም በሚፈጠር ግፊያ ምዕመናኑ ጉዳት እንዳይደርስበት፣ ንብረቶቹ እንዳይሰረቁበት እንዲሁም ከስፍራ ወደ ስፍራ ሲንቀሳቀሱ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ተገልጿል።
የእምነቱ ተከታዮች በተለይ ወጣቶች ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ሁሉ በተደራጀ መንገድ ከፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ለበዓሉ በሰላም መከበር እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል።
ህብረተሰቡ በማንኛውም ወቅት ከፀጥታ ስራ ጋር ተያይዥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለከት እና ማንኛውንም የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 01-11-26-43-77 ፣ 01-11-26-43-59 ፣ 01-18-27-41-51፣ 01-11-11-01-11 አሊያም በ991 ነፃ
የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳ ዙሪያ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑንና አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ የማቆሚያ ስፍራዎችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡
ምንጭ፦ fbc

የህዳሴ ግድብ‼️
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኤልክትሮ ሜካኒክ ስራዎች በዘርፉ ዓለማቀፍ እውቅና ባላቸው የውጭ ኩባንያዎች በመሰጠቱ ህዝቡ #ጥራትን በተመለከተ ሥጋት #እንዳይገባው ተገለጸ።
ግድቡን አስመልክቶ ዛሬ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተሳታፊዎቹ ዋና ጥያቄ “ግድቡን እንዴት እንጨርሰዋለን እና ጥራቱስ እንዴት ይጠበቃል” የሚለው ነበር።
በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ የሰጡት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት በኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ላይ የነበረው የዓቅም ውስንነት እንዲሁም የልምድ ማጣት ችግር ኢትዮጵያ ብዙ ገንዘብ እንድትከስር ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
አሁን ግን ለሜቴክ ተሰጥቶት የነበረው ይህ ሥራ በዘርፉ ዓለም አቀፍ እውቅና ባላቸው የጀርመን፣ የፈረንሳይና የጣሊያን ኩባንያዎች በመተካቱ ህዝቡ በዚህ ላይ ምንም ዓይነት ሥጋት እንዳይገባው አሳስበዋል።
እስካሁን ለግድቡ የወጣው 98 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 10 በመቶው ከህዝብ በተገኘ ድጋፍ የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
ግድቡን አለመጨረስ አገራዊ ክስረት እንደሚያስከትል የገለጹት ኢንጂነሩ ህዝቡ የኔነት ስሜት ተሰምቶት ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል
ጠይቀዋል።
እስካሁን ግድቡ 65 በመቶ መጠናቀቁን እና በ4 አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል።
ምንጭ፦ etv

ጎባ🔝በነሀሴ ወር በጎባ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ለወራት በከተማው የሰፈነውን ውጥረት #ለማርገብ ያለመ #የዕርቅ ስነስርዐት ዛሬ በጎባ ስቴድየም ተከናውኗል። በስነስርዐቱ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት፣ አባገዳዎችና የሀይማኖት መሪዎች ተሳትፈዋል።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በሰዉ ህይወት መጥፋትና በማፈናቀል ወንጀል የተጠረጠሩ 60 ሰዎች መያዛቸዉን የኦሮሚያ መንግስት ገለፀ።
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ለሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደገለፀዉ ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ፈፅመዋል የተባሉት በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት ደግሞ በቤንሻንጉል ክልል ከማሼ ዞን ነዉ። እንደ ቢሮዉ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ዉለዋል።
ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋሏቸዉ የኦሮሚያና የከቤንሻንጉ ጉምዝ ክልሎች ከምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት ጋር በጋራ መሆኑንም ቢሮዉ አመልክቷል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

በአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን ነዳጅ እጥረት #እንዲከሰት እና #እንዲባባስ በሚያደርጉ ነዳጅ #አቅራቢዎች እና አከፋፋዮች ላይ አስፈላጊውን #ክትትል እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በቂ ነዳጅ እያለ ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን እጥረት እንዲከሰት እና እንዲባበስ በመደረጉ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በከተማችን ነዳጅ ለማከፋፈል 120 ገደማ የሚሆኑ የነዳጅ ማደያዎች በህግ አግባብ ፈቃድ መውሰዳቸው እየታወቀ 106ቱ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ጥር 8 ቀን 2011 ዓ/ም በስራ ላይ ከሚገኙ 106 የነዳጅ ማከፋፈያዎች መካከል 100 ማደያዎች ላይ በተደረገው ክትትል 54ቱ በቂ የቤንዚን እና የናፍታ፣ 5ቱ የቤንዚን ብቻ፣ 8ቱ የናፍታ ክምችት ያላቸው ሲሆን 30 ማደያዎች ደግሞ ነዳጅ ማራገፍ ሲገባቸው ያላራገፉ በመሆኑ፣ ቀሪዎቹ ሙሉ ለሙሉ ዝግ ሲሆን አንዳንዶች ለእረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ጊዚያዊ የቤንዚን እጥረት መከሰቱን ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡
እጥረቱን ለማባባስ ልዩ ልዩ ምክንያች እንዳሉ በተደረገው ክትትል ማወቅ ሲቻል አንዳንድ የማደያ ሰራተኞች ከህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ነዳጅ በተለይ ደግሞ ቤንዚን በበርሜል በመገልበጥ፣ በሞተር ብሰክሌትና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ከስፍራ ወደ ስፍራ በማጓጓዝ በጥቁር ገበያ በከፍተኛ ዋጋ ሲሸጡ እንደተደረሰባቸው፣ እንዲሁም ሌሎች ሆን ብለው ነዳጅ በመደባቅ፣ ነዳጅ እያላቸው ለምሳና ለእራት ወጥተናል በሚል ሰበብ በመፍጠር ፣ የተወሰኑ ደግሞ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ሲገባቸው ያለበቂ ምክንያት በመዘጋታቸው የማደል ስራው እንዲስተጓጎል እያደረጉ መሆኑን ፖሊስ ገልፆ እጥረቱን ምክንያት በማድረግ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ህገ-ወጥ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ደርሶበታል፡፡
ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ያለበቂ ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ ማደያዎች በአስቸኳይ ስራቸውን እንዲጀምሩ እንዲሁም በጥቁር ገበያ ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ላይ ያሉ ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ አሳስቦ ነገር ግን ማሳሰቢያውን ተግባራዊ በማያደርጉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ ከላከው ዘገባ መረደት ተችሏል፡፡
መንግስት በልዩ ልዩ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለማረጋጋት በቂ ነዳጅ ወደ አዲስ አበባ እያስገባ በመሆኑ ከነዳጅ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥሙ ህገ-ወጥ ተግባራት ጥቆማ ለመስጠት ነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም 01-11-11-01-11 መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስተውቋል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ🔝
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ከፍተኛ የምክክር ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
via epa

ጃን ሜዳ🔝
በዛሬው እለት ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በጃን ሜዳ ተገኝተው ለጥምቀት በአል ሜዳውን አፅድተው ቆሻሻውን አቃጥለዋል። በዚህ ወቅት የለበሱት ነጭ ልብስ ሲሆን ከጀርባው "ዘረኝነት ይውደም! ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!" የሚል ጽሑፍ አለው። እነዚህ ወጣቶች "ፍቅር ያሸንፋል" የሚል ማህበር ያላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም የታላቁ አንዋር መስጂድና የራጉኤል ቤተክርስቲያን ሙስሊምና ክርስቲያን ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው በማፅዳት ቆሻሻንና ዘረኝነትን አቃጥለዋል። ወደፊትም ተመሳሳይ ተግባራትን እንደሚፈፅሙ እየተናገሩ ነው፡፡ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት!!!
via GETU TEMESGEN

ጋዜጠኛው ተገደለ‼️
በጋና #የሙስና_ቅሌትን በማጋለጥ የሚታወቀው የጋዜጠኞች ቡድን አባል የነበረው አህመድ ሁሴን-ስዋሌ ከስራ ወደ ቤቱ መኪና እያሽከረከረ ሲጓዝ በጥይት መገደሉ ተዘገበ፡፡
በጋና መዲና አክራ ከሞተር ሳይክል ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች 3 ጊዜ በጥይት ተመቶ የተገደለው የምርመራ ጋዜጠኛ በአገሪቱ በእግርኳስ ላይ በሰራቸው ዘገባዎቹ ዓለም አቀፍ እውቅና ለማትረፍ ችሎ ነበር፡፡
ቢቢሲን ጠቅሶ ኢቢሲ እንዳስነበበው ጋዜጠኛው ያጋለጣቸው የቀድሞ አገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሀላፊ የህይወት ዘመን እገዳ እንዲጣልባቸውም አስችሏል፡፡
ታይገር አይ በመባል የሚጠራውና በርካታ የሙስና ወንጀሎችን በማጋለጥ የሚታወቀው የምርመራ ጋዜጠኞች ቡድን መሪ ስለነበረው አናስ አርማያው አናስ ጋር ቢቢሲ የሰራውን ዶክመንተሪ ተከትሎ በርካታ ውዝግብ መነሳቱ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ BBC

#update በአማራ ክልል #ሰቆጣ_ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል #በሰላም እንዲጠናቀቅ ከተማ አስተዳደሩ ከወጣቶች ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ ለመስራት ዝግጅት መደረጉን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በሀይሉ መኮንን ገልጸዋል፡፡
Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia