TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አባ ገዳዎች🕊

"በሀገሪቱ #ዘላቂ_ሰላም እንዲሰፍን #የበኩላችን_አስተዋጽኦ እናበረክታለን"- አባገዳዎች
.
.
በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አስተያየታቸውን ለኢቢሲ የሰጡት የጉጂ አባገዳዎች ገልጸዋል፡፡

መንግስት በሀገሪቱ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲጠናከር ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ኦነግን ጨምሮ ባርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር በመግባት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ በኦሮሚያ በአንዳንድ አካባቢዎች ከሰላማዊ መንገዱ ውጭ በሚደረግ እንቅስቃሴ ከሰው ህይወት አልፎ፣ በአካል በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

አባገዳዎች እንዳሉት ሰሞኑን በኦሮሚያ የሰላም ሳምንት መታወጁን ተከትሎ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሰላማዊ ትግል ተቀላቅለዋል፡፡

የኦሮሞ አባገዳዎች ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ሳይወግኑ በኦሮሚያም ሆነ በአገሪቱ ሳላማዊ ፖለቲካ ትግል ብቻ ባህል እንዲሆን የጀመሩትን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) ከኦነግም ሆነ ከሌሎች ተፎካካሪ ፖለቲካ ድርጅቶች ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንዳለበትም አባገዳዎች አሳስበዋል፡፡

ኢቢሲ እንደ ዘገበው በኦሮሚያ በተለያዩ ስፍራዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በህብረተሰቡ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ላይ እክል መፍጠራቸውንም አባገዳዎች ጠቁመዋል፡፡

ሁሉም አባገዳዎች በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዲፍን የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዘዞ‼️

በአዘዞ ከተማ ለምን ዜጎች ከመተማ ይፈናቀላሉ በሚል ዛሬ ነዋሪዎች ከፀጥታ ሃይሎች ጋር መጋጨታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ነዋሪዎቹ እንደገለፁት ከቅማንት ድንበር አካባቢዎች የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በመኪና ተጉዘው አዘዞ ሲደርሱ ህዝቡ ወገኖቻችን ለምን ተፈናቀሉ በሚል ቁጭት መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሞውን እንደገለፀ ነው እኒሁ የአይን ምስክሮች ለጀርመን ድምፅ ራድዮ በስልክ የገለፁት።

ሌላዋ የዓይን ምስክር እንደገለፁት ምክንያቱን #በትክክል ማወቅ ባይችሉም በከተማዋ ከሰዓት በፊት ግርግር እንደነበር ጠቁመው ሁኔታውን የፀጥታ ሃይሉ ባጭር ጊዜ ማስቆሙን ተናግረዋል፡፡

ካለፈው ሐምሌ አንድ ጀምሮ በምዕራብ አማራ በተፈጠረው ግጭት በአካባቢው ሰብዓዊ ቀውስ መፈጠሩና እስካሁንም ችግሩ መብረድ እንዳልቻለ ሰሞኑን የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ሰሞኑን የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

በአሁን ሰዓት በጎንደር ከተማ ከጎሃ ሆቴል አጠገብ ምክንያቱ ምን እንደሆን ባይታወቅም የእሳት አደጋ ስለመድረሱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። የሚመለከተው አካል መልዕክቱን ተመልክቶ እሳቱ ሳይሰፋ እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት ችግር #በአጭር_ቀን ውስጥ #እንደሚፈታ ለመስማት ተችሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥቆማ‼️ በአሁን ሰዓት በጎንደር ከተማ ከጎሃ ሆቴል አጠገብ ምክንያቱ ምን እንደሆን ባይታወቅም የእሳት አደጋ ስለመድረሱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። የሚመለከተው አካል መልዕክቱን ተመልክቶ እሳቱ ሳይሰፋ እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር‼️

በጎንደር ከተማ ከጎሃ ሆቴል አቅራቢያ የተፈጠረውን የእሳት አደጋ ምክንያት እስካሁን ለማወቅ ባንችልም በአካባቢ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በአሁን ሰዓት እሳቱ በህዝቡ ርብርብ #መጥፋቱን ነግረውናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት የውጭ ቋንቋዎች ክፍል ዛሬ መደበኛ የፕሬስ መግለጫ አዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ወኪሎች ሰጠ። መግለጫውም በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮችና መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እያካሄዳቸው ባሉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ያተኮረ ነበር። ለሰላማዊ ውይይት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት የገለፁት የክፍሉ ኃላፊ በለውጡ የተገኙና የኢትዮጵያ ህዝቦች የተጎናፀፏቸውን የተለያዩ ነፃነቶችን መጠበቅና ማስቀጠል ንፁሀንን ከመከላከል ጎን ለጎን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ #የህግ_የበላይነትን በማስከበር የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ መሆኑን የአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች ተወካዮች ተናግረዋል።

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረሪ ክልል‼️

በሀረሪ ክልል ህገወጥነትና ስርአት አልበኝነት እንዲስፋፋ እያደረጉ ያሉ ሃይሎች እጃቸውን እንዲሰበስቡ የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ አሳሰበ።

ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ የህግ የበላይነት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የገለፀው ሊጉ በክልሉ የተጀመረው የለውጥ ስራ በሚፈለገው ፍጥነት ለማራመድ የህግ የበላይነት አለመከበር አዳጋች አድርጎታል ብሏል ባወጣው መግለጫ።

በክልሉ እየተስተዋለ ያለው ችግር የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ በፍቅርና በሰላም የመኖር ክልላዊ እሴቶችን የሚፃረር ተግባር መሆኑን አመልክቷል።

የህዝቡ የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ህልም እውን የሚሆነው የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ እንደሆነ ነው መግለጫው ያመለከተው።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ሊጉ በመግለጫው በክልሉ ህገ ወጥነትና ስርአት አልበኝነት በይዘቱና መጠኑ እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቁሟል።

በተለይም ካለፈው አመት ወዲህ የከተማ ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቤታቸውና ከይዞታቸው በጉልበት የማፈናቀል፣ አርሶ አደሮች ከማሳቸውና ከይዞታቸው ማፈናቀል፣ ህገወጥ የመንግስትና የህዝብ መሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታና ንግድ እየተስፋፉ ነው ብሏል።

እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ይዞታዎችን በሃይል የመውረር፣ የደቦ ፍትህ፣ አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የዜጎች የመንቀሳቀስ ፣ በሰላም የመኖርና የመስራት መብቶች መገደብ የዜጎችን ድህንነትንና የክልሉን ሰላም በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈታተኑት መሆኑን ጠቅሷል።

በተለይም ሰሞኑን በክልሉ በጥቂት ህገ ወጦችና ስርዓት አልበኞች የመንግስት መስሪያ ቤቶች ንብረት የማውደም እና የመንግስት ሃላፊ መኖሪያ ቤት ድረስ በመሄድ ጥቃት የመፈፀም እጅግ አሳዛኝ ተግባር መፈፀሙን ነው መግለጫው ያመለከተው።

በመሆኑም ህግን በሁሉም ላይ እኩል ተፈፃሚ በማድረግና ህግን ተላልፈው የሚገኙ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነት እንዲከበርና እንዲረጋገጥ የማድረግ ሀላፊነቱን እንደሚወጣ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

የህግ የበላይነት በማስፈን የህዝብና የክልሉን ፀጥታና ደህንነት ለማረጋገጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ህዝቡ ከሀብሊ ጎን በመቆም በክልሉ የተጀመረውን ለውጥ እውን ለማድረግ የማይተካ ሚናውን እንዲጫወት ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት🔝

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢኖቬሽን ቢዝነስ አክስለሬሽን (IBA Ethiopia) ጋር በመተባበር የአፍሪካ የኢኖቬሽን ሳምንት ከጥቅምት 17/2012 እስከ ጥቅምት 21/2012 ለማካሄድ ወስነዋል።

የኤግዚብሺኑ ዋና ዓላማ ወጣቶችን ብሎም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማስተዋወቅና ወደ ስራ እንዲገቡ
አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኢኖቬሽን ሳምንቱ መዘጋጀት ሚኒስቴሩ ለያዘው የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ስራ አጋዥ ይሆናል ብለዋል፡፡

በተለይ ለሴቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የአይ ቤ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ በዚህ ስራ ተሳታፊ ናቸው።

አቶ ሃይለማርያም የስራ አጥ ቁጥር መበራከት እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቴክኖሎጂ ማበልፀግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛ ኝ ዜና‼️

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ቁጥጥር ደህንነት የሥራ ሂደት ከፍተኛ ባለሙያ ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ለfbc እንደተናገሩት፥ አደጋው በትናነትናው እለት ነው የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ ተገልብጦ የደረሰው።

የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋም የ16 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 10 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲሁም 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱንም ኮማንደር ንጉሴ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የደቡብ ዞን የኦነግ ጦር #የሰላም_ጥሪውን መቀበሉ አባ ገዳዎችን በማሳተፍ የማይፈታ ችግር እንደሌለ ያሳያል›› - አቶ ሮባ ቱርጬ የጉጂ ዞን አስተዳዳሪ
.
.
የደቡብ ዞን የኦነግ ጦር የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በሰላማዊ መንገድ ትግል ለማድረግ መወሰኑ አባ ገዳዎችን በማሳተፍ የማይፈታ ችግር እንደሌለ ያሳያል ሲሉ የጉጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ #ሮባ_ቱርጬ ተናገሩ፡፡

አቶ ሮባ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጉጂ ዞን አባገዳዎች አማካኝነት የሰላም ሳምንት ታውጇል፡፡ በአካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረው የኦነግ ሠራዊትም የሰላም ጥሪውን ተቀብሏል፡፡ አባገዳዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነት አላቸው፡፡

በርካታ ችግሮች በነበሩበት ወቅትም ጭምር በውይይት በመፍታት ፋይዳቸው የላቀ ሲሆን፤ የአሁኑ ሁኔታም ይህን ያረጋግጣል፡፡ የደቡብ ዞን የኦነግ ጦር የቀረበለትን የሰላም ጥሪ መቀበሉ አባ ገዳዎችን በማሳተፍ የማይፈታ ችግር እንደሌለ ያሳያል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰዉ #ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ #ሳሙኤል_ጎችል_ወልደመስቀል በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555/ለ ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ ተላልፎ በፈፀመዉ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሽ በሌላ ሰዉ አካል ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ሰኔ 2 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 12፤30 ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ በግ ተራ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ የግል ተበዳይ አብርሀም ታፈረን በቦክስ በመምታት የላይኛዉ የፊት ለፊት አራት ጥርሶቹ እንዲወልቁ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመዉ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነዉ፡፡

ተከሳሽ ከላይ በክስ ዝርዝሩ አደረክ የተባልኩትን ድርጊት አልፈፀምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ቢሰጥም ዐቃቢ ህግ 4 የሰዉ ምስክሮችንና የሰነድ የማስረጃዎቹን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

መዝገቡን የተመለከተዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የየካ ምድብ የወንጀል ችሎትም ተከሳሽ ጥፋተኛ ነዉ ሲል ታህሳስ 08 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ 3ተኛ ወንጀል ችሎት በቅጣት ዉሳኔው ተከሳሽን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በ2 አመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

መጭው የጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲውል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር #ሰኢድ_አህመድ ለአብመድ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ የተጠናከረ ጥበቃ ይዳረጋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ወንጀል የሚፈጽሙ አካላትን ለመቆጣጠር የሰውር የወንጀል ክትትል አባላት አቅማቸው ከፍ እንዲል መደረጉንም ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

በጥምቀት በዓል የውጭ ሀገራት ጐብኝዎች ቁጥር ይጨምራል፤ጐብኝዎች በሚጓጓዙበትና በሚያርፉበት አካባቢ ልዩ ጥበቃ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ እንዳስታወቁት በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይኖራሉ፡፡

በዚህ ወቅት አሸከርካሪዎች በተዘጋጀላቸው አማራጭ መንገዶች መጠቀም አለባቸው ነው፤ ፍጥነታቸውን ቀንሰው ማሽከርከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

በዓሉን በማስመልከት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረግ የጦር መሣሪያ ተኩስ በህግ ያስጠይቃል፡፡ስለሆነም ከእንደዚህ አይነት ድርጊት መቆጠብ ተገቢ መሆኑንም አሣስበዋል፡፡

ህብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥም የሚችልን የወንጀል ድርጊት በስልክ ቁጥሮች 058 220 13 27 እንዲሁም 058 220 19 21 ደውሎ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

#የጥምቀት_በዓል ከመድረሱ በፊት የማዕከላዊ #ጎንደር ዞን የባሕል ሳምንት ያካሂዳል፡፡ የባሕል ሳምንቱም የአካባቢውን ትውፊታዊ ማንነት እና አጋጊያጥን ጨምሮ ለጎብኝዎች በጎዳና ላይ ትርኢት ያሳያል፡፡ የጎዳና ላይ ትርኢቱም የጥምቀት በዓል ከመከበሩ በፊት የሚካሄድ በመሆኑ የአካባቢውን ባሕል በአምባሳደሮቹ አማካኝነት ፍንትው አድርጎ በማሳየት ትልቅ ሚና እንደተወጣም ተነግሯል፡፡ ስምንተኛው የባህል ሳምንት ፌስቲባል በጎንደር ከጥር 7 እስከ 9/2011 ሲከበር ቆይቶ ከማዕከላዊ ጎንደር የተወጣጡ የባሕል አምባሳደሮች ዛሬ ትርኢታቸውን በጎዳና ላይ በማቅረብ አጠናቅቀዋል፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታላቁ የህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውይይት እያደረጉ ነው። የውይይቱ ዓለማ #የተቀዛቀዘውን ህዝባዊ ተሳትፎ ለመመለስ እንደሆነ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡ በአዲስ አበባ የጀርመን ኢምባሲ ባሰራጨው መረጃ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታንማየር ከጥር 19-22 ባሉት ለቀናት በሚያደርጉት ጉብኝት ከፕሬዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ፡፡ ላሊበላ የጉብኝታቸው አንዷ አካል ናት፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia