TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የድርጅትና የመንግስት የስራ አፈጻጸም እንዲሁም በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ላይ ሲሆን አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምም ይገመግማል። በስብሰባው በመስከረም ወር #በሀዋሳ በተካሄደው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአጋር ፓርቲዎች ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅግጅጋ‼️

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት በጅግጅጋ ከተማ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉብኝት አካሄደ፡፡

ጉብኘቱ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ነው የተካሄደው፡፡ በዚህ ወቅት በሰብዓዊ መብት አያያዝና አተገባበር ዙሪያ እያክናወነ ያለውን ተግባር የበለጠ አጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት ተነግሯል፡፡

የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል መሀመድ ወርፋ በቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት የስልጣን ዘመን የበርካታ ዜጎች ህይወት መጥፋቱን፣የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶች መጣሱን እና በርካቶች የላባቸውን ዋጋ ደመወዝ መከልከላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ የዜጎችን መብት ለማስከበር በሚንቀሳቀስበት ጊዜም ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስበት እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

በክልሉ ሀምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ ተክትሎ የኮሚሽኑን ጽህፈት ቤት በማውደምና በማቃጠል ሰነዶች እንዲጠፉ እና ኮሚሽነሩን ጭምር ለማፈን ሙክራ መደረጉን አብራርተዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው በአሁን ወቅት ቼል ኡጋዴን በሚል ይጠራ የነበረው የዜጎች ማሰቃያ እስር ቤት እንዲዘጋና የታስሩትም እንዲለቀቁ በማድረግ በክልሉ አሁን ላይ የተሻለ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲፈጠር ኮሚሽኑ የበኩሉን ጥረት ማበርከቱንም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከድሬዳዋ ደወሌ ጅቡቲ መንገድ በሱማሊ ክልል ሲቲ ዞን በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ ዛሬ #ተዘግቶ ውሏል። ተቃውሞ የተቀሰቀሰው በአፋር ክልል በሚኖሩ የሱማሊ ዒሳ ጎሳ አባላት ላይ ጥቃት ደርሷል የሚል መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አየር ሃይል‼️

‘በምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ ላይ በአየር ኃይል የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል’ ተብሎ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚናፈሰው ወሬ #ሃሰተኛ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል #ይልማ_መርደሳ ገለጹ።

ብርጋዴር ጄኔራሉ በምዕራብ ኦሮሚያ የጸጥታ ችግር መኖሩንና መንግስት ብዙ ትዕግስት ማሳየቱን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እርምጃ መውሰድ የጀመረ ቢሆንም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ‘በአየር ኃይል የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል’ ተብሎ የሚነዛው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአካባቢው ከምድር ውጊያና የሰፈር ግጭት ያለፈና አውሮፕላን መጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ አለመኖሩንም ነው የገለጹት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
.
.
.
ምንም እንኳን መንግስት የአየር ጥቃት አልተፈፀመም፤ የሚናፈሰው ወሬም ሀሰት ነው ቢልም ከቀናት በፊት ቢቢሲ ያነጋገራቸው #የኦነግ_ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ #ሚካኤል_ቦረና መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ #የአየር_ጥቃት እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም #እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን #የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብሔራዊ የፈተና መስጫ ቀን ይፋ ሆነ🔝

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የ2011 ብሔራዊ የፈተና መስጫ ቀን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፦

1. የ10ኛ ክፍል ከግንቦት 21 እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም
2. የ12ኛ ክፍል ከግንቦት 26 እስከ 30 2011 ዓ.ም
3. የ8ኛ ክፍል ከሰኔ 05 እስከ ሰኔ 07 2011 ዓ.ም እንደሚሰጥ ኤጀንሲው ገልጿል።

የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ረዲ_ሽፋ የፈተና መስጫ ቀናቱ ለሁሉም ክልሎች መላኩን ገልጸው ክልሎቹ #የተለየ ምክንያት ካላቸው ሌላ የፈተና መስጫ ቀን በመምረጥ ለኤጀንሲው ሊያሳውቁ እንደሚችሉም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ዓይነት የፈተና መሥጫ ዝርዝር ቀናትን በየክፍል ደረጃቸው ከዚህ በታች ካሉት የፅሁፍ ፎቶ ግራፎች መመልከት ትችላላችሁ።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ ሀዘናቸውን ገልፁ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አህመድ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት መንግሥት የተሰማውን ሀዘን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቃቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ #ዘግናኝ ድርጊት ሲሉ ኮንነውታል። ለተጎጂ ቤተሰቦችና በሀዘን ላይ ለሚገኙት መላው ኬንያውያን የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን ገልጸዋል። ትናንት ናይሮቢ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን የኬንያው ፕሬዚዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ ዛሬ መግለጻቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ የፀጥታ ችግር ታይቶባቸው የነበሩ አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማዊ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በምዕራብ ኦሮሚያ ባለፉት ወራት የሰዎችን ህይወት የቀጠፉ፣ የአካል እና ንብረት ጉዳት ያደረሱ ግጭቶች በተለይም በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ በተደጋጋሚ ተከስተው አሳሳቢ ችግር ተፈጥሮ ነበር። በምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ሆሩ ጉድሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ኢሉ አባቦራ እና በደሌ በከፊል መሰል ችግሮች ታይተዋል። አሁን ላይ መሻሻሎች እያታዩና የፀጥታ ችግር ታይቶባቸው የነበሩ አብዛኛዎቹ ከተሞችም ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል #አለማየሁ_እጅጉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ መረጃ👇

https://telegra.ph/በምዕራብ-ኦሮሚያ-የፀጥታ-ችግር-ታይቶባቸው-የነበሩ-አካባቢዎች-ወደ-ቀደመ-ሰላማቸው-እየተመለሱ-ነው-01-16
#update ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተከሰተው የነዳጅ እጥረት ዙርያ ምክክር ተካሂዷል። ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ጋር በመሆን በከተማዋ በተከሰተው ወቅታዊ የነዳጅ እጥረት ዙሪያ ከማደያ ባለቤቶች እና ከነዳጅ አቅራቢ ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
እያጣጣምን የምንረካባቸውና ደግመን ደጋግመን በልተን የማንሰለቻቸውን ኬኮች ፣ አይስ ክሬሞች እና ሌሎች ጣፋጮችን የሚያዘጋጁ ከ40 በላይ ዝነኛና ስመጥር ድርጅቶች የሚሳተፉበት ልዩ የጣፋጭ ፌስቲቫል።
ሸገር ኬክ ፌስቲቫል!!!

ለበለጠ መረጃ
0910554686/0921025811
@saryanevents