TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጉዞ አድዋ!

"የጉዞ አድዋ" ተጓዦች #የሽኝት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ነው። በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ፣ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተገኝተዋል። እንዲሁም “የጉዞ አድዋ” ተጓዦች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች እና የከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት የሽኝት መርሃ ገብሩ እየተካሄደ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኝ መረጃ ያመለክታል።

Via FBC
ፎቶ፦ የአ/አ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በምእራብ ወለጋ #የኦነግ ማሰልጠኛ ካምፕ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ቦታዎች ላይ ዛሬ ጥዋት #የአየር_ጥቃት መፈፀም መጀመሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። . . የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ... Ethiopia Defense Force begins #airstrike in western Oromia; says targets are OLF military training #camps. Ethiopian…
ኦነግ ላይ #ተሰነዘረ ስለተባለው የአየር ጥቃት!

#ጋዜጠኛ_ኤልያስ_መሰረት(AP)

ሰሞኑን አንዳንድ የሀገር ውስጥ ሚድያዎች በኦነግ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን ሲዘግቡ ሰንብተዋል። አንድ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ትናንት ምሽት anonymously የነገሩኝ ግን ፈፅሞ የተለየ ነበር፦

"ያው እንደምታውቀው መከላከያ የራሱ ስርአት ስላለው እና እኔም ወታደር ስላልሆንኩ ዝም ብዬ በነሱ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት አልችልም። ልነግርህ የምችለው ግን ምንም አይነት የአየር ጥቃት አየር ሀይል አልሰነዘረም። የአየር ቅኝት ሊኖር ይችላል። በሂሊኮፕተር ተደብድበው ቢሆን የኦነግ አመራሮች እስካሁን ዝም ይሉ ነበር ወይ ብለህ ራስህን ጠይቀው እስቲ። እኔ አሁን ያለሁት አሶሳ ቢሆንም ባለኝ መረጃ በጄት እና ሂሊኮፕተር #ድብደባ ደረሰ የተባለው ፍፁም #ሀሰት ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንተማ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሻማ ፋብሪካ‼️
የእሳት አደጋ‼️

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ መግቢያ ላይ የሚገኘው #ኢንተማ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሻማ ፋብሪካ ላይ በደረሰበት የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገለፀ።

በዚህ የእሳት አደጋ ከፋብሪካው አቅራቢያ የሚገኙ ሁለት የንግድ ሱቆችና አንድ መኖሪያ ህንፃ ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በአጠቃላይ 11 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ተናግረዋል።

ከንግድ ሱቆች 500 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን ከመኖሪያ ህንፃውና ከሱቆቹ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉንም ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠርም ከአመስት ቅርንጫፎቹ የተውጣቱ 80 የአደጋ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች፣217 ሺህ 500 ሊትር ውሃ፣ 5 ሺህ 975 ኬሚካል ፎም እና 13 ከባድ ተሸከርካሪዎችን መጠቀሙን አንስተዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር በነበረው ሂደትም አንድ የባለስልጣኑ ሰራተኛ ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የገለፁት ባለሙያው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮሎኔል ጉደታ ኦላና‼️

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ በኮሎኔል #ጉደታ_ኦላና ላይ የጠየቀውን የ15 ክስ የመመስረቻ ቀናት በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ።

የፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት የኢትዮ-ቴሌኮም የሴኪዩሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ ኮሎኔል ጉደታ ኦላና ላይ ክስ ለመመስረት ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ቀን ላይ በአብላጫ ድምጽ ነው ውሳኔ የሰጠው።

በሜቴክ ውስጥ የተፈፀመ የሙስና ወንጀል በሚያጣሩ ባለሙያዎች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የዐቃቤ ህግ ስራን በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ዐቃቤ ሕግም ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ያስረከበው መሆኑን ጠቁሞ በኮሎኔል ጉደታ ኦላና ደረሰ የተባለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ መዝገቡን ለማደራጀትና ክስ ለመመስረት ነው ተጨማሪ ጊዜውን የጠየቀው።

ፍርድ ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ለክስ መመስረቻ የተጠየቀውን ቀን በመፍቀድም ለጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያን በውጭ የሚወክሉ አምባሳደሮች ቆንስል ጄኔራሎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራሎችና ዳይሬክተሮች የተሳተፉበት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ አመታዊ ኮንፈረንስ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ተጀምሯል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያን ለ52 ዓመታት በተለያዩ ሀገራትና ተቋማት በመወከል በዲፕሎማትነት ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአገልግሎት ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡ አምባሳደር ቆንጅት የአገልግሎት እውቅናው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት ተሰጥቷዋል፡፡ ይህ ሽልማት አምባሳደሯ ለረጅም ዓመታት ላበረከቱት ስኬታማ አገልግሎት እንደተበረከተላቸው ተነግሯል፡፡አምባሳደር ቆንጂት በግብፅ፣ በእስራኤል፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀገራቸውን በዲፕሎማትነት በመወከል ውጤታማ ስራ ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2 ቀን ውስጥ በጎሳ ግጭት 400 ሰዎች ሞቱ‼️

በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ በታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረ #የጎሳ_ግጭት የ400 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።

በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አካባቢ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረው የጎሳ ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 400 የሚሆኑ ዜጎች ህይዎት አልፏል።

ግጭቱ የተፈጠረውም በዩምቢ ከተማና አካባቢው በሚገኙት #ባቴንድ እና #ባኑን በተሰኙ ጎሳዎች መካከል መሆኑ ነው የተገለፀው።

የግጭቱ ምክንያትም በአካባቢው ለመካሄድ ዝግጅት ላይ በነበረው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ነው ተብሏል።

የባቴንድ ጎሳዎች የገዢውን መንግስት መመረጥ #የሚደግፉ ሲሆን ፥ባኑኖች ደግሞ በአካባቢው እነሱን ወክሎ የሚወዳደረውን #የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ነበሩ።

በተፈጠረው ግጭትም ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም በርካቶች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

እንዲሁም በግጭቱ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ግጭቱን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ታህሳስ 30 ላይ በአካባቢው ሊካሄድ የነበረውን ምርጫ መሰረዙ ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️ በባህር ዳር ከተማ ተቃውሞ የሚያሰሙ ተማሪዎች ከክልሉ ልዩ ሃይል ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባታቸው ተጠቁሟል። በከተማይቱ ተቃውሞ እያሰሙ ያሉት ተማሪዎች የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ለቀው የወጡና መንግስት በክልላቸው እንዲማሩ እንዲያደርግ የሚጠይቁ ናቸው።

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱኝ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️

ፖሊስ፣ በሙስና ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሎ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው አቶ #ኤርሚያስ_አመልጋ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የተጠረጠሩት ኢምፔሪያል ሆቴልን ከሜቴክ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመመሳጠር በማይገባው የገንዘብ መጠን እንዲገዛ አድርገዋል ተብለው ነው፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ 51 ሚሊየን ብር የሚገመተውን ኢምፔሪያል ሆቴል 75 ሚሊየን ብር ለሜቴክ በመሸጥ የ21 ሚሊየን ብር ጉዳት አድርሰዋል ሲል መርማሪ ፖሊስ አመልክቷል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ኤርሚያስም፣ ኢምፔሪያል ሆቴል ከባለቤቶቹ የተገዛው 70 ሚሊየን ብር መሆኑንና የተሸጠውም 72 ሚሊዮን ብር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ክፍያ የተፈፀበትም 23 ሚሊየኑ ብቻ ስለሆነ የስም ዝውውር አለመፈፀሙን ተናግረዋል፡፡
ግዥውን የፈፀመው በቀጥታ እርሳቸው 5 በመቶ ባለድርሻ የሆኑበት አክሰስ ሪል ስቴት ነው ብለዋል፡፡

አክሰስ ሪል እስቴት፣ በህግ የፈረሰም በመሆኑ ሊጠየቅ እንደማይችልና የኢምፔሪያል ሆቴል ባለቤቶቹ የነበሩት አቶ ፀጋዬ አስፋውና ቤተሰቦቹ በቀጥታ ከሜቴክ ጋር ውል መፈፀማቸውን ተናግረውል፡፡

አቶ ኤርሚያስ፣ በእጃቸው ሊያሸሹት የሚችሉት ሰነድ የሌለ በመሆኑና ጉዳዩ ከእሳቸው ጋር ግንኙነት ስለሌለው ሊታሰሩ እንደማይገባ ለፍ/ቤቱ አመልክተዋል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ 10ኛ ወንጀል ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ትዕዛዝ ለመስጠት ለከሰዓት በኋላ ቀጥሯል፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦነግ ላይ #ተሰነዘረ ስለተባለው የአየር ጥቃት! #ጋዜጠኛ_ኤልያስ_መሰረት(AP) ሰሞኑን አንዳንድ የሀገር ውስጥ ሚድያዎች በኦነግ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን ሲዘግቡ ሰንብተዋል። አንድ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ትናንት ምሽት anonymously የነገሩኝ ግን ፈፅሞ የተለየ ነበር፦ "ያው እንደምታውቀው መከላከያ የራሱ ስርአት ስላለው እና እኔም ወታደር ስላልሆንኩ ዝም ብዬ በነሱ…
"የአየር ጥቃት ተፈፅሟል" ኦነግ‼️

ዕሁድ ጠዋት የሀገር መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የኦነግ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል የሚል መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ #ገመቺስ_ተመስገን በጉዳዩ ላይ BBC የአማርኛው አገልግሎት አስተያየታቸውን ጠይቆ፤ ''ይህ መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይንቀሳቀሳል። በተለያዩ አጋጣሚዎችም ከኦነግ ሠራዊት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ዕሁድ ዕለት የአየር ጥቃት ተሰንዝሯል ወይም #አልተሰነዘረም ማለት #አልችልም'' ብለዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአየር ጥቃት የተፈጸመው በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች አዋሳኝ ድንበር ላይ መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ይሁን እንጂ BBC ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች "የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ሲባል ሰማን እንጂ ያየነው ነገር የለም" ይላሉ።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የአየር ጥቃት ሲፈጸም #ባይመለከቱም በአከባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮች በብዛት ስለሚመላለሱ ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል።

#የኦነግ_ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ #ሚካኤል_ቦረና ግን መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ የአየር ጥቃት #እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን #የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጃል ኤልያስ‼️

የደቡባዊ ዞን የኦነግ ጦር መሪ የሆኑት ጃል #ኤሊያስ_ጋምቤላ የአባገዳዎችን ጥር በመቀበል ጦራቸውን አስቀምጠው በሰላማዊ መልክ ለመታገል ወስነው ህዝባቸውን ተቀላቅለዋል።

ምንጭ፦ ደረጀ ገረፋ ቱሉ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች🕊

የደቡብ ዞን የኦነግ ጦር የጉጂ ኦሮሞ #አባ_ገዳዎች ያቀረቡለትን #የሰላም_ጥሪ ተቀበለ። የጉጂ ዞን የኦነግ ጦር አባ ገዳዎች ባወጁት የሰላም ሳምንት ወቅት የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በትናንትናው እለት ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሱ ታውቋል። የጉጂ አባ ገዳዎች ባሳለፍነው ሳምንት አውጀውት የነበረው የሰላም ሳምንት በዚህኛውም ሳምንት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

Via Ahadu Radio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል #ህጋዊ የድንበር ላይ ንግድ ልውውጥ ለማስጀመርና ለመቆጣጠር አራት የንግድ ማስተላለፊያ ኬላዎችን ለመክፈት የልየታ ስራ ማጠናቀቁን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ከሚከፈቱት ኬላዎች መካከል ሁለቱ በዛላምበሳና ራማ የሚገኙ ናቸው። በአገሮቹ መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ ምጣኔ ኃብትን ጨምሮ አጠቃላይ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ለሁለት አስርት ዓመታት ቆይቷል።

via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አፈጻጸም፤ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ሂደት፤ እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።

ምንጭ፡- የኢህአዴግ ም/ቤት ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር‼️

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በባህርዳር ከተማ ተጠልለው የሚገኙ የቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ዛሬ ሰልፍ በወጡበት ወቅት ከፖሊስ ጋር #ተጋጭተዋል

ግጭቱ የተፈጠረው ተማሪዎቹ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉት ውይይት #ካለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ መከፋታቸውን ሀይል በተሞላበት ሁኔታ መግለጽ በመጀመራቸው ነው።

መንግስት ተማሪዎቹ ወደ ቡሌሆራ ተመልሰው መሄድ እንዳለባቸው የገለጸ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በአማራ ክልል በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች እንመደብ በማለት ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን በሰልፍ ማቅረባቸው ይታወሳል።

via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia