TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዋሽ 7🔝መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት በአዋሽ 7 ለቆሙ የባቡር ተጓዥ ዜጎች የአካባቢው ነዋሪ ምግብ እና ውሃ እያቀረበ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገሪቱ #አንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ #ግጭቶችን ለማስቆም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ይህንን ሚናቸውን እንዲወጡ ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩና #ተቀባይነታቸውም በመቀነሱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አለመሆኑን ባሙያዎች ተናግረዋል።

ሙሉውን አንብቡት...
https://telegra.ph/የሐይማኖት-አባቶችና-የአገር-ሽማግሌዎች-ሰላም-የመፍጠር-ሚና-ኮስሷል-01-14
ምክትል ጠሚ አቶ ደመቀ‼️

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

ሀበሻ ለፍቅር በሚል ማህበር የታቀፉት የኮሚኒቲ አባለቱ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲያስፖራውን ተሳትፎ፣ በኢትየጵያ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ እና በሌሎች ጉዳዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የኮሚነቲ አባለቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብለሹ አሰራር ለመከለከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ሊተገበር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

"በያዝናቸው የለውጥ መንገዶች የለውጡ አንዱ ትልቅ ደጋፊና አጋር ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለው በውጪ የሚኖረው ማህበረሰብ ነው" ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስር ደመቀ መኮነን የለውጡ ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ በ43 ሚሊየን ብር ወጪ የደህንነት ካሜራዎች እየተገጠሙ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱልባሲጥ አህመድ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ከቀይሽብር ሰማዕታት እስከ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አደባባይ ቁጥራቸው 140 የሆኑ የደንህነት ካሜራዎች መገጠማቸውን ተናግረዋል። ይህም የመጀመሪያው ዙር የከተማዋ የደህንነት ካሜራ ገጠማ ስራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታው 90 በመቶ መጠናቀቁን ያሳያል ብለዋል። የመግጠም ስራው ተጠናቆ የሙከራ ስራ ላይ ይገኛሉ የተባሉት ካሜራዎችም በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አገልገሎት የሚጀምሩ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ይህ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም ለፌደራል ፖሊስ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በመስጠት በከተማዋ የሚስተዋለውን የደህንነት ችግር ለማስወገድ ይረዳል ተብሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በስፔን ቫሌንሽያ በተደረገው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ፀሓይ ገመቹ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የርቀቱን የኢትዮጵያ ርከርድ አሻሽላለች፡፡ ፀሓይ ገመቹ 30 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባትና በጥሩነሽ ተይዞ የነበረውን ሰዓት በ15 ሰከንድ በማሻሻል ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
"በምዕራብ ወለጋ 10 ባንኮች ተዘርፈዋል"- የዞኑ አስተዳዳሪ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን 10 ባንኮች በታጣቂዎች መዘረፋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ለDW ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በዞኑ የአራት ወረዳዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን እና በሌሎቹ ወረዳዎች #ዝርፊያ መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ተመስገን ለDW እንደተናገሩት በመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት 10 ሰዓት ገደማ ነው። አስተዳዳሪው የታጠቁ ባሏቸው ኃይሎች ተፈጸመ ያሉት ዝርፊያ የተከናወነው በተመሳሳይ ሰዓት መሆኑንም ገልጸዋል።

“የታጠቀው ኃይል እዚህ አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እና በደረሰን መረጃ መሰረት 10 የሚሆኑ የመንግስት እና የግል ባንኮች ተዘርፈዋል” ብለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ። ከተዘረፉት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ሕብረት ባንክ እንዲሁም የኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ባንክ እንደሚገኙበት አስረድተዋል። በባንኮቹ ዝርፊያ የተወሰደው ገንዘብ መጠኑ ግን እስካሁን አለመታወቁን ጨምረው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

በጎንደር ከተማ ዛሬ የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል በልዩ ልዩ ክንውኖች እየተከበረ ነው፡፡ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ በ1811 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡

ምንጭ:- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አቅራቢያ የጭነት አገልግሎት የሚሰጥ አይሮፕላን በመጥፎ የአየር ሁኔታ ሊንደረደር ሲሞክር ተጋጭቶ 15 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ቦይንግ 707 የሆነው አውሮፕላኑ ከቴህራን በስተምዕራብ 40 ኪሎ ሜትር ላይ በሚገኘው ካራጅ በተባለ አውሮፕላን ማረፊያ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

አውሮፕላኑ ከመንደርደሪያው በመውጣት ነው ከሰዎች መኖሪያ ቤት ጋር የተጋጨው።

የኢራን ሰራዊት በአደጋው በህይወት የተረፈውን አንድ የአውሮፕላኑን ሰራተኛ ወደ ሆስፒታል በመውሰድ የነብስ አድን ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
የጭነት አውሮፕላኑ ከኪርጂዝ ዋና ከተማ ቢቢሽኪ ስጋ ሲያጓጉዝ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡
የአውሮፕላኑ ባለቤት ማን እንደሆነ እስካሁን በግልፅ አልታወቀም፡፡

ምንጭ፦ bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር‼️

ከአንድ ወር ገደማ በፊት ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ጥለው የወጡ ተማሪዎች #በአማራ_ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልንመደብ ይገባል የሚል ጥያቄ ይዘው በባሕር ዳር ከተማ ሰልፍ አደረጉ። በዛሬው ሰልፍ ወደ 2500 ተማሪዎች መገኘታቸውን በቦታው የተገኘው የDW ዘጋቢ ተናግሯል። ተማሪዎቹ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተነስተው እስከ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተጉዘዋል። ሰልፈኞቹ በክልሉ መንግሥት ቢሮ ፊት ለፊት "መንግሥት የለም! መንግሥት ቢኖር ጥያቄያችንን ይመልስልን ነበር" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን የDW ዘጋቢ ታዝቧል። የጸጥታ አስከባሪዎች ኹኔታውን በርቀት ሲከታተሉ ነበር። በአብዛኛው ጥቁር የለበሱት ተማሪዎች መንግሥት ጥያቄያችንን ይመልስልን፤ በአማራ ክልል እንመደብ" የሚል ጥያቄ በሰልፉ ላይ አሰምተዋል። የኢኖቬሽን እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ይመለሱ የሚል ምላሽ ባለፈው ሳምንት ሰጥቶ ነበር። ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑት "ሴቶች ይደፈራሉ፤ ወንዶች ይደበደባሉ" በሚል ምክንያት ነው። DW እንደዘገበው ተማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በሚገኝ ስታዲየም ተጠልለው ይገኛሉ።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ወቅታዊ ችግሮችን ከማርገብ ባለፈ ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን ከወትሮው በላቀ እንዲወጡ ተጠየቀ። ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

በዱቄት መልክ #አደገኛ_ዕጾችን ሲያዘዋዉር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ። ለሰው ልጅ ጤና ጉዳት የሚያደርሱ የተከለከሉ አደገኛ ዕጾችን ማዘዋወር ወንጀል የተከሰሰው የውጭ ዜጋ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ ሚስተር ዳኒ ቺካ ኑዋዱኬ የወንጀል ህግ አንቀጽ 525 /1/ለ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወር፣ በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን የኮኬይን እጽ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከብራዚል ሳኦወፖሎ ወደ በመነሳት ወደ ቦሌ አየር መንገደ ለትራዚተ ባረፈበት ወቅት በተደረገው ፍተሻ በያዘው የጉዞ ሻንጣ ውስጥ በዱቄት መልክ የተዘጋጀውን 5.2 ኪሎ ግራም እና በሆዱ ውስጥ ደግሞ 87 ጥቅል ፍሬ የሆነውን ኮኬይን የተባለውን እጽ ድብቆ በመያዝ ወደ ኢንጉ ከተማ ሊሄድ ሲል የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው መርዛማ እና አደገኛ ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተከሳሹ ማንነቱ ተረጋግጦ ክሱ ደርሶትና በችሎት ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ መቃወሚያ የለኝም ባለቤቴ መንታ ልጁ ስለወለደች በቸግር ምክንያት ድርጊቱን ፈፀሜለሁ ጥፋተኛ ነኝ በማለት ተናግራል፡፡ዐቃቤ ሕግን ተከሳሽ ድርጊቱን ባመነው መሰረት ሌላ ማስረጃ ማሰማት ሳያስፈል ጥፋተኛ ይባል ብሏል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ በተከሰሰበት አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ በመላት የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና በገንዘብ ችግር ምክንያት መሆኑን በማቅለያነት በመቀበል በ8 አመት ጽኑ እስራትና በ8000 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተዘጋው መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተከፈተም‼️

በተቃውሞ ሳቢያ የተዘጋው የአዲስ አበባ፤ አዋሽ ጅቡቲ መንገድ ዛሬም ሙሉ በሙሉ #አልተከፈተም። ወደ #ጅቡቲ የሚያመራው እና የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ የደም ሥር እንደሆነ የሚነገርለት የመኪና መንገድ አዋሽ ሰባት ከተማ ላይ ዛሬም ለተሽከርካሪዎች ዝግ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪ ለDW አረጋግጠዋል።

ተቃዋሚዎች ከትናንት ጀምሮ ዋናው መንገድ ከሚያልፍባት የአዋሽ ከተማ መውጪ እና መግቢያዎች እንደዘጉ መሆናቸውን የዐይን እማኙ ተናግረዋል።

በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የአዋሽ ነዋሪ "መንገዱ አልተከፈተም፤ ምንም የሚንቀሳቀስ ነገር የለም" ብለዋል።

በሎጊያ አካባቢ የሚገኘው የመንገዱ ክፍል ግን በዛሬው ዕለት ተከፍቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን አንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተናግረዋል። ትናንት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት መንገድ ላይ ማደራቸውን ለDW የገለጹት አሽከርካሪ ዛሬ ወደ ሎጊያ ከተማ ለመግባት መቻላቸውን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ላይ ስለመሆኑ መረጃ እንደደረሳቸው የገለጹት የከባድ መኪና አሽከርካሪ "ሕዝቡ ለሰባት ቀን ጊዜ ሰጥቶ አሁን መኪና መንቀሳቀስ ጀምሯል። በሰባት ቀናት ውስጥ ጥያቄያችን ካልተመለሰ #አሁንም_እንዘጋለን ብለዋል" ሲሉ ኹኔታውን አስረድተዋል።

በአዋሽ ሰባት የሚኖሩት ነጋዴ ግን የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ክፍኛ ያስተጓጎለው የመንገድ መዘጋት "እስከ ነገው ዕለት ይቀጥላል" የሚል መረጃ ደርሷቸዋል። "ሶስት ቀን እያሉ ነው። ነገንም ይጨምራል መሰለኝ" ያሉት የአዋሽ ሰባት ነዋሪ ከመንግሥት መፍትሔ ካልተገኘ ሊከፈት እንደማችል በተቃውሞው የተካፈሉ ሲዝቱ መስማታቸውን ለDW አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ባንኮች ተዘረፉ‼️

በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ተጨማሪ ስድስት ባንኮች በታጣቂዎች በትላንትናው ዕለት መዘረፋቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለDW ገለጹ። ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በሁለት የወለጋ ዞኖች የተዘረፉት ባንኮች 17 መድረሱን የየአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ኃይሉ ዛሬ ለDW እንደተናገሩት በአካባቢያቸው ባሉ ስድስት የመንግስት እና የግል ባንኮች ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት እሁድ ከቀኑ አምስት ሰዓት ጀምሮ ነው። “በትላንትናው ዕለት የባንክ ዘረፋ የተካሄደው በሃዋ ገላን ወረዳ፣ እሮብ ገበያ ላይ፣ በአንድ የንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ [ላይ] ነው። እዚያው ወረዳ ላይ መቻራ የምትባል ከተማ ላይ አንድ የንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተዘርፈዋል። ከዚያ ደግሞ ሰዲ ጨንቃ ወረዳ ላይ በጨንቃ ከተማ አንድ የንግድ ባንክ፣ አንድ የኦሮሚያ የህብረት ስራ ባንክ ዝርፊያ ተካሂዶበታል” ብለዋል።

ተዘረፉ በተባሉት ባንኮች እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በታጣቂዎች መወሰዱን የገለጹት የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የየባንኮቹ ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል የሚል ስጋት እንዳለም አስረድተዋል። “ ካሸሪዎች [ገንዘብ ያዥዎች] እና ስራ አስኪያጆችን ይዘው ሄደዋል ነው የሚባለው። እንግዲህ ሰዎቹን ስላላገኘን እስካሁን ምን ያህል ገንዘብ ተወሰደ የሚለውን ማወቅ አልቻልንም። ግን ደግሞ ሰዎቹን ይዘው ሄደዋል የሚል መረጃ ነው ያለን” ሲሉ አብራርተዋል።

ታጣቂዎቹ ከባንክ ዘረፋ በተጨማሪ በሁለት ወረዳዎች ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤት ማውደማቸውን አቶ ታመነ ይናገራሉ። “በላሎ ክሌ የመንግስት መስሪያ ቤት አቃጥለዋል። በዋሃ ገላን፣ በየ ማለጊ ወረዳ ላይም የመንግስት መስሪያ ቤት የተቃጠለበት ሁኔታ ነው ያለው። እንግዲህ እነኚህ ወረዳዎች ሰራዊት የሌለበት ወረዳ ነው። ሰራዊት ከሌላ አጎራባች ቦታ እስኪደርስ ይሄን ጉዳት አድርሰው የታጠቁት ኃይሎች ከአካባቢው ተንቀሳቅሰዋል” ብለዋል።

ዘረፋ እና የንብረት ቃጠሎ በደረሳባቸው ቦታው ግጭት እንደሌለ የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ተናግረዋል። አሁን በቦታዎቹ ላይ የጸጥታ ኃይሎች ገብተው ህዝቡን እየያረጋጉ እንደሚገኙም ገልጸዋል። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት በሄሊኮፕተር ታግዞ ጥቃት ፈጽሟል የሚባለውንም #አስተባብለዋል

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተከፍቷል‼️

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚወስዳው መንገድ #ተከፍቷል። ተጨማሪ እየተከፈቱ የሚገኙ መንገዶችን መረጃዎች እንደደረሱኝ አሳውቃለሁ።

🔹የአፋር ክልል ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ። የተዘጉ መንገዶችም እንደሚከፋቱ በአፋር የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተናግረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia