TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ጀግኒት" ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ🔝

በሴቶች ላይ የሚደርስባቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች መምሪያ አስታውቋል፡፡ መምሪያው ‹‹ጀግኒት›› የሴቶች ሰላም ኮንፈረንስ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አካሂዷል፡፡

ምንጭ፦ Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ‼️

በአዳማ ከተማ የሕብረተሰቡን #የልማት ጥያቄዎች #ሊመልሱ የሚችሉና 500 ሚሊየን ብር የወጣባቸው ከ20 በላይ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ዛሬ #እንደሚመረቁ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ #መስፍን_አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በመርሃ ግብሩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን፤ ፕሮጀክቶቹ ከዚህ ቀደም ይነሱ የነበሩ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደሚፈቱም ይታመናል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀቡቲ ዋናው መንገድ በአፋር ክልል በወጣቶች ተቃዉሞ ተዘጋ። በርካታ ጭነት የያዙ መኪኖች በያሉበት ቆመዋል። በአፋር ደቡቡባዊ ዞን በኢሳና አፋር በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች የአከባቢው ህዝብ ሠላም ርቆት እንደቆየ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን ዋና መንገድ የዘጉትም የአፋር ክልል ልዩ ኃይል አካባቢዉን ለቆ እንዲወጣ ተወስኗል በሚል ተቃውሟቸውን ለመግለጽ መሆኑን ተሠምቷል።

Via Zehabesha
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለለውጥ እንነሳ‼️

መጠላላቱን፣ በብሄር በዘር መከፋፈሉን፣ መሠዳደቡን፣ መተነኳኮሉን፣ እርስ በእርስ ለመጠፋፋት መሮጡን፣ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መሽቀዳደሙን ትተን ይህ እጅግ #አሳፋሪ እና #አስነዋሪ በዓለም ደረጃ አንገት የሚያስደፋንን ታሪክ ለመቀየር 24 ሰዓት እንስራ‼️

Half of the world's poor live in these 5 countries:

🔹India
🔹Nigeria
🔹Democratic Republic of Congo
🔹Ethiopia(#ኢትዮጵያ)
🔹Bangladesh

https://wrld.bg/Oeak30nhefz
ጥቆማ‼️

የአዋሽ መንግድ በመዘጋቱ መንገደኞች እየተጉላሉ ይገኛል። መንገዱ ከተዘጋ ከአንድ ሰዓት በላይ ሆኖታል። የሚመለከተው አካል ፈጣን መፍትሄ እንዲፈልግላቸው መንገደኞች ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሠብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ‼️

በሐዋሳ ከተማ #የድንገተኛ_አደጋዎችና የቀዶ ጥገና ስፔሻላይዝድ ህክምና ማዕከል ትናንት ተመረቀ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የክልሉ መንግሥት የኅብረተሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሟላት ለባለሀብቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የግል ባለሀብቶች በዘርፍ ለተገኙ ውጤቶች ድርሻቸው ከፍተኛ ሲሆን÷ ወደፊትም ለዚሁ ተግባር ኢንቨስትመንት የሚውል መሬት እንደሚመቻችላቸውም ነው የተናገሩት።

ባለፉት ዓመታት 4ሺህ 670 የጤና ተቋማትን መገንባታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ÷ የሰው ኃይልና ቁሳቁስን በማሟላት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ዕድገት ተምዝግቧል ብለዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በበኩላቸው ማዕከሉ በድንገተኛ አደጋዎች የሚከሰተውን ሞትና የአካል ጉዳት ለመቀነስ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የያኔት የድንገተኛ አደጋዎችና የቀዶ ጥገና ስፔሻላይዝድ ህክምና ማዕከል ባለቤት ዶክተር ግርማ አቢ እንዳሉት÷ ማዕከሉ በኢትዮጵያ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሶስተኛ ደረጃ በገዳይነቱ የሚታወቀውን በትራፊክ እና ሌሎች አደጋ ጉዳተኞችን እንደሚስተናግድ
ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ ባለ 11 ወለል ህንጻ የህክምና አገልግሎት ለሚሰጥበት ሆስፒታል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል።

ምንጭ ፡- ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvaheyhiopia
#update አዲስ በአበባን ከአዋሽ-ድሬዳዋ/ሐረር-ጅግጅጋ እና አዲስ አበባን ከአዋሽ-ሰመራ-ጅቡቲ የሚያገናኘው መንገድ በአፋር ክልል በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ምክንያት ከጠዋት ጀምሮ ተዘግቷል። በተቃውሞው የባቡር ትራንስፖርትም ተቋርጧል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia