#update "የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ ጥር 4 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ እሸቱ ጮሌ አዳራሽ ተካሂዷል። ኮንፈረንሱን የሰላም ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በኮንፈረንሱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የየአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል።
ምንጭ፦ ሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ‼️
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር #እንደተዘረፈ ተሰምቷል።
ታህሳስ 19፣ 2011 ዓ. ም. በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 80 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል።
ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ አሰቦት አካባቢ መሳሪያ በያዙ ሰዎች ተከበበ።
ከዚያስ? የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኮማንደር ጋዲሳ ንጉሳ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል " የተወሰኑ ኃይሎች ሽጉጥ የያዙ እንዲሁም ባዶ እጃቸውን የነበሩ ግለሰቦች መኪናውን መንገድ ላይ አስቆሙት። ሾፌሩን አስፈራርተው በማስወረድ አሰቦት ወደምትባል አካባቢ መኪናዋን ወሰዷት"
ከተዘረፈው 80 ሚሊዮን ብር ውስጥ በሽምግልና፣ በድርድርና በፍተሻ ማስመለስ የቻሉት ገንዘብ እንዳለም ይናገራሉ።
ይህን ያህል ገንዘብ አስመልሰናል ለማለት ሰነድ ባያጠናቅሩም "እጅ ከፍንጅ የተያዘ ገንዘብ የለም። አብዛኛው ብር የተመለሰው በጥቆማ ነው። በርካታ መኪና ይዘው ሲሄዱ በፍተሻ የተያዙ አሉ" ብለዋል።
ለመሆኑ አንድ ባንክ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ገንዘብ ሲያዘዋውር የሚደረግለት የጥበቃ ኃይል ወደየት ሄዶ ነው ዝርፊያው ሊፈፀም የቻለው? በሚል ቢቢሲ ኮማንደሩን ጠይቋል።
"በወቅቱ አብረው የነበሩት ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ መያዝ አልቻሉም። ወደ ሌላ እርምጃ ከተገባ በነሱም ደህንነት ላይ አደጋ ስለሚመጣ በልመናና በድርድር ገንዘቡን መውሰድ እንዲያቆሙ ለማድረግ ተሞክሯል። ማስፈራራትና ወደ ሰማይም ተተኩሷል።"
ዘራፊዎቹ በቁጥር ብዙ እንደነበሩ የሚናገሩት ኮማንደሩ፤ ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ከዘረፉበት ቦታ ወደ ከተማ ይዘው ከሄዱ በኋላ ለመከፋፈል ሲሞክሩ የከተማው ከንቲባ "የሕዝብ ንብረት ነው" ብለው በድርድር ለማስቆም ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ይገልጻሉ።
ፎርቹን ጋዜጣ፤ ብሩ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ ላይ እንደነበር ጠቅሶ 100 ግለሰቦች በዝርፊያው ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲል ዘግቧል።
ከዘረፋው ጀርባ ያሉ ሰዎችን ማንነት ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኮማንደሩ ቢናገሩም፤ "ዘራፊዎቹ ከሩቅ የመጡ አይደሉም" የሚል ጥቆማ ሰጥተዋል።
ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከድሬዳዋ ቅርንጫፍ 80 ሚሊዮን ብር ጭኖ በመኢሶ ወረዳ ሲተላለፍ ነበር። ያኔ ገንዘቡን ይዞ ይጓዝ የነበረው መኪና አሽከርካሪ አህያ ገጭቶ በአካባቢው ፖሊስ ተይዟል። በወቅቱ የተገኘው ገንዘብና አጓጓዡ የያዘው ሰነድ ላይ የሰፈረው የገንዘብ መጠን መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
ገንዘቡን መጫን የነበረበት መኪና ሰሌዳ ቁጥርና በፖሊስ የተያዘው መኪና ታርጋ ቁጥርም የተለያየ ነው ተብሎ ነበር። ለመሆኑ የዚህ ገንዘብ ጉዳይ ከምን ደረሰ? ኮማንደር ጋዲሳ ምላሽ አላቸው።
"አምሳ ሚሊዮኑን የሚያሳይ ሰነድ በገንዘብ ያዡ እጅ አልነበረም። ይህም ከኔትወርክ ችግር ጋር የተያያዘ ነው። መንገድ ላይ በኢሜይል እንልክላችኋለን የሚል ነገር ነበር"
ገንዘቡ ከወጣበት ቅርንጫፍ ጀምሮ ስለነበረው ሂደት ምርመራ ተእየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
መጀመሪያ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የነበረው መኪና ሰሌዳው ቁጥር ሌላ ሲሆን፤ ይህም በአጋጣሚ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የታሰበው ሾፌር በህመም ላይ ስለነበር ነው ብለዋል።
"ስለ ሹፌር ለውጥ የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይቀየርብ ሌላ መኪና በመተካቱ ነው" ሲሉ የድሬዳዋ ስራ አስኪያጅ እንደነገሯቸው ኮማንደሩ ገልፀዋል።
"ገንዘቡ ህጋዊ መሆኑን ነው የምናውቀው። አሁን ምርመራ ላይ ነው። በቅርብ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ" ብለዋል።
መኪና ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ውስጥ እንዲቆይ መወሰኑንም ኮማንደር ጋዲሳ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ BBC

TIKVAH-ETHIOPIA pinned «ከጥር 1 - ጥር 21 : የሰለም፣ የፍቅር እና የአንድነት ሳምንታት-#TIKVAH_ETHIOPIA @tsegabwolde @tikvahethiopia»
#Update በሰሜንና በምዕራብ ጎንደር ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ ከ500 በላይ ታጣቂዎች ከመንግስት ጋር #ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ዛሬ ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️
የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን እንደደረሰበትና ከፈፃሚዎቹ ጥቂቶቹን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው እንደገለጹት፥ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተደርሶበታል።
በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ከተሳተፉት ውስጥም ጥቂቶቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸወን አስታውቀዋል።
የወንጀሉ ፈፃሚዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በተለያየ መንገድ በእጃቸው እንደሚያስገቡ የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው፥ የወንጀሉ ተሳታፊዎችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ዩንፎርም ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው የጎረቤት አገራትም የደንብ ልብሱ ለወንጀል መፈፀሚያነት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየሰሩ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችም በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
በተመሳሳይ ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።
ፖሊስ በተያዘው ወር ለሚካሔዱት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።
ለዚህም ስኬት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ በማለት ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#Update የኢትዮጵያን ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዲፕሎማቶች ለማስተዋወቅ ያለመ የኢትዮጵያ የባህል ዲፕሎማሲ ቀን ተከብሮ ውሏል። የባህል ዲፕሎማሲ ቀኑ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነን ጨምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ አፍሪካ ሀገሮች አምባሳደሮች ተገኝተዋል። የባህል ዲፕሎማሲ ቀንን በማስመልከትም የእንጦጦ ቤተ መንግስትና ሙዚየም፣ የአዲስ አበባ ቱሪስት መዳረሻ ፓርክ እና ያያ ቪሌጅ ጉብኝት ተደርገዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጥበባትና ባህላዊ እሴቶች፣ ባህላዊ ሙዚቃዎችና ባህላዊ ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ ቅርሶች ለበዓሉ ታዳሚዎች ቀርበዋል።
via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopiq
via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopiq
ከባህር ዳር...
"ሰላም ጸግሽ እንዴት ነህ? የዛሬው የባህርዳር እና የደደቢት ጨዋታ ፍጹም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት የተንጸባረቀበት ነበር!! የባህርዳር ደጋፊም ለ ደደቢት ክብር ሰጥቶ ሲያጨበጭብ ነበር!! አንድ የደደቢት ተጫዋችም፡ሜዳውን እየዞረ ህዝቡን ፍቅር ሲያሳይ ነበር!! እናም በጣም ደሥ ብሎናል!!"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰላም ጸግሽ እንዴት ነህ? የዛሬው የባህርዳር እና የደደቢት ጨዋታ ፍጹም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት የተንጸባረቀበት ነበር!! የባህርዳር ደጋፊም ለ ደደቢት ክብር ሰጥቶ ሲያጨበጭብ ነበር!! አንድ የደደቢት ተጫዋችም፡ሜዳውን እየዞረ ህዝቡን ፍቅር ሲያሳይ ነበር!! እናም በጣም ደሥ ብሎናል!!"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊ሰላም🕊
ሚዲያዎች ለሀገሪቱ #ሰላም የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒሰቴር ዴኤታዋ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ምሁራን ትውልድን በእውቀት በማነፅ ሰላምን ይገነባሉ" በሚል መሪ ቃል በምሁራን በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ተናግረዋል፡፡
ሰላም ከማህበረሰብ ጋር በመሆን የሚጠበቅ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስቴር ዴኤታዋ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የህብረተሰቡ አንድ አካል መሆናቸውን ጠቅሰው የሰላም ሚኒስተር ደግሞ ይሄን በማሰብ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ በዋናነት ሰላም በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ በተለያዩ ምልከታዎች አብራርተውታል፡፡ በፅሁፉ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ ምሁራንና ተማሪዎች ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱም ሰላምን ማስፈን የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ

#Update በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በአንድ ዳቦ መጋገሪያ ቤት ላይ በተፈጠረ #ፍንዳታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ገደማ በተፈጠረው ፍንዳታ ከ50 በላይ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን 12ቱ የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሑበርት የተባለው የዳቦ መጋገሪያ ፍንዳታው በተከሰተበት ቅፅበት ክፍት እንዳልነበር የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። ፍንዳው በተከሰተበት ወቅት ጋዝ ከዳቦ መጋገሪያው እየወጣ ነው የሚል ጥቆማ የደረሳቸው የእሳት አደጋ ሰራተኞች መፍትሔ ለመፈለግ ወደ ቦታው በመጓዝ ላይ ነበሩ። አደጋው ሲከሰት ቢጫ ለባሾቹ ተቃዋሚዎች መንግሥትን ለመተቸት አደባባይ ወጥተው ነበር።
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ለ2 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጁልየስ ማዳባዮ ጋር በፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራው ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ የጉብኝት ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።
ምንጭ፡- ም/ጠ /ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ም/ጠ /ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞው የጤና ሚኒስትር ዶክተር #ከሰተብርሃን ‘የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ’ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ። ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ የአፍሪካ ባለራዕይ መሪዎች አጋር በማድረግ በአህጉሩ ልማት፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት፣ የሰለጠነ ሰው ልማት፣ ትምህርት ለምርታማነት እንዲውል እና በወጣቶች የስራ ዕድል ዙሪያ የሚሰራ ተቋም ነው።
via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ዛሬ ጥር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አካባቢዎች በትናንትናው እለት ተከስተው የነበሩት ግጭቶች መረጋጋት አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን በምዕራብ ጎንድር ዞን መተማ ወረዳ ከገንዳውኃ ከተማ በስተ ደቡብ ምስራቅ በኩል በምትገኘዋ ሽንፋ ቀበሌ አሁንም ግጭቱ #አልበረደም፡፡ ከሁለቱም የታጠቁ ሀይሎች (ከቅማንትና አማራ) ወደ ቦታው እየተንቀሳቀሱ ተጨማሪ ግጭት የፈጠሩ ነው፡፡ በዚህ ግጭት ሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ወደስፍራው በመንቀሳቀስ ግጭቱን ለማብረድ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
Via Asemahagn Aseres
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Asemahagn Aseres
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ #አይታገስም፡፡" ኢ/ር ታከለ ኡማ
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎች የስራ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለብክነት የተጋለጠ እንደነበርም አንስተዋል፡፡
በግንባታ ላይ ያሉ ነባር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ውስጥ የማይጠናቀቁ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ ያሳወቁት ኢ/ር ታከለ ኡማ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ የተሰጧቸውን ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ያልቻሉ እና የህዝብን ሃብት ለከፍተኛ ብክነት እየዳረጉ ያሉ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች በቀጣይነት የከተማ አስተዳደሩ በሚያሰራየው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ አንስተዋል፡፡
እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ እንደማይታገስም አስታውቀዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡት ግንባታዎች በአስቸኳይ ኦዲት ተደርገው ለከተማ አስተዳደሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ፕሮጀክቶችን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ አጠናቅቀው እንዲያስረክቡ አሳስበዋል፡፡
via Mayor Office of Addis Ababa