ከጥር 1 እስከ ጥር 21...
ከላይ ከተዘጋጁት ምስሎች መካከል #መርጣችሁ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ፕሮፋይል ምስላችሁ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እለምናለሁ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Update በትግራይ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢ ለልማት ባለስልጣን አስታወቀ። በመንፈቅ ዓመቱ የተሰበሰው ገቢ የእቅዱን ሙሉ በሙሉ ያሳካ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ በ18 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአቶ ገላሳ ዲልቦ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የኦነግ የአመራር ቡድን መንግስት ያደረገለትን ጥሪ ተከትሎ ነው ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሀገር የተመለሰው።
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦብነግ‼️
‹‹የሶማሌዎች መብት በሕገመንግሥቱ መሰረት ከተከበረ መነጠል አያስፈልግም›› አቶ አብዱልራህማን መሀዲ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ፀሐፊ
.
.
.
የሶማሌዎች መብት በሕገ መንግሥቱ መሰረት ከተከበረ መነጠል አስፈላጊ መሆኑን እንደማያምን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ ግንባር አስታወቀ፡፡
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ዋና ጸሐፊና መስራች የሆኑት አቶ አብዱልራህማን መሀዲ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳስታወቁት፤ የሶማሌዎች መብት የሚገኘው በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያሉ መብቶች ከተከበሩ መነጠል አስፈላጊ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ኦብነግ በፕሮግራሙ የሶማሌ ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ለማስቻል የተቋቋመና እስከ መገንጠል የሚለውን ሃሳብ የሚያቀነቅን ድርጅት ነበር በአቋም ደረጃ የተለወጠ ነገር አለ ተብለው የተጠየቁት አቶ አብዱልራህማን ‹‹ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በጣም ሰፊ ነው፡፡
መብትህን እንደ ብሄር መጠቀም፣ የራስህን ባህል መጠበቅ፣ የራስህን ተቋማት መገንባት፣ የራስህን ጉዳይ በራስህ ማስተዳደር፤ በሰላም መኖር፤ በሌሎች ብሄሮች አለመጨቆንን ያቅፋል›› በማለት፤ እነዚህ መብቶች ከተጣሱ መገንጠል ከተከበሩ ደግሞ አብሮ መኖር እንደሚቻል ጠቅሰዋል፡፡ ይህ መብት በህገ መንግሥቱም መረጋገጡን አስታውቀዋል፡፡
እንደ አቶ አብዱልራህማን ማብራሪያ፤ አንዳንድ አካላት የኦብነግ ዓላማ መገንጠል ነው እያሉ ይፈርጃሉ፡፡ ይሄን ፍረጃ የሚያቀርቡት ሰዎች የተሳሳተ ግንዛቤ ነው የሚፈጥሩት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ መብታቸው ከተከበረ አብረው ይኖራሉ፡፡ ዋናው ጉዳይ የብሄሮችና ብሄረሰቦች መብት መከበርና መብቶቹን ማስጠበቅ ከሌሎችም ጋር ተቻችሎና አብሮ መኖር ነው፡፡
‹‹ብሄሮችና ብሄረሰቦች በመንግሥት ማእቀፍ ተሳስረው ይኖራሉ፡፡ መንግሥት አይደለም፤ ሕዝብ ነው መንግሥትን የሚመርጠው›› ያሉት የኦብነግ ዋና ፀሐፊ፤ ለሕዝብ ተጠያቂ የሆነ ዴሞክራሲዊ መንግሥት ካለ መገንጠል አማራጭ አይደለም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ረገድ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣታቸውን የገለጹት አቶ አብዱልራህማን፤ኦብነግ ለተወሰዱት ተግባራዊ ዕርምጃዎች አድናቆት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ቀጣይነት እንዲኖረው የበኩላቸውን እንደሚወጡ አመልክተዋል፡፡
ኦብነግ እኤአ በ1984 የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን፤ መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል በተያዘው ዓመት ህዳር ወር ወደ አገር ውስጥ ገብቷል፡፡
ምንጭ፥ ኢ.ፕ.ድ

#Update የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጡ።
https://telegra.ph/የአማራ-ክልል-ርእሰ-መስተዳድር-አቶ-ገዱ-አንዳርጋቸው-የክልሉን-ወቅታዊ-ሁኔታ-በተመለከተ-መግለጫ-ሰጡ-01-10

Telegraph
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጡ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሰሞኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት አንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት መኪኖቹን ከአንደኛው ፕሮጀክት ወደ ሌላኛው ፕሮጀክት ለማንቀሳቀስ በሞከረበት ወቅት በተፈጠረ አለመግባባት አሳዛኝ ክስተት ተፈጥሯል፡፡ ‹‹ባለፈው እሑድ (ታኅሳስ 28 ቀን 2011ዓ.ም) ጭልጋ አካባቢ በመንገድ ሥራ…
ከ100 በላይ አመራሮች ከሃላፊነት ተነስተዋል‼️
በታራሚዎች ላይ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል እና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያለውን ችግር ለማስቀረት ቀደም ሲል በየማረሚያ ቤቶች የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ አመራሮችን ከሃላፊነት ማንሳቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተናገረ፡፡
አስተዳደሩ እንደተናገረው በፍትህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ #የመብት_ጥሰቶች ሲፈፀሙ ቆይተዋል፡፡ ከነዚህም ተቋማት ውስጥ ማረሚያ ቤቶች እንደሚገኙበትና ይህንንም ለማስተካከል በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው ሲነገሩ እንደተሰማው በየማረሚያ ቤቶቹ ላይ ከዚህ ቀደም ሲፈፀም እንደነበረው የመብት ጥሰት እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዳይኖር ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡ አሁን ላይም ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከዚህ ቀደም የነበረው ችግር አለመኖሩን ባደረግነው ክትትል አረጋግጠናል ብለዋል። ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥም የዳሰሳ ጥናት መደረጉንና ይህም ራሳቸውን ታራሚዎች፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች ወገኖች የተሳተፉበት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
ዋነኛ የለውጥ ስራ ለማድረግም በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ሀላፊዎችን በአዲስ እንዲተኩ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በማረሚያ ቤቶች ያለውን የታራሚዎች አያያዝ ይበልጥ ለማሻሻልም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የሚገኙ አራት ማረሚያ ቤቶች በአዲስ እየተገነቡ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገነባው ማረሚያ ቤት ግንባታው 96 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን በዚህ አመት ስራ ይጀምራል ተብሏል፡፡
በዚህ አመት ከየማረሚያ ቤቶቹ ከ6 ሺ በላይ ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ተደርጓል መባሉን ተሰምቷል።
ምንጭ፦ ሸገር 102.1

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ለሰው ልጆች ፍቅር
ለሰው ልጆች ሰላም
ለሰው ልጆች በዓለም ዙሪያ ሁሉ
ሰላም ይሁን ምድሩ ሁሉ።
ፈጣሪ እስከዘላለሙ አፋቅሮ ያኑረን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሰው ልጆች ሰላም
ለሰው ልጆች በዓለም ዙሪያ ሁሉ
ሰላም ይሁን ምድሩ ሁሉ።
ፈጣሪ እስከዘላለሙ አፋቅሮ ያኑረን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥር 1 እስከ ጥር 21...
የምንሰራቸው ስራዎች፦
1. በየዕለቱ ሰላምን ፍቅርን እና አድነትን የሚመለከቱ በቻናላችን የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሁላችንም በፌስቡክ ገፃችን ላይ መለጠፍ።
2. ስለሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት የሚገልፁ መልዕክቶችን ለወዳጆቻችሁ መላክ።
3. #ጥላቻ እና #ዘረኝነትን የሚሰብኩ የፌስቡክ ጓደኞችን #ብሎክ ማድረግ።
4. የተለያዩ የሀሰተኛ መረጃዎች የሚሰራጩባቸውን የፌስቡክ ገፆች አለመከተል።
5. ስድብ፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ብሄር ተኮር ጥላቻዎችን የምትሰሙባቸውን ሚዲያዎች ማግለል።
የቻናላችን አባላት በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ከጥር 1 እስከ ጥር 21 የሰላም፣ የፍቅር እና አንድነት ሳምንታት ታውጇል!!

ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው፦
‹‹ሁኔታው አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ምንም ዓይነት ምክንያት ይቅረብለት በዚህ ዓይነት የግጭት ወቅት ንጹኃንን መጠበቅና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባ ነበር፡፡››
‹‹ኃላፊነት የጎደለው፣ ትክክለኛ ያልሆነ እርምጃ ተወስዷል፤ በደረሰው ጉዳት ኃላፊነት መውሰድ ያለበት አካል ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል፡፡››
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሁኔታው አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ምንም ዓይነት ምክንያት ይቅረብለት በዚህ ዓይነት የግጭት ወቅት ንጹኃንን መጠበቅና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባ ነበር፡፡››
‹‹ኃላፊነት የጎደለው፣ ትክክለኛ ያልሆነ እርምጃ ተወስዷል፤ በደረሰው ጉዳት ኃላፊነት መውሰድ ያለበት አካል ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል፡፡››
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አራት ሀገራት ይካፈሉበታል ተብሎ በሚጠበቀውና በአስመራ አስተናጋጅነት በሚካሄደው “የሠላም እና የወዳጅነት ዋንጫ” ላይ እንደሚሳተፍ ፌዴሬሽኑ ማረጋገጫ ሰጠ። በየካቲት ወር በአስመራ አስተናጋጅነት በሚካሄደውና በኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ወጣት ቡድኖች መካከል በሚደረገው ‘የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ’ ላይ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን እንደሚሳተፍ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። የአራቱን አባል ሀገራት ወዳጅነት እና የዞኑን የእግርኳስ ትስስር ለማጠናከር ታስቦ ለመጀመርያ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደሚካፈል እና ከቀናት በኋላ ዝግጅት እንደሚጀምር ተነግሯል።
ምንጭ፡-ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡-ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት!
‹‹ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት መጠናከሪያ እንጂ #የነውጥ እና #የጥላቻ መነሻ መሆን #አይገባቸውም፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
‹‹ማኅበረሰቡ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገረ ሽማግሌዎች የተቋሙን #ሰላም ለማስጠበቅ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመቀናጀት እየተሠሩ ነው›› የደሴ ከተማ ነዋሪዎች
‹‹ዩኒቨርሲቲውን እየፈተኑ ያሉት በውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሆኑ #የውጭ ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ
https://telegra.ph/ውሎ-ዩኒቨርሲቲ-01-10

ውሎ ዩኒቨርሲቲ፦
ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ተምሳሌት እንጅ የችግር መነሻ መሆን እንደማይገባቸው ነው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተናገሩት። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ዙሪያ ትልቅ ሥራ ሠርቷል። የወሎ የኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው በየነ ሰጠኝ እንደተናገረው የዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መረጋገጥ የተማሪዎች ሰላም ወዳድነት ትልቁን ቦታ ይይዛል። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር፣…
#Update አቃቤ ህግ በሜጀር ጄኔራል #ክንፈ_ዳኘው እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መሠረተ። በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በመዝገብ ቁጥር 229396 ዛሬ በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከእርሳቸው በተጨማሪ በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ረመዳን ሙሳ፣ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ አቶ ቸርነት ዳና ላይ ክስ መመስረቱን አቃቤ ህግ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት አስታውቋል። በዚህም መሠረት ተጠርጣሪዎቹ በ10ኛ ወንጀል ችሎት የነበራቸው መዝገብ ተዘግቶ ጉዳያቸው በ15ኛ ወንጀል ችሎት እንዲታይ ተደርጓል።
ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ከጥር 3 – 4 ቀን 2011 ዓ.ም በሴራሊኒዮን ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ጉብኝቱ የሚካሄደው የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የሴራሊዮን ኢትዮጵያን ወዳጅነት ሊያጠናክር የሚችል ምክክር የሚደርግ ሲሆን የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ‼️
የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ስለ ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርና ስለ መከላከያ ዩኒፎርም ተጠይቀዋል። ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ምዕራብ ጎንደርና ትግራይ መከላከያው የወሰደው እርምጃና ያሳየው ትዕግስት አድሎአዊ ነው ስለመባሉም ተጠይቀዋል።
“ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት አጋጣሚ በመጠቀም ራሳቸውን በገንዘብ ማበልፀግ የሚፈልጉ ሰዎች በጦር መሣሪያ ንግድ ላይ ተሠማርተው ተገኝተዋል” ሲሉ የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ይህ ሁኔታም በተለያየ ቦታ “ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር እንዲኖር መንገድ ከፍቷል” ብለዋል።
ለሁለቱም ችግሮች መፍትኄ ለማግኘት መንግሥታቸው እየሠራ መሆኑን የጦር አዛዡ ተናግረዋል። ጄኔራል ብርሃኑ በሃገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ላይ በዚህ ሣምንት ፓርላማው ፊት ቀርበው የሰጡትን ማብራሪያ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በምዕራብ ኦሮምያ፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች ውስጥና በመካከላቸውም ያለውን የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ መሥሪያ ቤታቸው ሰሞኑን ስለሚሠነዘሩበት ወቀሳዎች፤ እንዲሁም ካለመረጋጋቱ ጋር ተያይዞ ‘የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር አገሪቱን መምራት አቅቶታል’ እየተባለ ስለሚወራው ጉዳይ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።
ምንጭ፦ VOA

አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 3 ተማሪዎች ሞተው ከተገኙ በኃላ የተቋሙ ተማሪዎች ለደህንነታችን ስጋት ገብቶናል፤ ተማሪዎቹ በምን ምክንያት እንደሞቱ ይነገረን ካለበለዚያ ትምህርት መቀጠል ይከብደናል ሲሉ ገልፀዋል። በተማሪዎቹ ቅሬታም ረቡዕ ሊሰጥ የነበረው የMid Exam ሳይሰጥ ቀርቷል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ግቢውን ለቀን እንሄዳለ ባሉ ተማሪዎች እና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። ዩኒቨር ሲቲው ረቡዕ የተቋረጠው ፈተና በመጭው ሰኞ እንዲቀጥል ሲል ማስታወቂያ አውጥቷል።
🔹ፖሊስ ምርመራ እያደረኩ ነው በቅርቡም የምርመራ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ሲል ከቀናት በፊት ገልጿል። የተማሪዎቹ ሞት ከሚጡበት አካባቢ ጋር የተያያዘ ስላለመሆኑ ፖሊስ ገልጿል፦ "ተማሪዎቹ ከመጡበት አካባቢ ጋር ተያይዞ ጥቃት እንደደረሰባቸው የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አላገኝንም፤ ተማሪዎቹም ከተለያየ አካባቢ ነው የመጡት" የአዳማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደረጀ ሙልዕታ

#Update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም፤ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የለዉጥ እንቅስቃሰ ሂደት፤ እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ:- EPRDF Official
@tsegabwolde @tikvqhethiopia
ምንጭ:- EPRDF Official
@tsegabwolde @tikvqhethiopia
#Update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ከ60 በላይ የኢፌዴሪ አምባሳደሮች በመጪው ሰኞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ይወያያሉ፡፡ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮችና አምባሳደሮች የአገሪቱ ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሚዳብርበት ሁኔታ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ አሃዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አሃዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹመት!
አቶ #ነቢያት_ጌታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ መለስ አለም የኬንያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አቶ ነቢያት ጌታቸው ቃል አቀባይ ሆነው የተሾሙት።
አቶ ነቢያት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለበርካታ አመታት ያገለገሉ ሲሆን በዲፕሎማሲ ልምድ አካብተዋል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና ካሪቢያን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሆነውም አገልግለዋል። በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካና የአኢኮኖሚ ትብብር አማካሪ፤ በስዊድንና በኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የፖለቲካ ደስክ ዲፕሎማት ነበሩ።
አቶ ነቢያት ከእንግሊዙ ሊድስ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ኮሚዪኒኬሽን ማስተርስ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሰሩት ደግሞ በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ ነው።
ምንጭ፦ BBC