TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አማራ ክልል ወሎ በኦሮሞና አፋር አዋሰኝ ድንበር ላይ ባለፉት ሦስት ቀናት በተባባሰው ግጭት ቢያንስ የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲቀጠፍ፤ ሌሎች 12 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ለDW ዛሬ ተግረዋል። የግጭቱ መንስዔ በባቲ ዙሪያ እና አፋር አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች መካከል በተከሰተ የግጦሽ መሬት ይገባኛል ጸብ መኾኑ ተገልጧል።

Via~DW Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ቶሎሳ እንዲህ ብለዋል...

"ጀርመን ሄጀ የወለድኩት ልጅ ጀርመነኛ ቢናገር፣ እንግሊዝ የወለድኩት ልጅ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ቢሆን፣ ጣሊያን ሀገር የወለድኩት ጣሊያንኛ ተናጋሪ ቢሆን ልጆቼ የተለያየ ቋንቋ ስለተናገሩ ወንድማማችነታቸው ይፋቃል ወይ? እኔስ ኦሮሞኛ፣ አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኔ ወይም ልጆቼ የሚናገሩትን ቋንቋ ስላልተናገርኩ አባትነቴ ይፋቃል ወይ? የሚያዛምደን ስጋና ደማችን እንጅ #ቋንቋችን አይደለም፤ ስለዚህ እኛ #ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ መናገራችን ሊከፋፍለንና ሊያጋጨን አይገባም"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት 4ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ለምክር ቤቱ የቀረበውን የክልሉን አስፈፃሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት 18 የነበሩ የስራ አስፈፃሚ ተቋማት ወደ 14 ዝቅ ተደርገዋል፡፡ ምክር ቤቱ ሌሎች አዋጆችንም መርምሮ አፅድቋል፡፡

በዚህም የጠቅላይ አቃቢ ህግን ለማደራጀት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ እና የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ ከሰኔ 16ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት ጋር በተያያዘ የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ባበክር ሃሊፋን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ሙለታ ወንበር እንዲሁም ምክትል አፈ
ጉባዔ አቶ ደርጉ ዚያድ ለምክር ቤቱ የስልጣን መልቀቂያ ያቀረቡ ሲሆን በምትካቸዉ ዋና እና ምክትል አፈ ጉባዔ ተሸሟል፡፡

በዚህም መሰረት አቶ ሃብታሙ ታዬ ክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ፣ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ተደርገዉ ተሸመዋል፡፡

በተመሳሳይም የክልሉ ዋና ኦዲት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ፀሃይ ሞርካ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸዉን ለምክር ቤቱ አቅርበዉ ተቀባይነት በማግኘቱ በምትካቸዉ አቶ ከማል ሃሰን የክልሉ ዋናዉ ኦዲት ቢሮ ሃላፊ ሆነዉ ተሸመዋል፡፡ በርእሰ መስተዳድሩ የቀረቡ የመንግስት አካላት ሹመት ምክር ቤቱ አፅድቋል፡፡

1ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ ለክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር

2ኛ. አቶ አበራ ባየታ ለክልሉ የሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ

3ኛ. አቶ ሙሳ አህመድ ለክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ

4ኛ. አቶ ዚያድ አብዱላሂ ለክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ሃላፊ

5ኛ. ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ለክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ

6ኛ. አቶ ኢብራሂም ዑመር ለክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

7ኛ. አቶ አሊ ኢብራሂም የክልሉ አከባቢ፣ደንና መሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

8ኛ. አቶ ቀልቤሳ ኦልጂራ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

9ኛ. አቶ አካሻ ዑስማዔል የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ

10ኛ. አቶ ፀጋዬ ተሰማ የክልሉ ዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ

11ኛ ወ/ሮ ፀሃይ ሞርካ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

12ኛ ወ/ሮ ሃጂራ ኢብራሂም የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ

13ኛ. አቶ ቶማስ ኪዊ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነዉ ተሸመዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃ🔝

"እነዚህ ሁለት ፎቶዎች እና አንድ ወይም ሁለት ሌሎች ቪድዮዎች በብዛት ሼር ሲደረጉ ነበር። አንዳንዶች #አልሻባብ የማረካቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲሉ ሌሎች ሀገር ውስጥ የሆነ ነው ያሉም ነበሩ። ሶማልያ ካለ አንድ ጋዜጠኛ ጓደኛዬ እና ከጋዜጠኛ ኤልያስ ገ/ስላሴ ጋር በመሆን ማጣራት የቻልኩት የሚከተለው ነው: በአሁን ሰአት ሶማልያ ውስጥ በሳድ እና ማሬሀን ጎሳዎች መሀከል በመሬት ምክንያት ግጭት ተቀስቅሷል። ቪድዮው ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ከማሬሀን ጎሳ ጎን ሆነው ሲዋጉ የተያዙ ናቸው የተባሉ ሲሆን የሞቱም አሉ ተብሏል። ማሬሀን የአሁኑ ፕሬዝደንት ፎርማጆ ጎሳ ነው። አንዱ ቪድዮ ላይ ኢትዮጵያውያኑ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ እንዲያምኑ ሲገደዱ ያሳያል። ይህም ለፕሮፓጋንዳ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ተብሎ ሊታሰብ ይችላል። የአልሸባብ ታጣቂዎች ናቸው እና ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተ ነው የተባለውን ግን ሀሰት ነው።"

Via~ELIYAS MESERET
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

የአፍሪቃ መዲና ናት በምትባለዋ ትልቋ ከተማ መኪና አቁሞ መንገድ ላይ #መሽናት ምን ይሉታል?? ይህ እጅግ እየተለመደ የመጣ ድርጊትም ሆኗል። ይህ ጥሩ ተግባር አይደለም ቢቀርብንስ...!??

ፎቶ፦ ቴዲ አበራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

"ቴሌ ስለነሱ የሚነሱ #ቅሬታዎች ቢዘረዘሩ አንድ ቀን እንኳን የሚበቃ አይመስለኝም። ህዝቡም አማራጭ ስላጣ እንጂ የነሱ አገልግሎት ተስማምቶት አደለም። አሁን ደግማ የADSL ወይንም የባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት እናስገባለን ብለው ሲያስተዋውቁ የሰማችሁ ይመስለኛል አገልግሎቱም በፍጥነት እንሰጣለን ሲሉ እንዲሰማችሁ እርግጠኛ ነኝ ይህ ግን ከእውነታው የራቀ ነው እንኳን በፍጥነት ይቅርና በስርዓት እራሱ የሚያነጋግር የለም። በተለይ #በኮተቤ #መሳለሚያ ቴሌ ያለዉ ሁኔታ በጣም ያሳዝናል። ይኸው ከወር በፊት ያመለከቱት ለአገልግሎቱም ክፍያ ያጠናቀቁ እራሱ አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም። ቅሬታ እንኳን የሚሰማ የለም። የሚገርመው ወር ሲማላ ክፍያ መጠየቃቸው ነዉ ላልተሰጠ አገልግሎት። ቴሌ ተቆጣጣሪ ያለው መስሪያ ቤት እራሱ መሆኑን እጠራለሁ። የሚመለከተው አካል ካለ ይህንን ቅሬታ ቢያተኩርበት መልካም ይመስለኛል ምክንያቱም ህዝብ የናንተን አገልግሎት ተስፋ በመቁረጥ እየጠበቀ ነዉና።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ፦ ትላንት፣ ዛሬ እና ነገ” የሚል ርዕስ ያለዉን ስዕል ለ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ሰዕሊ ተክለ ማርያም ዘውዴ አበርክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ግጭት ለሳምንታት በስጋት ቆየን ያሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን ለቀው በመውጣት ወደ ክልላቸው ተመልሰዋል። ተማሪዎቹ ትናንት ምሽት ባህርዳር የገቡ ሲሆን ተማሪዎች ለሊቱን በባህርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አሳልፈዋል።

ምንጭ፦ Ethiopia Live Update
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ🔝

የሰማያዊ ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ከሰዓታት በፊት (ፒያሣ አትክልት ተራ ባለው ካሊፋ ህንፃ 3ኛ ወለል/ፎቅ) ጀምሯል፡፡ ይህ ጉባዔ በኢትዮጵያ ተቃውሞ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ልዩና ታሪካዊ ውሳኔ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል፡፡

ምንጭ፦ አቶ ዳንኤል ሺበሺ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጃል መሮ‼️

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን አንግሷል። ይህን ብቻ አይደለም በቅርቡ በክልሉ ውስጥ ለሚፈጸሙ ግድያዎች እና ዘረፋዎች መንግሥት ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል።

በቅርቡ የክልሉ ፖሊስ እና ባለስልጣናት በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ኦነግን የአከባቢው አስተዳደሮችን ይገድላል፣ ጦር መሳሪያ ይዘርፋል እንዲሁም ሚሊሻዎችን ትጥቅ ያስፈታል ሲሉ ከሰዋል።

ኩምሳ ዲሪባ ወይም በትግል ስሙ ጃል መሮ ተብሎ የሚታወቀው በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ጦር አዛዥ ነው።

ጃል መሮ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሳው የኦነግ ሠራዊት ዘንድ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ብቻም ሳይሆን አንዳንዶች ከሊቀመንበሩ ዳውድ ኢብሳ እዝ ነጻ ሆኖ በራሱ የሚንቀሳቀስ ቡድንን የሚመራ እንደሆነ ይነገርለታል።

ቢቢሲ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ሁኔታ እና ከኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስላለው ግነኙነት #ከጃል_መሮ ቃለምልልስ አድርጓል።

ቢቢሲ ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የኦነግ ጦር ተልዕኮው ምንድነው?

ጃል መሮ፡ ኦነግ የራሱ የሆነ ፍላጎት ወይም ተልዕኮ የለውም። ኦነግ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትን ነው የሚያስጠብቀው። ጦሩም የኦነግን ተልዕኮ ነው የሚወጣው። ይሄው ነው።

ቢቢሲ ፡ የኦነግን ጦር ወደ ካምፕ በማስገባቱ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አቋም ምንድነው?

ጃል መሮ፡ በቀላል ቋንቋ ላስረዳህ። በአንድ ቤተሰብ አባለት ውስጥ አባት፣ እናት እና ልጆች ይኖራሉ። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ወላጆች ማለትም እናት እና አባት እስካሉ ድረስ ቤተሰባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት የሚኖርባቸው እነርሱ ናቸው፤ ልጆች አይደሉም። የኦነግ ጦር ወደ ካምፕ ይግባ ወይም አይግባ በሚለው ላይም የኦነግ አጠቃላይ አመራሮች የሚወስኑትን ነው እኛ የምናስፈጽመው። ወደ ካምፕ እንገባለን ወይም አንገባም የሚለውን እኔ ልመልስ አልችልም።

ቢቢሲ ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ጦር ከሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ትዕዛዝ ውጪ ነው ይባላል። ከአቶ ዳውድ ቁጥጥር ውጪ ናችሁ?

ጃል መሮ፡ በምዕራብ ዞን የሚገኘውም ይሁን በሌሎች ዞኖች ውስጥ የሚገኘው የኦነግ ሥራዊት በሙሉ ተጠሪነቱ፣ የሚመራውም፣ ትዕዛዝ የሚቀበለውም ከኦነግ ሊቀመንበር ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ነው። አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር ናቸው። የኦነግ ጦር ደግሞ ካሉት የኦነግ ዘርፎች አንዱ ነው። ስለዚህ ተጠሪነቱም ለሊቀመንበሩ ነው። በአጭሩ ይሄው ነው። ከዚህ የተለየ ነገር የለም።

ቢቢሲ ፡ በቅርቡ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር በምዕራብ ኦሮሚያ ተገናኝታችሁ እንደተወያያችሁ ተሰምቷል። የውይይታችሁ ርዕሰ ጉዳይ ምን ነበር?

ጃል መሮ፡ አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር እና የጦር የበላይ አዛዥ ናቸው። ከእሳቸው ጋር ብዙ ጉዳዮች ያገናኙናል። ብዙ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ውይይታችንም አንዴ ወይም ሁለት ጊዜ አይደለም። በቋሚነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ይህ አዲስ ነገር አይደለም። የተወያየንበትን ርዕሰ ጉዳይ ማወቅ ካሻህ ግን እሳቸውን ደውለህ ጠይቅ።

ቢቢሲ ፡ ሰሞኑን እርሶ ለኦነግ ወታደሮች ያስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ የተነገረ ደምጽ በርካቶች በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ሲቀባበሉት ነበረ። ድምፁ የእርስዎ ነው?

ጃል መሮ፡ ስለ ጉዳዩ የማውቀው ጉዳይ የለም። እስቲ ነገረኝ፤ ምንድነው እሱ?
ቢቢሲ ፡ በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሰዎች ሲጋሩት የነበረው ወደ 48 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው የእርስዎ ነው በተባለ ደምጽ፤ 'ትጥቅ ያስታጠቀንም ሆነ የሚያስፈታን የለም' የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ነው የተላለፈበት።

ጃል መሮ፡ እንዲህ ባለ ጉዳይ ላይ ድምጽ ቀርጸን አናሰራጭም። ይህ የምትለው ድምጽ የት እንደተቀረጸ፣ ማን እንደቀረጸው እና እኔ መሆኔ መረጋገጥ አለበት።

ቢቢሲ ፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ አስተዳዳሪዎችም እንዲሁም በቅርቡ አቶ ለማ መገርሳ ለካማሼ ዞን አስተዳደሪዎች ግድያ ተጠያቂው የኦነግ ጦር ነው ብለዋል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምነድነው?

ጃል መሮ፡ በዚህ አካባቢ የታጠቀ ኃይል በርካታ ነው። የታጠቀ የመንግሥት አካል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጣቂዎች እንዲሁም የኦነግ ታጣቂዎች በስፍራው ይንቀሳቀሳለሁ። ይህ ሁሉ ታጣቂ ቡድን ባለበት ኦነግ ላይ ብቻ ጣት መቀሰር አይቻልም፤ ትክክልም አይደለም። ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል ወንጀሉን የፈጸመውን ማጣራት አለበት።

ቢቢሲ፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኦነግ በምዕራብ ኦሮሚያ የመንግሥት ሥርዓትን ይንዳል፣ ጦር መሳሪያዎችን ይዘርፋል የሚሉ በርካታ ክሶችን ይሰነዝራል። እርስዎ ምን ይላሉ?

ጃል መሮ፡ ከዚህ ቀደም ጦርነት ላይ ነበርን። ስንዋጋ ነበረ። የሚወጋንን ጦር አስተዳደራዊ ሥርዓቱን፣ ፖሊስን፣ ሚሊሻውን መበጣጠስ ደግሞ ግድ ነው። የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከደረስን በኋላ ኦነግ በራሱ ተነሳሽነት መንግሥት ላይ ተኩስ ከፍቶ አያውቅም፤ አጸፋዊ እርምጃ ካልወሰድን በቀር።

ይህ ሁሉ ክስ ግን ሃሰተኛ ነው። መንግሥት ይህን ክስ የሚያቀርበው በዚህ አካባቢ ላይ ጦሩን በማዝመት ጦርነት ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት ሲያከናውን ነው እንጂ ኦነግ ያፈረሰው የመንግሥት ሥርዓት የለም፤ የዘረፈውም የጦር መሳሪያ የለም። እንደውም የኦነግ ጦር ሥነ-ምግባር በተሞላበት መልኩ ተቆጣጥሮ ከያዘው ስፍራ አልተንቀሳቀሰም።

ቢቢሲ ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ ተቆጣጥሬያለሁ የሚለው መሬት የትኛውን ነው?

ጃል መሮ ፡ እሱን የምዕራብ ኦሮሚያ ህዝብን መጠየቅ ትችላለህ።

ቢቢሲ ፡ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሰማራው የሃገር መከላከያ ጦር ጋር የተፈጠረውን ግጭት ይንገሩኝ እስቲ

ጃል መሮ፡ የመጣብንን ጠላት መመከት እና ወደ መጣበት የመመለስ ችሎታውም ሆነ አቅሙ አለን። መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ ነን። አሁንም ቢሆን የመጣብንን ኃይል እየተከላከልን እንገኛለን። በዚህ መካከል ግን ችግር ውስጥ እየገባ ያለው እና እየተሰቃየ ያለው የኦሮሞ ህዝብ ነው። የመንግሥት ጦር ውስጥም ያሉት ወታደሮች ህጻናት እና የደሃ እናት ልጆች ናቸው። ይህ ግጭት ግን ለሁለቱም [ኦነግ እና መንግሥት] ወገን የሚያስገኘው ጥቅም የለም። በዚያም ሆነ በዚህ እየተጎደ ያለው ኦሮሞው ነው።

ቢቢሲ ፡ ለዚህ መፍትሄው ምንድነው?

ጃል መሮ፡ የግል የፖለቲካ ጥቅምን ለማስጠበቅ ከማሴር ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ብናስቀድም፤ ይህ ሁሉ ችግር በአንድ ለሊት መፍትሄ ያገኛል። የግል የፖለቲካ ጥቅም ከህዝብ ፍላጎት ካስቀደምን ግን ለዚህ ችግር መቼም ቢሆን መፍትሄ አይገኝም።

ቢቢሲ ፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ ኦነግ ሰላማዊ ትግል ለማካሄደ ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኋላ ጦር እንደ አዲስ በመመልመል እያሰለጠነ ይገኛል ይባላል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው?

ጃል መሮ፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ የተካሄደ ምንም አይነት ስልጠና የለም።

ቢቢሲ ፡ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምን ያስባሉ?

ጃል መሮ ፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልግም።

ቢቢሲ ፡ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ለውጦች መጥተዋል። እርስዎ የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን አግኝቷል ብለው ያምናሉ? ወይም ኦሮሞ ነጻነቱን የሚጎናጸፈው መቼ ነው?

ጃል መሮ፡ እኔ እንደ አንድ ግለሰብ ነጻነቴን አላገኘሁም። ህዝቡም የእራሱን መልስ መስጠት ይችላል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia