TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለተማሪዎች🔝

ሚዛን ቴፒ እና ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን ጠርተዋል። አዲስ እና ነባር ተማሪዎች ከላይ ባለው ማስታወቂያ መሰረት ወደተቋማችሁ ለመግባይ ዝግጅት አድርጉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ አባ ገዳዎች የሰላምና ዕርቅ ተልዕኮ አንግበው ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ሊሄዱ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ አባ ገዳዎች በቀጣዩ ሳምንት ወደ ቦታው የሚያቀኑት መንግሥት በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ነው፡፡ በጠመንጃ ልዩነትን መፍታት እንደማይገባ በማመን በምዕራብ ኦሮሚያ ሰላም ሳናወርድ አንመለስም- ብለዋል አባ ገዳዎቹ፡፡

Via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት በሰላም ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን በማህበራዊ ድረገፅ የሚራገበው #የተሳሳተ መረጃ ትክክል እንዳልሆነ እየገልፅን ዩኒቨርሲቲው በአሁን ወቅት ፍፁም ሰላማዊ እና በተረጋጋ መንገድ የትምህርት እና ማህበራዊ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።" የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት በሀሰተኛ ማስረጃ በማህበር ለተደራጁ ግለሰቦች ይህን ማስታወቂያ አውጥቷል።

Via Haile Alene
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማሮ ወረዳ‼️

በአማሮ ወረዳ #ታጣቂዎች በድጋሚ ጥቃት አደረሱ። በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 4 ሰዎችን ገድለው 1 ማቁሰላቸውን የወረዳው መስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ማዳሞ ለDW እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው የኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞንን በምትዋሰነውና ካርማ ጅላ በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው፡፡

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎችን ገድለው እንድ ማቁሰላቸውን የወረዳው መስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ማዳሞ ለዲ ደብሊው እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው የኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞንን በምትዋሰነውና ካርማ ጅላ በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው፡፡

በጥቃቱ ከሞቱት ነዋሪዎች መካከል ሶስቱ የሸንኮራ አገዳ ምርት በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ሲሆኑ አንዱ ግን በከብት ጥበቃ ላይ የተሰማራ ታዳጊ እንደነበር ዋና አዛዡ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ገልጸዋል፡፡ በሥፍራው ነበርኩ ያሉ እንድ የአይን እማኝ በበኩላቸው ጥቃት አድራሾቹ በከፈቱት የተኩስ እሩምታ የተደናገጡ መምህራንና ተማሪዎች ወደ አጎራባች መንደሮች መሸሻቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሌት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) ከኦነግ በስተቀር በክልሉ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። ፓርቲው በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በምን መልኩ እየሰራ እንደሆነ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የኦዴፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት የህዝብ አስተያየትና የህዝብ ግንኙነት ክፍል ዳይሬክተር አቶ #ታዬ_ዳንዳአ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፤ የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ ለማስቀጠል ከአንድ ፓርቲ በቀር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

Via~ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአውሮፓ ህብረት ተወካይ በ48 ሰአት ኪንሻሳን ለቀው እንዲወጡ ህብረቱን አሳሰበች፤የአውሮፓ ህብረት እኤአ ታህሳስ 30 /2018 እጩ ፕሬዚዳንት ሆነው የሚወዳደሩትን ጆሴፍ ካቢላን ጨምሮ 15 የኮንጎ ባለስልጣናት ላይ ለጣለው ማዕቀብ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ ምሁራንንና ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ ፎረም ሊያቋቁም መሆኑን ተናግሯል፡፡ ፓርቲው ከኦነግ በስተቀር በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች ተፎካካሪ ድርጅቶች ጋር በሕግ የበላይነት፣ የዴሞክራሲ ስርዓት የግንባታ፣ የተቋማት ግንባታ፣ የኢኮኖሚ እድገት እና የክልሉን #ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ በመግባባት መንፈስ እየሰራ ነው፡፡

በሌላ ዜና...

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ(ኦዲፒ) ከሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውህደት ለምፍጠር ድርድርእያካሄደ መሆኑን ገለጸ፡፡ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴው ፅህፈት ቤት ሃላፊ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ደንደአ እንደተናገሩት ኦዲፒ በጀኔራል ከማል ገልቹ ከሚመራው የኦሮሞ ብሄራዊ ድርጅትና በአባ ነጋ ጃራ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡ ውይይቱም ሁለቱ የፖለቲካ ድርጀቶች ከኦዲፒ ጋር #መዋሀድ በሚችሉበት ነጥብ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ fbc,ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ33 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ዱባይ ልታስወጣ የነበረች #ተጠርጣሪ ተያዘች፡፡ግለሰቧ 33 ሺህ 250 የአሜሪካ ዶላርና 6 ሺህ 500 የሳውዲ ሪያል በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ዱባይ ልታስወጣ እያለች ነው በቁጥጥር ሥር የዋለችው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት በእነ #ጎሃ_አፅበሃ መዝገብ የተካተቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በተጠረጠሩ 33 ግለሰቦች ላይ ለፖሊስ ከ10 እስከ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። መርማሪ ፖሊስ ያላጠናቀቃቸው የምርመራ ስራዎች እንዳሉት በመግለፅ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር #ወርቅነህ_ገበየሁ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ወረዳ የሚገኘውን የኩየራ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ከነገ በስተያ - ዕሁድ ይካሄዳል ለተባለው ምርጫ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንና ፀጥታና ደኅንነቱም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠበቅ ፕሬዚዳንቱ #ጆዜፍ_ካቢላ ዛሬ አስታውቀዋል።

Via~VOA
@tsegabwolde @tikvhethiopia
የሟቾች ቁጥር 19 ደርሷል‼️

በሱዳን የነዳጅና የዳቦ ዋጋ #መጨመርን ተከትሎ በተከሰተው የኑሮ ውድነት ምክንያት በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ #የሞቱት ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱ ተገለፀ።ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭትም እስካሁን ሁለት የፖሊስ አባላትን ጨምሮ የ19 ሰዎች ህይዎት ማለፉን የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ቦሻራ ጁማ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የጦርነት እና የጥላቻ ንግግሮችን #እቃወማለሁ። "ሌላውን" ህዝብ በመሳደብ የሚገኝ "ጀግንነት" ይቅርብኝ። የሚያለማኝን ሰላም ትቼ የሚያጠፋኝን ግጭት አልመኝም። ሰው ሁሉ ወገኔ ነው። ለጥላቻ ሳይሆን ለህዝብ ፍቅር አሜን በሉ። አሜን!" #አብርሃ_ደስታ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ጉጅ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ ፊንጨዋ ከተማ ላይ የመከላከያ ሰራዊት አደረሰ በተባለ ጥቃት 11 ሰዎች ሲገደሉ ከ20 በላይ ቆስለዋል መኖሪያ ቤቶችና ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ከተማ ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት በተተኮሰ ጥይት የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ቢያንስ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት

🔹በደረሰው አሳዛኝ ክስተት መንግስት የሚሰጠው መግለጫ ካለ ወድእናተ አደርሳለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መነ ቤኛ‼️

ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ መነ ቤኛ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በጥይት ተመተው #መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።

የዞኑ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ተረፈ፤ የተገደሉት ሁለቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት የፊንጫአ ኃይል ማመንጫ እና ጌዶ ከተማ ላይ የሚገኝ የኃይል ማከማቻ ጠባቂዎች ነበሩ ብለዋል።

''መኪና ላይ ሆነው ወደ ፊንጫአ እየተጓዙ ሳሉ ተኩስ ተከፈተባቸው'' በማለት አቶ ደሳለኝ ሁኔታውን ያስረዳሉ።

ጥቃቱን ማን እንደሰነዘረ አልታወቀም የሚሉት አቶ ደሳለኝ የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ትናንት እኩለ ቀን ገደማ መገደላቸውን ተናግረዋል።
በምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢዎች የጸጥታ መደፍረስ ካጋጠመ ሰንብቷል።

የክልሉ መንግሥት በአከባቢው ለሚደርሱ ጥቃቶች የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ተጠያቂ ያደርጋል። በቅርቡ የኦዲፒ መአከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ ኦነግ የመንግሥት ባለስልጣናትን ይገድላል፣ የአስተዳደር ስርዓቱን ያፈራርሳል፣ ዘረፋ እና ሚሊሻዎችን ጦር ያስፈታል ሲሉ ኦነግን ከሰዋል።

በሌላ በኩል የኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ ድርጅታቸው ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰባቸው ጉዳዮች በመንግሥት እየተጣሱ ነው በማለት ቅሬታቸውን ይናገራሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የቁልቢ ገብርዔል ዓመታዊ ንግሥ በሰላም ተጠናቋል፡፡ በተመሳሳይ #የሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia