ጥቆማ‼️
"ከደንቢ ዶሎ-ጊንቢ ያለው መንገድ ከተዘጋ ዛሬ 6 ቀኑ ነው፡፡ ከትላንትና ጀምሮ በደንቢ ዳሎ ከተማ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም በርሀብ አለቅን!!"
ይህን መልዕክት ያደረሱት በስራ ጉዳይ ወደ ደንቢ ዶሎ ያቀኑና በአሁን ሰዓት በአንድ ሆቴል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ናቸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም ገነት ቆርቆሮ ፋብሪካና በግንባታ ላይ ያለው ፎር ፖይንት ሸራተን ሆቴል ባለቤት አቶ ዓለምፍፁም ገብረስላሴ ላይ የክስ መመስረቻ 10 ቀናት ፈቅዷል።
Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️ በመቱ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ አለመረጋጋት የዛሬው የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቋረጥ ሆኗል። የሚመለከተው አካል ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ እንዲፈልግ ተማሪዎች ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ነዳጅ የጫኑ ሁለት ቦቴ መኪኖች መነሻቸዉን ጅቡቲ በማድረግ ወደ ሀገር ዉስጥ ገብተው ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ ተሸከርካሪዎቹ ነዳጁን ወደ አዶላ እና ደባርቅ እንዲያደርሱ የተሰጣቸውን ፍቃድ በመጣስ ተመልሰው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡ ኮድ 95687/29557 ኢት የሆነ 46ሺ 700 ሊትር ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ደባርቅ እንዲሁም ኮድ 95829/29334 ኢት ተሳቢ ደግሞ 47 ሺህ 59 ሊትር ነዳጅ ጭኖ ወደ አዶላ ከተፈቀደላቸው መስመር ውጪ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በህብረሰቡ #ጥቆማ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ አሳዉቀዋል፡፡ ይሄን መሰል ህገ-ወጥ ደርጊት ለመከላከል መንግሥት ከምን ጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ደመላሽ ተናግረዋል፡፡ ህዝቡም እያደረገ ያለውን ንቁ ተሳትፎ ምስጋናቸዉን ገልጸዋል፡፡በቀጣይ ህገ ወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም መገለጹን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ
#tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ኢዜአ
#tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️
"ሰበር አፈትላኪ መረጃ" ተብሎ እና ከላይ ያለውን ምስል አስደግፎ እየወጣ ያለው መረጃ #ሀሰት እንደሆነ ቢታወቅ! "በእርግጥ በምእራብ ኦሮሚያ አንዳንድ ስፍራዎች የፀጥታው ችግር እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም በሂሊኮፕተር የታገዘ መከላከያ ሰራዊት ከኦነግ ጋር #እየተፋለመ ነው ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ ከተወሰነ አቅጣጫ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የሀሰት ነው" ብለው አሁን ላይ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ በክልሉ በሀላፊነት ቦታ ያሉ ግለሰብ ዛሬ ከሰአት ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

ሸካ ዞን‼️
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል በሸካ ዞን ባለፉት ወራት ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት አገልግሎት አቁመው የነበሩ ተቋማት ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸው ተገለፀ።
የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ በአሁን ወቅት አንፃራዊ ሰላም የሰፈነበት መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሺዋስ ዓለሙ አስታውቀዋል።
በፀጥታ መደፍሱ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አሁን ላይ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ የገለፁ ሲሆን፥ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩንም አስረድተዋል፡፡
አስተዳዳሪው #የሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢም ተማሪዎችን ተቀብሎ የዓመቱን የትምርት መርሀ ግብር ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል።
በፀጥታ መደፍረሱ የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ ከመምህራን እና ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመሆን ይሰራልም ተብሏል፡፡
በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ አካባውን ለቀው የነበሩ ነዋሪዎችም ወደ ቀደመው ህይወታቸው እንደተመለሱም ተጠቁሟል።
በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ማህበረሰቡ ከመንግስት ጋር በትብብር እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል።
ምንጭ፥ SRTA

#update የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ #ቴፒ ግቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የዓመቱን የትምህርት መርሀ ግብር ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ከ8ዐ ሺ በላይ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ ድርሃም፣ የሳዑዲ ሪያል፣ የሱዳን ፓውንድ እና ከ271 ሺ ብር በላይ መያዙን አስታወቀ፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ ሁለቱ ተቋማት ታህሳስ 14 እና 15/2011 በጋራ በቦሌ ክፍለ ከተማ ባደረጉት የኦፕሬሽን ገንዘቡ መያዙ ተገልጿል፡፡ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታውቋል፡፡
ከተያዙት ገንዘቦች በተጨማሪ በሕገወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተዋል ያሏቸውን ልዩ ልዩ ቁሰቁሶችና በአንድ ሥፍራ ብቻ የተገኙ 1 ሺህ 23 የውኃ ቆጣሪዎች ተይዘው ሕጋዊነታቸውን ለማረጋገጥ የምርመራ ሥራ እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም በተደረጉ ተመሳሳይ የኦፕሬሽን ሥራዎች ከፍተኛ የውጪ ሀገር ገንዘቦች መያዛቸውን ኮሚሽኑ አስታውሶ ወደፊትም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ተግባሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
#ሕብረተሰቡ ለኮሚሽኑ ሥራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ትብብር ምሥጋናውን እያቀረበ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቋል፡፡
ምንጭ፦ ebc

ሀዋሳ‼️ሰኞ ታህሳስ 15 በሀዋሳ ከተማ የተፈጠረውን ሁኔታ የከተማይቱ ከንቲባ አቶ #ስኳሬ_ሹዳ ለBBC አብራርተዋል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከባለፈው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ #በተቀሰቀሰ ግጭት የመማር ማስተማር ሂደት ተቋርጦ ቆይቷል። አብዛኛዎቹ ተማሪዎችም ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ሆኖም በግቢው ውስጥ በቀሩ ተማሪዎች እና በዩኒቨርስቲው አስተዳደር መካከል በተደረገ ውይይት ትምህርት እንዲጀመር ተወስኖ፣ ትምህርቱ ከትላንት ጀምሮ በከፊል ተጀምሯል፡፡
Via~VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via~VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 75 መድረሱን የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ ከበደ፥ ኮሚሽኑ በዘጠኝ ቅርንጫፎቹ ሲያካሂድ በነበረው ምርመራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም እስካሁን በተከናወነው የማጣራት ስራ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
እስካሁን በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም፦
🔹ከኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ተቋም
አቶ ተሾመ ለገሰ- ዋና ዳይሬክተር
አቶ ተሾመ ከበደ- የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
ወይዘሮ መስከረም ዳባ- የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
🔹ከኦሮሚያ ግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ አመራር የነበሩ እና በአሁኑ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ
አቶ መሃመድ ቃሲም- ዋና ዳይሬክተር
አቶ እንዳልካቸው በላቸው- የኤጀንሲው የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
አቶ ይልማ ዴሬሳ- የኤጀንሲው የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል
አቶ አብዶ ገለቶ፦ የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር
አቶ መንግስቱ ረጋሳ፦ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚሮ ምክትል ሀላፊ የነበሩ በአሁኑ ወቅት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ
🔹ሻሸመኔ ከተማ
አቶ ፈይሳ ረጋሳ፦ የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ
አቶ አብዶ ገበየሁ፦ የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አቶ ገመዳ በዳሶ፦ የሻሸመኔ ከተማ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ
🔹ጅማ ዞን
አቶ ፋንታ በቀለ፦ በጅማ ዞን የማንቾ ወረዳ አስተዳዳሪ
በአጠቃላይ እስካሁን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉየመንግስት የስራ ሀላፊዎች ቁጥር 75 መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
ምንጭ፦ fbc

#update በጊንቢ ከተማ ሁለት ወጣቶች #በታጠቀ ኃይል #መገደላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ከትላንት በስቲያ አንድ በጉልበት ሥራ የሚተዳደር ወጣት ሲገደል፣ ትላንት ደግሞ የአእምሮ ጤና እክል ያለበት ወጣት ተገድሏል፤ ይላሉ የዓይን እማኞች፡፡ ከትላንት በስቲያ እና ትላንት ከተማውማዋ በከፍተኛ የጦር መሣሪያ ድምፅ ስትታመስ መቆየቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል፤ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት በበኩሉ #የመከላከያ_ሰራዊት ማንንም አልገደለም ብሏል፡፡
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
MesobTower!! #በመሶብ_ቅርፅ የተዘጋጀ አዲስ ህንፃ መዲናችን አዲስ አበባ ከ5-6 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ልታገኝ ነው። ህንፃው ባለ 70 ፎቅ፣ 250 ሜትር ከፍታ ያለው፣ 50 ሺህ ካሬና ከዛ በላይ የሚፈልግ፣ በ20 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚሰፍር እንደሆነ ተነግሯል። ፕሮጀክቱም በመንግስት እና የግሉ ዘርፍ በጋራ ፋይናንስ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻሸመኔ‼️
በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን ሻሸመኔ ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት እና ድብደባ የሚያሳየውን ቪዲዮ አስመልክቶ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ አደም ከማል ለሸገር ተናግረዋል።
“ሻሸመኔን የተመለከተው በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ቪዲዮ ከዛሬ 2 ወር በፊት የሆነ ነው፡፡ ሁለቱም ወገኖች ኋላ ላይ አጥፊው ወገን ካሳ እንዲከፍል ተደርጎ፣ ተመራርቀው ተለያይተዋል” ያሉት ከንቲባው፣ “ይህን ያለፈ ነገር ዛሬ እንደተደረገ አድርጎ ቪዲዮውን ማሰራጨት #ለማንም_የሚጠቅም አይደለም ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1

በሻሸመኔ ከተማ ተፈፅሟል የተባለው ድርጊት ከወር በፊት #በእርቅ የተፈታ ጉዳይ ነው፡- የከተማ አስተዳደሩ
.
.
በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የተፈፀመ ድርጊት በሚል የተለቀቀው አሰቃቂ ቪዲዮ ብዙዎችን በማህብራዊ ሚዲያ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ኢቢሲ ወደ ሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ደውሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ ስለተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ለማጣራት እንደሞከረው፣ ድርጊቱ የተፈፀመው በከተማዋ ይሁን እንጂ ከአንድ ወር ከ11 ቀን በፊት የተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ኮሙዪኒኬሽን ኃላፊው አቶ ሀሮን ከድር ለኢቢሲ እንደገለፁት ጉዳዩ ህዳር 6፣2011 በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል የተፈመ ፀብ ነበር፡፡
ፀቡን ተከትሎም ጉዳት በደረሰባቸው እና ድርጊቱን በፈፀሙት ወገኖች መካከል የፀጥታ አካላት፣የከተማው ከንቲባና የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት እርቀ ሰላም ከተፈፀመ ውሎ ማደሩንና ጉዳዩ አሁን ላይ በቪዲዮ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መለቀቁ የከተማዋን ገፅታ ሆን ብሎ ለማጠልሸት የታለመ መሆኑን አቶ ሀሮን ተናግረዋል፡፡
በሻሸመኔ ከተማ አሁን ላይ ምንም አይነት የተፈጠረ ችግር የለም ፤ከተማዋም የተረጋጋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተከናወነባት መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡